ከድምፃዊ ቤቲ ጂ እና ቸሊና ጀርባ ያለው ወጣት

ያምሉ ሞላ

ከሁለት ዓመታት በፊት ገደማ ነበር ድምፃዊት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) 'ማነው ፍፁም' በተሰኘ አልበም ብቅ ያለችው። ቀጥላም 'ወገግታ' ብላ በሰየመችው ሁለተኛ አልበሟ ኢትዮጵያና አፍሪቃን ዋጀች።

ቤቲ ጂ፤ በአምስተኛው የመላው አፍሪቃ የሙዚቃ ሽልማት (አፍሪማ) ላይ በስድስት ዘርፎች ታጭታ ሦስቱን ወደሃገሯ ይዛ ተመለሰች።

ታድያ ከቤቲ ጂ ስኬታማ አልበም ጀርባ ብዙ ያልተባለለት አንድ ወጣት አለ።

ያምሉ ሞላ 'ወገግታ' አልበምን ሙሉ በሙሉ 'ፕሮዲዩስ' ከማድረግም አልፎ የአልበሙን ሙዚቃዎች ሙሉ ግጥም የፃፈላት እርሱ ነው።

ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ለመዋብ ምን ያህል ይከፍላሉ?

የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች

«አልበሙ የሁለታችንም ሕይወት ነፀብራቅ ነው። አንድ ዘፈን አብረን ፅፈናል። በሳምንት አንዴ ሁለቴ እንገናኝ ነበርና እናወራለን። ከዚያ በአምስት ወር ገደማ አልበሙን አጠናቀቅነው። ድህረ 'ፕሮዳክሽን' የነበረው ሂደት ግን ጊዜ ወስዶብናል።»

ቤቲ ጂ እና ያምሉ የለፉበት ሥራ ፍሬ አፍርቶ የአልበሙ ስኬታማነት በአፍሪካ ናኝቷል፤ አልፎም በሥራዎቿ ትልቁን የአፍሪማ ሽልማት ልታገኝ ችላለች።

«በጣም ደስ የሚያሰኝ ጊዜ ነበር። ሥራዎቻቸው ቢልቦርድ ላይ የወጡላቸው ታዋቂ ዘፋኞች ነበሩ። ከአንድ ሃገር ብዙ በታጨ በሚለው እኛ ነበርን አንደኛ። ቤቲ በስድስት ዘርፎች፤ እኔ ደግሞ በሁለት ዘርፎች። የዓመቱ ምርጥ አልበም ተብለን ስንሸለም በጣም 'ሰሪል' የሆነ ስሜት ነበር የተሰማን።»

ያምሉ ሞላ በሁለት ዘርፎች ቢታጭም ሽልማት ሊያገኝ ግን አልቻለም። ለምን?

«እውነት ለመናገር ነገሩ ግርታን ፈጥሮብኛል። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ አንድ አልበም ሲያሸንፍ፤ አልበሙን ያቀናበሩ፤ ግጥሙን የፃፉ፤ ዜማ የደረሱ አብረው ይሸለማሉና። አሠራራቸው እንዴት እንደሆነ አላውቅም፤ ግን እኔ የታየኝ ነገር ቤቲ ማሸነፏ እኔ እንዳሸነፍኩ እንደሆነ ነው። እናሸንፋለን ብዬ አስቤ ስላልነበር፤ እጅግ በጣም ደስ የሚል ጊዜ ነበር። እኔ ይህ በመሆኑ ምንም አልከፋኝም። ምክንያቱም ይህ ገና የመጀመሪያ ነው እንጂ የመጨረሻው አይደለም።»

ሊና

'ሳይ ባይ' በተሰኘው ነጠላ ዜማዋ የምትታወቀው ቼሊና በቅርቡ የመጀመሪያ አልበሟን ለሙዚቃ አድማጩ ማበርከቷ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። 14 ሙዚቃዎች የተካተተቡት ይህ አልበም አዲስ ነገር ይዞ መጥቷል ሲሉ በርካቶች እያወደሱት ይገኛሉ። ታድያ ከ14ቱ ሙዚቃዎች 11 ያህሉን ያዘጋጃቸው ያምሉ ነው።

“ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ

«ከቼሊና ጋር ሥራውን የጀመርነው የዛሬ ሁለት ሦስት ዓመት ገደማ ነው። ከዚያ መሀል ተቋርጦ ነበር። እንደገና ደግሞ ተመለስንበት። ብዙዎቹን ጽፌያቸዋለሁ፤ ግጥምና ዜማቸውን። እሷም ጎበዝ ዜማ ሠሪ ናት። አልበሙ ከወጣ ብዙ ጊዜ አልሆነውም። ቢሆንም ደስ የሚል 'ፊድባክ' እየሰማሁ ነው።»

አዳዲስ ሥራዎች

"ወገኛ ነች" እና "እስከመቼ" በተሰኙ ነጠላ ዜማዎቹ ይታወቃል፤ ጊታሩ ተጫዋቹ ዜመኛ ዘሩባቤል ሞላ። የያምሉ ሞላ ወንድም ነው። በቅርቡ ሙሉ አልበም ሠርተው ለአድማጭ ጆሮ ለማድረስ ተፍ ተፍ እያሉ ነው።

ያምሉ፤ «ዘሩባቤል በጣም ጎበዝ ጊታሪስት እንዲሁም ቮካሊስት ነው» ሲል ስለ ወንድሙ ይመሰክራል።

ያምሉ፤ ከታዋቂ ሙዚቀኞች ይልቅ ከአዳዲሶቹ ጋር መሥራትን እንደሚመርጥ ይናገራል።

«በጣም ታዋቂ ከሆኑ ሰዎች ጋርም እየሠራሁ ነው። ነገር ግን እኔ የሚያስደስተኝ ከአዳዲስ ሙዚቀኞች ጋር ስሠራ ነው። ከዘሩባቤል በተጨማሪ ከሚኪያስ (የሃሴት አኩስቲክ አባል)፤ ጋር አልበም እየሠራን ነው። ፌላ የምትባል አዲስ ልጅ አለች። አርቲስት፣ ራፐር እንዲሁም የግጥምና ዜማ ደራሲ ከሆነው ደስ (ደስ አበጀ) ጋርም እየሠራሁ ነው። ብዙ ጽሑፎችን የጻፈ ነው፤ ለጃኖ ባንድ የመጨረሻ አልበም ሙዚቃዎችን አበርክቷል።»

3-11

ብዙ ጊዜ የሙዚቃ ሰዎች ሥራዎቻቸውን ከቀን ይልቅ ምሽት ላይ መሥራት እንደሚመርጡ ሲናገሩ ይደመጣል። ያምሉ ግን የፈለገ ቢሆን አምሽቼ መሥራት አልመርጥም ይላል።

ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም"

«ትልቁ ነገር ምን መሰለህ? ጤና ነው። ጤንነት ያስፈልጋል። ሙዚቀኞች ሌሊት ላይ የሚሠሩበት የራሳቸው ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል። እኔ ግን ጠዋት በሰዓቴ ገብቼ ደንገዝገዝ ሲል ነው መውጣት የምፈልገው። አንደኛው ምክንያቴ ደግሞ ከሱስ መራቅ መፈለጌ ነው። ላምሽ ብዬ ጫት መቃምም ሆነ ሌላ ዓይነት አበረታች ነገር መውሰድ አልፈልግም።»

ሙዚቃ፣ ፀሎት እንዲሁም በዙሪያው ያሉ ነገሮች ማነቃቂያው እንደሆኑ የሚናገረው ያምሉ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ትልቅ ምሣሌ አድርጎ ይወስዳል።

«እኔ ፖለቲካ አልወድም። ነገር ግን እርሣቸው በዚህ ዕድሜያቸው እንቅልፍ ሳይወስዳቸው ለሃገር ይህን ሁሉ ነገር ካደረጉ እኔም ማድረግ አያቅተኝም ብዬ አስባለሁ። እርሳቸው በ40ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ናቸው። እኔ ደግሞ በ30ዎቹ።»

ስኬት ሲለካ

እውን ያምሉ ስኬትን የሚለካው እንዴት ይሆን? በሽያጭ? በተቀባይነት? ወይስ በሽልማት?

«(ፈገግ. . .) ምን መሰለህ? እኔ አነዚህ ነገሮች አይመለከቱኝም። ምን አስባለሁ መሰለህ ሁሌ. . . እኔ የምወደው ሥራ ነው? አብሬው ከምሥራው ሙዚቀኛ ጋር የውስጣችንን ማበርከት ችለናል ወይ? እኛ ወደነዋል ወይ? እኛ ጋር ያለው ስሜት ጤነኛ ነው ወይ? ነው የኔ ጥያቄ። ለመጨረስ ነው የሠራነው? ወይስ የተሰማንን ነገር በሙዚቃ ለማበርከት? ዋናው ነገር ነገ የምፀፀትበት ነገር፤ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ተጨምሬ ወደኋላ የምጎትትበት ነገር እንዳይሆን ነው ትልቁ ስጋቴ።»

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ