የአሜሪካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን በከፊል ከመዘጋት የሚታደግ ስምምነት ተደረሰ

ስደተኞች በድንበር አካባቢ Image copyright Getty Images

የአሜሪካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን በከፊል ከመዘጋት ለመታደግ ሲባል ለድንበር ጥበቃ በሚያስፈልገው ገንዘብ ዙሪያ ዲሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደረሱ።

ሕግ አውጪዎቹ እንዳሉት ስምምነቱ የተደረሰው ዋሽንግተን ውስጥ በተካሄደ ዝግ ስብሰባ ነው።

ስለስምምነቱ ዝርዝር የወጣ መረጃ የለም። በጉዳዩ ላይ ሲደረግ የነበረው ንግግር ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን ማሰርና ፕሬዝዳንት ትራምፕ የድንበር አጥር ለመሥራት በሚያስፈልጋቸው ገንዘብ ምክንያት ተቋርጦ ነበር።

ትራምፕ ስለስደተኞች በተናገሩት ወቀሳ ደረሰባቸው

"ለወጣቶች አስፈሪ ጊዜ ነው" ትራምፕ

የጌታቸው ረዳ ዕይታ፤ ስለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስምምነቱን እንደሚደግፉት ያሉት ነገር ባይኖርም፤ በየትኛውም መንገድ በድንበራቸው ላይ ለመገንባት ያሰቡት አጥር ጉዳይ ተግባራዊ እንዳይሆን የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

ቴክሳስ ውስጥ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር ስምምነቱን በዝርዝር ለመመልከት ጊዜ እንዳልነበራቸው፤ ነገር ግን "አደገኛ ወንጀለኞች በጅምላ እንዲለቀቁ የሚያደርግ ስምምነትን ፈጽሞ አልፈርምም" ሲሉ በአጽንዖት ተናግረዋል።

አንዳንድ የፌደራል መንግሥቱ መሥሪያ ቤቶች ያላቸው በጀት ከማለቁ በፊት ስምምነቱ አርብ ዕለት መጽደቅ ይኖርበታል ተብሏል።

ዲሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች ለበረካታ ሰዓታት ተደራድረው ከስምምነት የደረሱት ለድንበር ጥበቃ ትራምፕ ከጠየቁት ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ ያለውን የፈቀደ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሊታሰሩ የሚችሉ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን ቁጥር መቀመነስንም ያካትታል።

. በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ

አሜሪካዊው ወታደር የወንድ መራቢያ አካል ንቅለ-ተከላ ተደረገለት

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ