በፓፑዋ ኒው ጊኒ ከዓለም አቀፍ ስበሰባ በኋላ 300 መኪኖች ጠፉ

ጣሊያን ሠራሽ ማሴራቲስ ቅንጡ መኪኖች ተገኝተዋል Image copyright AirBridgeCargo
አጭር የምስል መግለጫ ጣሊያን ሠራሽ ማሴራቲስ ቅንጡ መኪኖች ተገኝተዋል

ለእስያ-ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ዓለም አቀፍ ስብሰባ የፓፑዋ ኒው ጊኒ መንግሥት የተዋሳቸው 300 መኪኖች እምጥ ይግቡ ስምጥ ባለመታወቁ የፓፑዋ ኒው ጊኒ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ አውጥቷል።

በድህነት አረንቋ ውስጥ ወደምትገኘው ፖፑዋ ኒው ጊኒ የሚሄዱ መሪዎችን በቅንጡ መኪኖች ለማንሸራሸር ታስቦ ነበር የሃገሪቱ መንግሥት በውሰት ወደ ሃገር ውስጥ መኪኖቹን ያስገባቸው።

ይሁን እንጂ የሃገሪቱ ፖሊስ ኮማንደር እንዳስታወቁት በስብሰባው ማግስት 284 መኪኖች መጥፋታቸው ተረጋግጧል።

የጠፉት መኪኖች ቅንጡ ላንድክሩዘር፣ ፎርድ፣ ማዝዳ እና ፓጃሮ መሆናቸውን ሱፐርኢንተንደነት ዱኒስ ኮርኮራን ተናግረዋል። መኪኖቹን ለማፈላለግ ልዩ የፖሊስ ግብረ ኃይል መቋቋሙም ተሰምቷል።

ኮማንደሩ ጥቂት ጣሊያን ሠራሽ 'ማዜራቲ' ቅንጡ መኪኖች መገኘታቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ አንዳንዶቹ መኪኖች በጥሩ ይዞታ ላይ እንደሚገኙ የተቀሩት ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አልያም በርካታ አካላቸው የተሰረቀ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።

ወንዶች አዞ ለመምሰል ቆዳቸውን የሚበሱባት ሃገር

ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች ይፋ ሆኑ

የፓፑዋ ኒው ጊኒ መሪዎች ዓለም አቀፍ ስብሰባው ኢንቨስትመንት እንደሚስብ ተስፋ አድርገው ነበር። ሆኖም ስብሰባውን ለማሰናዳት ሃገሪቱ እጅግ ብዙ ገንዘብ አፍስሳለች። ከሌሎች ሃገሮች ድጎማ ለመጠየቅም ተገዳለች።

አውስትራሊያ፣ አሜሪካና ኒው ዚላንድ የፓፑዋ ኒው ጊኒ ስብሰባ ተሳታፊዎች ደህንነት እንዲጠበቅ ልዩ ኃይል ልከዋል።

መገናኛ ብዙሃንና የመብት ተሟጋቾችም ድሃዋ ፓፑዋ ኒው ጊኒ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ማስተናገዷ ላይ ጥያቄ አንስተው ነበር። ለስብሰባው ተሳታፊዎች የተዘጋጁት መኪኖች የሃገሪቱ መንግሥት አባካኝነት መገለጫ ናቸው ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች