"ኦሮሞነትን ከፍ አድርጌ ኢትዮጵያዊነትን የማሳንስ አይደለሁም" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ፖለቲከኛው ቡልቻ ደመቅሳ በመንግሥት ስራ መሳተፍ የጀመሩት በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ሲሆን በወቅቱም የገንዘብ ሚኒስቴር ም/ሚኒስትር በመሆን ለአስር አመት ያህልም አገልግለዋል።

አሜሪካ ሀገር በሚገኝ ሴርኪኡዝ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የተማሩት አቶ ቡልቻ ለአስር አመት ካገለገሉ በኋላ ተመልሰውም ወደ ውጭ ኃገር ሄዱ።

አሜሪካ በነበሩበትም ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ይሰሩ የነበሩ ሲሆን ኢትዮጵያም መጥተው ቀዳሚ የግል ባንኮች አንዱ ከሆኑት አዋሽ ባንክን አቋቁመዋል። የባንኩም ዋና አላማ ለኦሮሞ አርሶ አደር ብድር ለማመቻቸት እንደሆነ አቶ ቡልቻ ይናገራሉ።

ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ

ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ቡልቻ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

የፓርላም አባል ነበሩ። ስለ ፖርላማው ምን ሀሳብ አለዎት?

የኢትዮጵያን ፓርላማን ለማየት እንጅ የእዉነት ነው ብየ አይደለም የገባሁት። ምክንያቱም እንደሌሎች ሃገራት ህዝቦች በቁጥራቸዉ መጠን አልነበረም የሚወከሉት።ለምሳሌ እኔ ከወለጋ ነበር የተመረጥሁት። እዉነት ቢሆን ኖሮ እኔ ከተመረጥኩበት ወረዳ ሶስት ሰዎች ይወከሉ ነበር።ማን የት እንደሚመረጥ ደግሞ ኢህአዴግ ይወስን ነበር። ስለዚህ ለመረጠኝ ህዝብ ድምጽ መሆን ከንቱ ምኞት ሆኖ ቀረ።

ጤፏን ለማስመለስ እየተውተረተረች ያለችው ኢትዮጵያ

ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያን ችግር ማዉራት ብፈልግም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ግን ስለመጣሁበት ቀበሌና እንድናገር ስለተገደድኩ በወከልኩት አካባቢ ታጥሬ ነበር።

እንደ አንድ የኢትዮጵያ ዜግነቴ ስለመላዉ ኢትዮጵያ እንጅ ስለቦጅድርማጅ እና ላሎ አሰብ ብቻ ማዉራት አለብኝ እንዴ?

ለምሳሌ ያህል ኢትዮጵያ ሶማሊያ ላይ ለምን ጦርንነት ታዉጃለች ብየ ስጠይቅ ምን አገባህ የሚል መልስ ተሰጥቶኛል። ለዚህም ነዉ የኢትዮጵያ ፓርላማ እንደሌሎች አይደለም የምለው። እንደሚታወቀው ፓርላማዉ የነሱ ብቻ ነበር። ከኢህአዴግ ሀሳብ ውጭ የሚናገሩ ካሉ በጠላትነት ይታዩ ነበር።

በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው?

በጊዜዉ ፓርላማዉ እንጅ የዴሞክራሲ ፅንሰ ሃሳብ አልነበረም። ፍላጎታቸው በፓርላማው ውስጥ የነሱን ሃሳብ የሚያንፀባርቅና ተመሳሳይ ንግግሮችን የሚያደርግ ሰው ነው የሚፈለገው። ለኔ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ይፈልጋል የሚለውን ነው ቅድሚያ የምሰጠው። ለምሳሌም ያህል ስለ ሀገሪቷ የምጣኔ ሃብት፣ የዉጭ ጉዳይና ግብር ስለመሳሰሉ ጉዳዮች ጥያቄ አነሳ ነበር። በተለይም ትምህርት ቤቶች ሊስፋፉ እንደሚገቡ አፅንኦት ሰጥቼ እናገር ነበር። በኋላም ላይ ትምህርት ቤቶችን አስፋፍተዋል ለዚህም ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነዉ። ባጠቃላይ ግን ስናየው ያ መንግስት ሀገር የሚያሳድግ ሳይሆን የሚያቀጭጭ ነበር።

ለዉጡን እንዴት ያዩታል?

ይሄ ለዉጥ በዚህ አጭር ጊዜ ይመጣል ብየ አላሰብኩም ነበር። ምክንያቱም በተደጋጋሚ የኢህአዴግ መንግሥት የሚመጡትን 25 አመታት አስተዳድራለሁ ይል ስለነበር። አምላክ በዚች አጭር ጊዜ ይሄን ብርሃን ያሳየናል ብየ አላሰብኩም። ወደዚህ ሀገር ከተመለስኩ በኋላ ብዙ አዲስ ነገሮችን አይቻለሁ። ለምሳሌ አሁን ቃለመጠይቁን በራሴ ቋንቋ ነዉ እየሰጠሁህ ያለሂሁት።ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት እድል አግኝተን አናዉቅም ነበር። ከ20 አመት በፊት ለቢቢሲ ሁለት ደብዳቤ ጽፌ ነበር። የኦሮሞ ህዝብ ብዙ ቁጥር ስላለዉ በራሳችን ቋንቋ ሚዲያ እንዲከፍትልን ነበር።አሁን ይሄዉ ቢቢሲ በራሳችን ቋንቋ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።ለለዚህም ቢቢሲን አመሰግናለሁ።

ኢትዮጵያዊነትን እና ኦሮሞነትን እንዴት ያዩታል?

ከኦሮሞ ዉጭ ኢትዮጵያ የለችም። ይሄ ብቻም አይደለም። አማራም ጉራጌም እና ሌሎች ብሄሮችም ለኢትዮጵያ ያስፈልጓታል።እኔ ኦሮሞነትን ከፍ አድርጌ ኢትዮጵያዊነትን የማሳንስ አይደለሁም።

ኦሮሞን በስፋትና በብዛት ካየን የኢትዮጵያ የበኩር ልጅ ነዉ። የኦሮሞ ህዝብ ለዚች ሃገር እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነዉ።አዲስ አበባ ዉስጥ የሚሰሩ ሚዲያዎች አብዛኞች በአማርኛ ነዉ አገልግሎት የሚሰጡት። የኦሮምኛ ግን ትንሽ ናቸዉ። እና በቁጥርና በምጣኔ ሃብት በልጠን ሳለ እንዳናድግ ተደርገናል።ኦሮሞን እንደበፊቱ መጨቆንና እንዳያድግ ማድረግ ፈጽሞ አይቻልም። በአጠቃላይ አሁን የመጣዉ ለዉጥ ተስፋ ሰጭ ነዉ። ሆኖም ግን ይህንን መንግሥት ካቅም በላይ መጫን የለብንም። መንግሥት መፈጸም ያለበትን በራሱ መንገድ እንዲፈጽም ካልፈቀድንለት በስተቀር ከተጫንነዉ ሊወድቅ ይችላል።ውድቀቱ ደግሞ እኛን ይጎዳናል እንጅ አይጠቅመንም። አሁን ተስፋ እንጅ ያገኘነዉ ነገር የለም። ሰባት ስምንት አመታት ተስፋ ብቻ ከሆነ ግን ህዝቡ ተሰላችቶ ጦርነት ሊያስነሳ ይችላል።

ፓርቲዎን እንዴት መሰረቱት? አላማውስ ምን ነበር?

የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ዋና አላማዉ ኦሮሞ እንደ ህዝብ ያጣቸዉንና ሊያገኛቸው ይገባል ብለን የምናስባቸውን መብቶች ለማስገኘት የተመሰረተ ፓርቲ ነው። በወቅቱ አብዛኛዉ ኦሮሞ በሩን ዘግቶ ነበር የሚቀመጠዉ።ስለዚህ እኛም 'ኦሮሞ አለ' ለማለት ነዉ። አሁንም እንደነ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣በቀለ ገረባ እና አቶ ሙላቱ ገመቹ በፓርቲያቸው ጥሩ እየሰሩ ነዉ።

መጭዉ ምርጫ ላይ ይሳተፋሉ?

አዎ እሳተፋለሁ።የምወዳደረዉ በፓርቲ ደረጃ ሳይሆን በግሌ ነዉ። በግሌ ፓርላማ ገብቼ የምናገረዉ አለኝ።የሀገርን ጉዳይ የሚያሳድግና የሚያቀጭጨዉ ፓርላማ ነዉ። ስለዚህ ፓርላማ ገብቼ ብዙ ጉዳዮች ላይ የግሌን ሃሳብ መስጠት እፈልጋለሁ።

ተያያዥ ርዕሶች