ጃንሆይና ራስ ተፈሪያን

የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ሐውልት

ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ጉልህ ሚና ከነበራቸው መሪዎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱት የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የመታስቢያ ሃውልት በአፍሪካ ሕብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተመርቆ ይፋ ሆኗል።

አፄ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ጉልህ ሚና ከመጫወታቸውም በላይ 1955 ዓ.ም የተካሄደው የህብረቱ የመጀመሪያው ስብሰባ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ከፍተኛ ጥረት አድረገዋል። ምንም እንኳ በ1994 ላይ የአፍሪካ እንድነት ድርጅት ወደ የአፍሪካ ህብረት የተቀየረ ቢሆንም የአንድነት ድርጅቱን በማቋቋም ላበረከቱት ሚና ሃውልቱ እንዲቆምላቸው ሆኗል።

ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ

የጌታቸው ረዳ ዕይታ፤ ስለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

ጤፏን ለማስመለስ እየተውተረተረች ያለችው ኢትዮጵያ

አፄ ኃይለ ሥላሴ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቋቋም ጋር ብቻ ሳይሆን ከራስተፈረያን ጋር ተያይዞ ስማቸው ይነሳል። አጼ ኃይለ ሥላሴ በሌላኛው የዓለም ክፍል በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ ይህን ያክል ተቀባይነት ያላቸው ለምን ይሆን? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው።

የአፄ ኃይለ ሥላሴ ንግስናን እና የጥቁሮች የመብት ተሟጋች የነበረውን የጃማይካዊውን ማርከስ ጋርቬይ ትንቢት የሚያገናኙት ብዙዎች ናቸው።

ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ንግስናን 10 ዓመታት በፊት ጃማይካዊው የመብት ተሟጋች ማርከስ ጋርቬይ ተከታዮቹን ''ወደ አፍሪካ ተመልከቱ፤ ጥቁር ንጉስ ይነግሳል፤ የመሰጠት ዓመትም ይመጣል'' ሲል ነገራቸው።

Image copyright AFP

ከትንቢቱ 10 ዓመታት በኋላ ራስ ተፈሪ መኮንን የተሰኙ በኢትዮጵያ ሲነግሱ በርካቶች ትንቢቱ እውነት የመሆኑ ምልክት ነው አሉ።

ከ10ሺህ ኪ.ሜ በላይ ርቀው የሚገኙት ሰዎች፤ አፄ ኃይለ ስላሴን እንደ ፈጣሪ ኢትዮጵያንም የቃል-ኪዳኗ ምድር አድርገው ወሰዱ።

አፄ ኃይለ ስላሴ 1950ዎቹ መጀመሪያ ላይ ጃማይካን ጎብኝተው ነበር። በጉብኝታቸው ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ጃማይካውያን የደመቀ አቀባበል አድረገውላቸዋል።

"ኮሜዲ፣የጤፍ ዝናብ ነው" ቤቲ ዋኖስ

ጣልያን በተሸነፈችበት አድዋ ቆንስላዋን ለምን ከፈተች?

ከ1940ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ በርካታ ራስተፈሪያኖች ወደ ኢትዮጵያ መትመም ጀምረው ነበር። የጃንሆይ ጉብኝትን ተከትሎም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ጃማይካውያን ቁጥር ጨምሮ ነበር።

አፄ ኃይለ ስላሴ በ1967 ዓ.ም ህይወታቸው ሲያልፍ በተከታዮቻቸው ዘንድ ግራ መጋባት ተፈጥሮ ነበር። ከዚያም ያረፈው የምድር አካላቸው ነው ተብሎ በተከታዮቻቸው ዘንድ ታመነ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ''ወደ አፍሪካ ተመልከቱ፤ ጥቁር ንጉስ ይነግሳል፤ የመሰጠት ዓመትም ይመጣል'' ብሎ የተንበየው ጋርቬይ የአፄ ኃይለ ስላሴ ተቺ ነበር።

አሁንም ቢሆን አፄ ኃይለ ስላሴ ለኢትዮጵያ መልካም ነበሩ፤ አይደለም ኢትዮጵያን በድለዋል የሚሉ የሃሳብ ክፍፍሎች እንዳሉ ናቸው።

የሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት በኢትዮጵያ 1966 ተከስቶ ለሁለት ዓመታት በዘለቀው እና ወደ 200ሺህ ህዝብ ላለቀበት ረሃብ አፄ ኃይለ ስላሴ ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት አላሳዩም ሲል ይወቅሳቸዋል።

በስልጣን ዘመናቸውም በተቀናቃኞቻቸው ላይ በሚወስዷቸው የማያዳግም እርምጃ ይታወቃሉ።

የጣሊያን ወረራ ተከትሎ አፄ ኃይለ ስላሴ ሃገር ጥለው መሸሻቸው በማርከስ ጋርቬይ ጭምር አስወቅሷቸዋል።

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ አፄ ኃይለ ስላሴ ከቀድሞ የጋና ፕሬዚዳንት ኩዋሜ ኑኩሩማ የአፍሪካ እንድነት ድርጅት በተቋቋመት ወቅት አዲስ አበባ ላይ።

መምህሩ ዮሃንስ ወልደማሪያም (ዶ/ር) አፄ ኃይለ ስላሴ እንደ አምባገነን ነው መታሰብ ያለባቸው ሲሉ ይሞግታሉ። አፄ ኃይለ ስላሴ አርቅቀው ያጸደቁት ሕገ-መንግሥት ስልጣኑን በሙሉ በእሳቸው ቁጥጥር ሥር ያደረገ መሆኑ ይወሳል።

በተቃራኒው የጃንሆይ ደጋፊዎች አፄ ኃይለ ስላሴ ድንቅ መሪ መሆናቸውን እና ኢትዮጵያን ለማዘመን የታተሩ መሪ መሆናቸውን ይገልጻሉ።

ኢትዮጵያ በጣሊያን ከተወረረች በኋላ በሊግ ኦፍ ኔሽን ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ያቀረቡት አቤቱታ አሁንም ድረስ ይታሰባል።

በአዲስ አበባ የቆመውም ሃውልት በርካቶችን አፄ ኃይለ ስላሴ ለፓን አፍሪካኒዝም ትብብር ለማጠንከር የነበራቸውን ህልም ለተቀረው የአህጉሪቱ ህዝብ አስታዋሽ ሆኖ ይቆያል የሚል እምነት አሳድሮባቸዋል።

ተያያዥ ርዕሶች