ለ10 ዓመታት እጆቹን ያልታጠበው የቴሌቪዥን አቅራቢ

ፎክስ እና ጓደኞቹ የተሰኘው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ ፒት ሄግሴት Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ እጆቼን አለመታጠቤ ክትባት እንደመወጋት ያህል ነው -ፒት ሄግሴት

ፎክስ እና ጓደኞቹ የተሰኘው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ የሆነው ፒት ሄግሴት በቀጥታ ሥርጭት ወቅት "ጀርም እውነት ስላልሆነ" አጆቹን ለ10 ዓመታት እንዳልታጠበ አሳውቋል።

በሚያቀርበው ፕሮግራም ፒት አነዚህ ጥቃቅን ፍጥረታት (ጀርሞች) በዓይን ስለማይታዩ የሉም ብሎ ማመኑን ተናግሯል።

"እራሴን ነው የምከትበው" በማለት የሃርቫርድና የፕሪንስተን ምሩቁ ተናግሯል።

ደስታን አጥብቀን ስለፈለግን ለምን አናገኘውም?

መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች

ይህንም ኑዛዜ ያስከተለው ኤድ ሄንሪ እና ጄደዳያ ቢላ የተሰኙት ባልደረቦቹ ያደረ ፒዛ እበላለሁ ሲላቸው ይህም ይግረማችሁ ብሎ ነበር።

"በ2019 ለእራሴ ቃል የገባሁት ከካሜራው ጀርባ የምናገራቸውን ነገሮች በአየር ላይ መናገር ነው" ብሏል።

በማህበራዊ ገፆች ላይ አንዳንዶች ሲያንቋሽሹት ሌሎች ደግሞ ሲያበረታቱት ታይቷል።

ፒት ሄግሴት ቀጥሎም ዩኤስኤ ቱዴይ ለተሰኘው መገናኛ ብዙሃን ንግግሩ ቀልድ መሆኑን ተናግሯል።

"ያለንበት ማህበረሰብ በኪሱ ፒዩሬል (አጅ ማፅጃ ኬሚካል/ሳኒታይዘር) ይዞ የሚዞር ነው። አጆቻቸውን በቀን 19 ሺህ ጊዜ ያፀዱበታል፤ ሕይወታቸውን ያተርፈው ይመስል" ብሏል።

"እራሴን እጠብቃለሁ ሆኖም ግን ሁሉም ነገር አያስጨንቀኝም"።

የሕዝቡን ምላሽ በተመለከተ ደግሞ፤ ሰው 'ጭንቅላቱ እስኪፈነዳ' ሁሉን ነገር 'በግርድፉ' እንዴት እንደሚረዳው ይገርመኛል ብሏል።

በጥዋት ከእንቅልፍ መነሳት ውጤታማ ያደርጋል?

በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው?

የአሜሪካው ጤና ጥበቃ እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ ጀርሞችን በማስወገድ ከተለያዩ በሽታዎች እንደሚጠብቅና ከዚያም አልፎ ጀርሞች ወደ ሌሎች ሰዎች አንዳያተላለፉ ይረዳል ይላል።

የአሜሪካው ባዮቴክኖሎጂ መረጃ ብሔራዊ ማዕከል ባሳተመው ጥናት መሠረት አንድ ግራም የሰው ሰገራ እስከ ሦስት ትሪሊየን ጀርሞችን እንደሚይዝ ይናገራል።

ባልታጠቡ እጆች ሊሰራጩ ከሚችሉት ባክቴሪያዎች መካከል ሳልሞኔላና ኢኮላይ ይገኙበታል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እራሳቸው በተለያዩ ቃለ መጠይቆች ላይ ጀርሞፎብያ (የጀርም ፍራቻ) እንዳለባቸው ተናግረዋል።

እ.አ.አ በ1997 በታተመው 'አርት ኦፍ ዘ ካምባክ' በተሰኘው መጽሐፋቸው ፕሬዚዳንት ትራምፕ " የአሜሪካ ማህበረሰብ ዋኘኛው ችግር እጅ መጨባበጥ ነው። በተለይ የአንድ ሰው ታዋቂነት እየጨመረ በመጣ ቁጥር ይህ ልማድ እየተባባሰ የሚመጣ ይመስላል።"

የአከርካሪ ቀዶ ጥገና ባልተወለዱ ልጆች ላይ

ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና

"ለእጅ ንፅህና ያለኝ ቦታ በጣም ከፍተኛ ነው። እጆቼን በደንብ ስታጠብ ሰላም የሰማኛልና በተቻለኝ መጠን በተደጋጋሚ ለመታጠብ እሞክራለሁ።"

ስቲቭ የሚባል የቢቢሲ አንባቢ አስተያየቱን እንዲህ በማለት አካፍሎናል "ይህን መቼም እላለሁ ብዬ አላውቅም ግን ከዶናልድ ትራምፕ ጋር እስማማለሁ።"

አክሎም "የሃርቫርድና የፕሪንስተን ምሩቅ መሆን ትንሽም ቢሆን እውቀት ይጨምራል ብዬ አስብ ነበር፤ ለካ ትርጉም የለሽ ነው።"

የአንድ ሰው ስለንፅህና ብዙ መጨነቅ ጤናማ አይደለም ምክንያቱም ተፈጥሯዊውን የመከላከያ አቅማችንን ያዳክማል ያሉም አሉ።

ሌላ ኬቪን ኩክ የተሰኘው የቢቢሲ አንባቢ እንደሚለው "ለ10 ዓመታት እጅን አለመታጠብ ለሌሎች ሰዎች ጤና ደንታ እንደሌለን የሚያሳይ ነው" ብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች