ናይጀሪያዊቷ ከመንግሥት ጋር በመተባበር ባለቤቴን ገድሏል በማለት ሼል ኩባንያን ከሰሰች

ኢሽተር ኪዮቤል በፍርድ ቤት Image copyright Getty Images

በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1995 ከተገደሉት ናይጀሪያዊያን ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች መካከል የአንዱ ባለቤት ግድያው የማይሽር ጠባሳን ትቶ እንዳለፈና በድህነት እንድትማቅቅ እንዳደረጋት ገልፃለች።

ኢሽተር ኪዮቤል የተባለችው ይህች ግለሰብ ሄግ በሚገኘው ፍርድ ቤት ለምስክርነት የቀረበች ሲሆን፤ ሼል ላጠፋው ጥፋት ካሳን እንዲሁም ይቅርታን እንደምትሻ ገልፃለች።

በናይጀሪያ የነዳጅ ክምችት የተትረፈረፈ ኃብት አላት በምትባለው ኦጎኒ ግዛት ላይ ሼል እያደረሰ ያለውን ብክለትና የሰዎች ጉዳት በመቃወም ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመፅና እንዲሁም ተቃውሞዎች መነሳት ጀመሩ።

ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ

ይህንንም ተከትሎ ተቃውሞውን ይመራሉ ያላቸውን ተሟጋቾች በአውሮፓውያኑ 1995 የናይጀሪያ መንግሥት አንቆ ገደላቸው።

ምንም እንኳን ሼል ቢያስተባብልም በዚህም ግድያ ሼል ተባብሯል በማለት ይወነጀላል።

ጤፏን ለማስመለስ እየተውተረተረች ያለችው ኢትዮጵያ

ተቃውሞዎቹ በዚያን ጊዜ ለነበረው ወታደራዊ አመራር ጄኔራል ሳኒ አባቻና ሼል እንደ ከፍተኛ ስጋት ታይተው ነበር።

በወቅቱ እንቅስቃሴውን ይመሩ ከነበሩት ዘጠኙ አቀንቃኞች አንዱ የሆነው ኬን ሳሮ ዊዋ በወታደራዊ መንግሥቱ ታንቆ ከተገደሉት አንዱ ነው።

ግድያቸው በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞን ያስነሳ ሲሆን ናይጀሪያንም ከኮመንዌልዝ አባልነቷ ለሶስት አመት አሳግዷታል።

ባሎቻቸው ከተገደሉባቸው መካከል ሁለቱ በፍርድ ቤቱ የተገኙ ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ ቪዛ በመከልከላቸው ምክንያት አልተገኙም።

ከሁለት አስርት አመታት በፊት ባሏ የተገደለባት ኢሽተር በእንባ እንደተጥለቀለቀች የቢቢሲዋ ዘጋቢ አና ሆሊጋን ከፍርድ ቤት ዘግባለች።

እንባዋን እየጠረገች፣ በተቆራረጠና ሳግ በተሞላው ድምፅ ባለቤቷ ባሪኔም ኪዮቤል "ቀና ልብ " ያለው ሰው ነበር ብላለች።

በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው?

ከዚህ በተጨማሪም በተፃፈ መግለጫዋም "ጥሩ ባለቤቴን እንዲሁም ጓደኛየን አጣሁ" በማለት ተናግራለች።

"በህይወቴ እንደ እንቁ የማየውን ነገር ሼል ቀማኝ፤ ሼል ባሏ የሞተባት ደሃ አደረገኝ። ሼል ስደተኛ እንድሆንና በከፍተኛ ድህነት ውስጥ እንድኖር አድርጎኛል። " ብለላች

በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ጥገኝነት ጠይቃ ዜግነቷን ያገኘችው ይህች ግለሰብ ጨምራም "የናይጀሪያ መንግሥትና ሼል ተባብረው ባሌን እንዲሁም አጋሮቹን ኬኑሌ ቱዋ ሳሮ ዊዋ፣ ጆን ክፑይነን፣ ባሪበር ቤራ፣ ፖል ሌቩላ፣ ኖርድኡ ኢያዎና የሌሎቹንም ህይወት ነጥቆናል"

Image copyright Tim Lambon/Greenpeace
አጭር የምስል መግለጫ ሼልንና የናይጀሪያ መንግሥትን በመሞገት የሚታወቀው ኬን ሳሮ ዊዋ

"ባሌና ሌሎቹ የተገደሉትም አጋሮቹ ስቃይና እንግልት አሁንም ትናንት የተፈፀመ ይመስል ትዝ ይለኛል። አሁንም ቢሆን ህመሜን ቀለል ባያደርገውም ፍትህን እፈልጋለሁ" ብላለች።