አሰልጣኝን አሻፈረኝ ማለት ይቻላል?

ኬፓ አሪዛባላጋ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ኬፓ አሪዛባላጋ

የቼልሲው በረኛ ኬፓ አሪዛባላጋ የአሰልጣኙ ማሪዞዮ ሳሪን ትዕዛዝ አልቀበልም ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል።

አሰልጣኙ ለካራቦ የፍፃሜ ጨዋታ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በተደረገው ጨዋታ የቡድኑን በረኛ ኬፓ አሪዛባላጋን ለመቀየር አስቦ ትዕዛዝ ቢያስተላልፍም በረኛው አሻፈረኝ ብሏል።

ጨዋታው ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ሲያመራ፣ አሰልጣኙ የፍጹም ቅጣት ምት ኳሶችን የማዳን ብቃቱን በ2016 ከሊቨርፑል ጋር ባደረጉት ጨዋታ ባዳናቸው ሦስት ግቦች ያስመሰከረውን ዊሊ ካባልሮን ለማስገባት ፈለጉ።

የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት

ሆኖም ኬፓ ቦታውን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልነበረም። አሰልጣኙ ቢጮሁ፣ እጃቸውን ቢያወናጭፉ ኬፓ የሚሰማ አልነበረም። ስለዚህም ኬፓ በበረኛነቱ ቀጠለ። አሰልጣኙ ሳሪ በብስጭት ነደዱ።

በፍጹም ቅጣት ምቱ ኬፓ ማዳን የቻለው አንድ ኳስ ብቻ ነበረ። በደንብ ዝቅ ቢል መመለስ የሚችለውን ኳስ ሳያድን ቀርቶ ማንችስተር ሲቲ ድል ተቀዳጀ።

በእርግጥ ሳሪ የአሰልጣኙን ትእዛዝ አልቀበልም ያለ ብቸኛው ስፖርተኛ አይደለም።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሰሬና ዊልያምስ

ሴሬና ዊሊያምሰ

እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 በሴሬና ዊሊያምስ እና ናኦሚ ኦስካ መካከል የተደረገው የሴቶች ዩኤስ ኦፕን የሜዳ ቴኒስ የፍፃሜ ግጥሚያ ላይ ሴሬና አሰልጣኟን ተገዳድራለች።

ሴሬና ለአሰልጣኟ ባሳየችው ያልተጋባ ድርጊትና የጨዋታ ሕግ በመጣሷ ከተቀጣች በኋላ ጨዋታው አሳዛኝ ሆኖ ተጠናቋል። ያልተገባ ቃል በመናገሯም ከአንድ ጨዋታ ታግዳ ነበር።

በታላቁ ሩጫ ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ላይ የአበረታች መድኃኒት ምርመራ ሊካሄድ ነው

ሰሬና የጨዋታው ስርዓት አስከባሪ ከአሰልጣኟ ፓትሪክ ሞራቶግሉ ጋር መክሮ ቅጣት ካስተላለፈባት በኋላ "ውሸታም" እና "ሌባ" ብላው ነበረ።

ሰሬና በጨዋታው ላይ አሰልጣኟ ምክር እንዳልሰጣት ስትናገር አሰልጠኟ ግን ምልክት እያሳየኋት ነበር በማለት ወቀሳዋን ችላ ብሏል።

በወቅቱ ሰሬና እንዲህ ብላ ነበር "እንቅስቃሴ እያደረኩ ልነግራት ሞክሬያለው ይላል። ለጨዋታው ምክር ሰጥቻታለው ብሎም ይናገራል። ለእኔ ይሄ ምንም ትርጉም አይሰጥም። ለምን እንደዛ እንዳለም አላውቅም።"

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ፓውላ ራድክሊፍን አሰልጣኟ

ፓውላ ራደክሊፍ

ብዙ ጊዜ የአሰልጣኝ እና የአትሌት ግንኙነት ውስብስብ ነው። እንደ ፓውላ ራደክሊፍ እና አሰልጣኟ ጋሪ ሎፍ ባል እና ሚስት ሲሆኑ ደግሞ ውጥረቱ በደንብ ይታያል።

እንደ አውሮፓውያኑ በ2001 ፓውላ ራድክሊፍ የኤድመንተንን የሴቶች 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ለማሸነፍ መቃረቧ ይታወሳል።

ጋሪ ሎፍ ከመግቢያው መስመር ጀርባ ሆኖ ለራድክሊፍ በጩኸት ምክር እያዘነበላት ነበር። ተፎካካሪዎቿ አትሌቶች ደራርቱ ቱሉ፣ ብርሃኔ አደሬ እና ጌጤ ዋሚ ጀርባ ስትደርስ ጋሪ እንባ የተናነቃት ሚስቱ የሰራችውን ስህተት ሊነገራት ቀረበ።

ሁኔታው እንዳሰበው አልሄደም። ራድክሊፍ ገፍትራው አለፈች።

ጆርጅ ዊሃ በላይቤሪያ ምርጫ እየመራ ነው፤ አርሰን ቬንገር ተሸወዱ

"ሯጯ እሷ ናት ስለዚህም ውሳኔው የሷ ነው" ብሏል አሰልጣኟ። "በጣም ይቅርታ ብያታለው፤ ውጤቱን እንደምትቀበለው ተስፋ አለኝ።"

ራድክሊፍ መልስ የሰጠችው ሁላችንም በስሜት ውስጥ ነበርን ስትል ነበር።

"ያን ሰዓት ላይ የተሳሳትኩትን ነገር ለመናገር ትክክለኛው ጊዜ አልነበረም" ብላለች።