በምዕራብ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች የአስቸኳይ ጊዜ ወይስ የመሣሪያ እገዳ?

ሰዎች የጦርመሣሪያ እና ዱላ ይዘው ሲጨፍሩ Image copyright Eric Lafforgue/Art in All of Us

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምዕራባዊና ማዕከላዊ ጎንደር በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለውን አለመረጋጋትና የህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ተገለጸ።

የሃገር መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እሁድ ዕለት እንዳስታወቁት ከጎንደር፣ መተማ፣ ሁመራ መስመርና በጎንደር ከተማ ውስጥ ግለሰቦች የጦር መሳሪያ ታጥቀው እንዳይንቀሳቀሱ ገደብ መጣሉንና ይህንን ትላልፈው በተገኙ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳትን ያስከተሉ ግጭቶች መከሰታቸውና ግጭቱን ለመቆጣጠር ከክልሉ አቅም በላይ በመሆኑ እና የጸጥታው ችግር ከመሻሻል ይልቅ በየጊዜው እየተባባሰ በመምጣቱ ተጨማሪ ኃይል አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነ በመግለጫው ተመልክቷል።በዚህም ምክንያት የአማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግሥት ለፌዴራል መንግሥት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግና ሠላም ለማስከበር ከእሁድ የካቲት 10/2011 ዓ.ም ጀምሮ በተጠቅሱት አካባቢዎች ላይ እንደተሰማራ ተነግሯል።

ደቡብ ጎንደር መካነ እየሱስ ውስጥ ምን ተፈጠረ?

የጦር መሳሪያዎቹ ምንጫቸው የት ነው?የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ለቢቢሲ እንደተናገሩት ይህን እርምጃ መውሰድ "መንግዶች እየተዘጉ ነው፣ ሰዎች እየተፈናቀሉ፣ ዝርፊያ እየተፈጸመ፣ ሰዎች እየተገደሉ እና ንብረት እየተዘረፈ በመሆኑና የመንግሥት አገልግሎት መስጠት ባለመቻሉ ሰላም የማስከበር ሥራ በፍጥነት ለማከናወን ነው" ብለዋል።

ኮሚሽነሩ ጨምረውም እርምጃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አለመሆኑን አመልክተው፤ ክልከላው ለፀጥታ ሥራ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል የተተደረገ እንጂ የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት በአዋጅ የመገደብ እርምጃ አይደለም ብለዋል።

"ከመቼውም ጊዜ በላይ የፀጥታ ኃይሉ ከፍትኛ ስምሪት የሚያደርግበት በመሆኑ ለዚህ የሚመች ሁኔታ ለመፍጠር እንጂ ዜጎች ህጋዊ እስከሆኑ ድረስ ከተከለከሉት አካባቢዎች ውጪ ባሉት ቦታዎች መሳሪያ ይዘው መንቀሳቀስ ይችላሉ" በማለት አብራርተዋል።

የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በተከሰተባቸው አካባቢዎች መኪና አስቁሞ ዝርፊያ፣ ግድያ፣ ሰዎችን አፍኖ የመውሰድ ወንጀል የሚፈጽሙ ቡድኖች መኖራቸውን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ተናገግረዋል።

እነ አቶ በረከት በማረሚያ ቤቱ ኢንተርኔት የለም አሉ

ኦሮምኛ ዘፋኙ ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን አጣ

"ክልከላው የሚቆየው የአካባቢውን ሰላም አስከብረን መደበኛ የልማት እንቅስቃሴ እስኪጀመር ይሆናል። የክልልና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ከሕብረተሰቡ ጋር በትብብር እየስሩ ነው ክልከላውም ይህን ስራ ለማሳለጥ ነዉ። ስለዚህ ስራችንን ስንጨርስ የሚነሳ ይሆናል" ብለዋል።የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ በአካባቢዎቹ አስተማማኝ ሰላም እስኪሰፍን ድረስ መሆኑን በማመልከት ክልከላው የሚመለከታቸውን ቦታዎች በዝርዝር አስቀምጧል።በዚህም መሠረት ከጎንደር ወደ መተማ በሚያመራው መስመር ከመንገድ ግራና ቀኝ በአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ በቡድንም ሆነ በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ ክልከላ ተጥሏል።

ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል?

በደቡብ ወሎ ሙሽራና ሚዜውን የገደለው ቦምብበጎንደር ከተማ ውስጥም በመንግሥት ከተፈቀደላቸው ፀጥታ አካላት ውጪ ማንኛውም ሰው መሣሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ እንደማይችልም በመግለጫው ላይ ተመልክቷል።

ክልከላውን በመተላለፍ በፀጥታ ማደፍረስ ተግባር ውስጥ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል እርምጃ እንደሚወሰድበትና 'ሰላም ለማስከበር' በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከፈቃድ ውጪ መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል እገዳ ተጥሏል።

ውሳኔውን ጥሰው በተገኙ ሰዎች ላይ የሚወሰድ እርምጃን በተመለከተም ኮሚሽነሩ ሲናገሩ "ክልከላው ተግባራዊ ሆኗል። የክልል እና ፌደራል መንግሥታት የሚያዉቁት ክልከላ ነው። ክልከላውን በተላለፉ ሰዎች ላይ በህግ የመጠየቅና በያዙት መሳሪያ ላይም ውሳኔ የማስወሰን ሥራ ይሰራል" ብለዋል።በተጠቀሱት አካባቢዎች የተጣለው የጦር መሳሪያ ይዞ የመንቀሳቀስ እገዳ ከእሁድ ጀምሮ ተፈጻሚ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ገልጸው ክልከላውን ተላለፈው በሚገኙ አካላት ላይ የፀጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ መታዘዛቸውን አመልክተዋል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖረው ህዝብ ካለው የጦር መሳሪያን ይዞ ከመንቀሳቀስ ልምድ አንጻር ክልከላውን ለማስፈጸም አስቸጋሪ አይሆንም ወይ? ተብለው የተጠየቁት ኮሚሽነሩ "ክልከላው በተጣለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ውሳኔውን እንዲረዱት በተለያዩ አካላት ሥራ እየተሰራ ነው። ነገር ግን በሌሎች አካባቢዎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ ህጋዊ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ይቻላል። አላማውም ከትጥቅ ማስፈታት ጋር የሚያያዝ አይደለም" ብለዋል።

በቅርቡ በምዕራብና ማዕከላዊ የጎንደር አካባቢዎች በተከሰቱ የሰላም መደፍረስ ችግሮች ምክንያት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከደረሱ ጉዳቶች በተጨማሪ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ክልሉ መግለጹ ይታወሳል።

ድብቅ የህጻናት ጋብቻዎች

የሴት ልጅ ግርዛት ምንድነው? የት እና ለምን ይፈጸማል?

ከዚህ አንጻርም ኮሚሽነሩ ባለፉት ሳምንታት በተከሰቱ ግጭቶች ጥፋት ያደረሱ ግለሰቦች ተፈልገው በህግ እንዲጠየቁ እንደሚደረግና በአጠቃላይ እስካሁን በዚህ የብጥብጥ ሂደት ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦችን በቁጥጥር የሚያውል የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ አስፈላጊውን ተግባር እያከናወነ መሆኑንና "አጠቃላይ የጥፋቱ መጠን፣ የጠፋዉ ንብረት፣ የተሳታፊዎች ዝርዝር፣ የተጎዱ ሰዎችን በተመለከተ በቀጣይ ይፋ ይደረጋል" ብለዋል።

ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግም የሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፖሊስና የጸጥታ ሃይሎች እንደተሰማሩም ተገልጿል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ