ሀንጋሪ የሕዝብ ቁጥሯን ለማሳደግ እናቶችን ከግብርና ከዕዳ ነፃ ልታደርግ ነው

ህፃን ልጅ በእጅ ተይዞ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የሀንጋሪ የህዝብ ቁጥር እየቀነሰ ሲሆን አሁን የሚወሰደው ርምጃ ችግሩን ያቃልለዋል ተብሎ ይታመናል።

የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚንስትር አራት አሊያም ከዚያ በላይ ልጆች ያሏት ሀንጋሪያዊ እናት ግብር ከመክፈል ነፃ እንደምትሆን አስታውቀዋል፤ የውልደት መጠንን ለመጨመርም እቅድ ተይዟል።

የሰው ልጅ ዘር እየመነመነ ነው

ጠቅላይ ሚኒስተር ቪክተር ኦርባን እንደተናገሩት እርምጃው በስደተኞች ላይ ጥገኛ ከመሆን የሚያድንና የአገሪቷን መፃኢ ዕድል የሚያሻሽል ነው ብለዋል።

የሀንጋሪ የህዝብ ብዛት በዓመት በ32 ሺህ ይቀንሳል፤ በአውሮፓ ኅብረት በአማካይ ከተቀመጠው የውልደት መጠን ሀንጋሪያን ሴቶች ያላቸው የልጆች ቁጥር ዝቅተኛ እንደሆነም ተነግሯል።

ይህንንም ለማስተካከል ከሚወሰዱ የመፍትሔ ሃሳቦች ከወለድ ነፃ የሆነ 36 ሺህ ዶላር (1 ሚሊየን ብር) ብድር የሚያገኙ ሲሆን ሦስት ልጅ ከወለዱ በኋላም ይህ ብድር ሙሉ በሙሉ ይሰረዝላቸዋል።

ለምዕራባዊያኑ የውልደት መጠን መቀነስ ምክንያቱ በአገር ውስጥ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር ሲሆን፤ ለአንድ ቁጥሩ ለቀነሰ ህፃን በሌላ ስደተኛ ህፃን ስለሚተካ ቁጥሩ ያን ያህል አሳሳቢ አይሆንም ሲሉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ የሃንጋሪ ህዝቦች የተለየ አስተሳሰብ ነው ያላቸው የሚሉት ሚኒስትሩ "ቁጥር አንፈልግም፤ የምንፈልገው ሀንጋሪያዊያን ህፃናትን ነው" ብለዋል።

«የወሊድ መቆጣጠሪያን ወዲያ በሉት»፦ ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ

ቢሆንም ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ኦርባን ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት መንግሥት የሚያወጣቸውን አዳዲስ ህጎች በመቃወም በቡዳፔስት ህዝባዊ ተቃውሞ ተደርጎ ነበር።

ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችም በሚኒስትሩ ቢሮ አቅራቢያ በመሰባሰብ እንዲሁም ሌሎች በዳንዩብ ወንዝ ላይ የተገነባውንና በአገሪቱ ትልቅ የሚባለውን ድልድይ በመዝጋት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የውልደት መጠንን ለመጨመር የሚያስችል ሰባት የእቅድ ዝርዝሮችን አንስተው ነበር።ከእነዚህም መካከል

• በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት 21 ሺህ የሚሆኑ የህፃናት ማቆያ ቦታዎችን ማዘጋጀት

• ለአገሪቱ የጤና ክብካቤ የሚውል ተጨማሪ 2.5 ቢሊየን ዶላር ማዋል

• ሰባት የተሳፋሪዎች ወንበር ያለው ተሽከርካሪ ለመግዛት መንግስት ድጋፍ ማድረግ የሚሉትን ነጥቦች የዘረዘሩ ሲሆን ንግግራቸውንም "ረጂም እድሜ ለሀንጋሪና ለህዝቦቿ" ሲሉ ተደምጠዋል።

መቀመጫቸውን ለማስተለቅ የሚታትሩ ሴቶች እየሞቱ ነው

አንዲት ሀንጋሪያዊት ሴት በሕይወት ዘመኗ የውልደት መጠኗ በአማካይ 1.45 ሲሆን ይህም የአውሮፓ ህብረት ከተቀመጠው አማካይ የውልደት መጠን 1.58 ያነሰ ነው።

ፈረንሳይ ከአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ከፍተኛ የውልደት መጠን ያላት ሲሆን በአማካይ 1.96 ነው፤ በተቃራኒው ስፔን 1.33 አሃዝ በዝቅተኛ ደረጃ ተመዝግባለች።

አፍሪካዊቷ ኒጀር ደግሞ በዓለማችን ከፍተኛ የውልደት መጠን ያለባት አገር ተደርጋ ተመዝግባለች ፤ ይህም አንዲት እናት በአማካይ 7.24 ልጆች ሊኖሯት ይችላሉ ማለት ነው።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ