የዩክሬን ባለሥልጣናት በአሲድ ጥቃት ግድያ ክስ ተመሠረተባቸው

የዩክሬን ባለስልጣናት በአሲድ ጥቃት ክስ ተመሰረተባቸው Image copyright AFP

የዩክሬን አቃቤ ሕግ ታዋቂ የፀረ-ሙስና ተሟጋችን በኢሰድ ጥቃት ለሞት ዳርገዋል ያላቸው ባለስልጣናት ላይ ክስ መሠረተ።

የ33 ዓመቷ ካትሪያና ሃንድዝዩክ ሕልፈት ዩክሬናውያንን እጅጉን ያስደነገጠ ነበር። የአሲድ ጥቃቱ ካደረሰባት ቃጠሎ በኋላ በሕክምና ስትረዳ ብትቆይም ከሦስት ወራት በፊት ሕይወቷ አልፏል። የፀረ-ሙሰና ተሟጋቿን ሕይወት ለማትረፍ ከ10 በላይ የቀዶ ሕክምና ተደርጎላት ነበር።

"ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ

ክስ ከተመሠረተባቸው ባለሥልጣናት መካከል የአንድ ግዛት ምክር ቤት ኃላፊ ግድያውን በማቀነባበር ተጠያቂ ሆነዋል። ከእኚህ ግለሰብ በተጨማሪ ሌሎች 5 ሰዎች ከግድያው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ይገኛሉ።

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በፀረ-ሙስና አቀንቃኟ ላይ የደረሰው ጥቃት በርካቶችን ያስቆጣ ሆኗል።

የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ ወደ 50 በሚጠጉ የፀረ-ሙስና አቀንቃኞች ላይ የተለያየ መልክ ያላቸው ጥቃቶች ተሰንዝረዋል።

አሲድን እንደ መሳሪያ

የሶስት ዓመት ጨቅላን በአሲድ ያጠቁ ታሰሩ

ግድያውን በማቀነባበር የተከሰሱት ግለሰብ ቤት በፖሊስ የተበረበረ ሲሆን የተከሳሹ ጠበቃ ግን በደንበኛዬ ላይ የተገኘ ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም ይላሉ።

ክስ የተመሠረተባቸው የምክር ቤት ኃላፊም ሟቿን እንደማያውቋት እና ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌላቸው በመናገር ለምርመራው ተባባሪ መሆናቸውን ጨምረው ተናግረዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ