አፕል ሴቶችን ከመንቀሳቀስ የሚያግድ የሳዑዲ መተግበሪያ ሊመረምር ነው

መተግበሪያው ሴቶችን ተከትሎ ከጉዞ ለማገድ ይውላል Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ መተግበሪያው ሴቶችን ተከትሎ ከጉዞ ለማገድ ይውላል

ሴቶችን በመከታተል ከጉዞ ማገድ የሚያስችል የሳዑዲ አረቢያ መተግበሪያ ላይ ምርመራ ሊያካሂድ መሆኑን አፕል አስታወቀ።

የአፕል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቲም ኩክ፤ 'አብሽር' ስለተባለው መተግበሪያ የሚያውቁት ነገር እንዳልነበረ ከኤንፒአር ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ አሳውቀዋል። መተግበሪያው ላይ ምርመራ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች መተግበሪያውን ተቃውመውታል።

ሳዑዲ ለሮቦት ዜግነት ሰጠች

ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች

ሳዑዲ የፀረ-ሙስና ዘመቻዬን አጠናቀቅኩ አለች

የአሜሪካው ሴናተር ሮን ዋይደን፤ አፕልና ጉግል መተግበሪያውን፤ ከመተግበሪያ መደብራቸው (ስቶር) እንዲሰርዙ ጠይቀዋል።

ሴቶች ከሳዑዲ አረቢያ ለመውጣት ከአባታቸው፣ ከባለቤታቸው ወይም ሌላ የቅርብ ወንድ (ጋርዲያን) ፍቃድ ማግኘት አለባቸው።

አብሽር የተባለው መተግበሪያ፤ የመንጃ ፍቃድ የሚያድስ ክፍልን ጨምሮ በተለያዩ የመንግሥት ተቋሞች ጥቅም ላይ ይውላል። ሴቶች ከሀገር እንዳይወጡ የመከላከል ሂደትን ቀላል የሚያደርግ ሲሆን፤ በስልክ ላይ ተጭኖ ጥቅም ላይ ይውላል።

መተግበሪያው በሳዑዲ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ጥቅም ላይ እንዲውል ታስቦ የተሰራ ሲሆን፤ ለበርካታ ዓመታትም አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ከአንድ ሚሊዮን ጊዜ በላይም ተጭኗል።

ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

የጀማል ኻሾግጂን ግድያ ለመሸፈን 'ባለሙያዎች ተልከዋል'

ወንዶች ሚስቶቻቸውን፣ እህቶቻቸውን ወይም ሴት ልጆቻቸውን በመተግበሪያው መዝግበው ከሀገሪቱ ውጪ ከሚደረግ በረራ ያግዷቸዋል። አንዲት ሴት ከሳዑዲ ለመውጣት ብትሞክር መተግበሪያው ለወንዱ ማሳሰቢያ (ኖቲፊኬሽን) ይልካል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች "እንዲህ አይነት መተግበሪያዎች የሴቶችን መብት ይጥሳሉ" ሲሉ ኮንነዋል።

ሴናተር ሮን ዋይደን፤ "የሳዑዲ አገዛዝ ሴቶችን መጨቆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ሆኖም የአሜሪካ ተቋሞች የሳዑዲን ጭቆና መደገፍ የለባቸውም" ብለዋል።

አንዳንድ ሴቶች ወንዶች ስልክ ላይ ያለውን መተግበሪያ አሰራር (ሴቲንግ) በመቀየር መጓጓዝ እንዲችሉ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

በጉዳዩ ላይ ቢቢሲ ከጉግል ምላሽ ቢጠይቅም ለማግኘት አልቻለም።