ኬንያዋ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሞታ ተገኘች

ካሮሊን ምዋታ

በባለፈው ሳምንት ረቡዕ ጠፍታ የነበረችው ኬንያዊቷ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ካሮሊን ምዋታ ሞታ ተገኘች።

በመዲናዋ ናይሮቢ ፖሊስ የሚፈፅመውን ግድያዎችን የመመዝገብና ለህዝብ ይፋ የማድረግ ስራ ትሰራ እንደነበር ተገልጿል።

የአስከሬን ምርመራዋ ለሚቀጥለው ሰኞ የተላለፈ ሲሆን ለዚህም እንደ ምክንያትነት የተሰጠው ዋናው የአስከሬን መርማሪው ጆሀንሰን ኦዱር መገኘት ባለመቻላቸው እንደሆነ ሲትዝን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ናይጀሪያዊቷ ባለቤቴን ገድሏል በማለት ሼል ኩባንያን ከሰሰች

በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው?

ሌላኛው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሁሴን ካሊድ በዛሬው ዕለት የአስከሬን ምርመራ ባለመደረጉ እንዳሳዘነው መግለፁን የሀገሪቱ ጋዜጣ ዘ ስታር ዘግቧል።

በጠፋችበት ወቅት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምነስቲ በህይወት የመገኘቷ ነገር እንደሚያሳስበው በትዊተር ገፁ አስፍሮ ነበር።

"ኦሮሞነትን ከፍ አድርጌ ኢትዮጵያዊነትን የማሳንስ አይደለሁም" አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ነገር ግን ፖሊስ እንደገለፀው አደገኛ በሆነ ውርጃ ምክንያት መሞቷንና ከድርጊቱም ጋር ተያይዞ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል።