የምግብ ምርጫዎ ስለማንነትዎ ይናገራል?

ባህላዊ ምግብ Image copyright Cyrus McCrimmon

ብዙ ጊዜ ከምግብ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ነገር የቤተሰብ አባላት ስለ ምግብ ያላቸው አስተሳሰብ ነው። በዚሁ ዙሪያ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት አብዛኞቹ አሜሪካዊያን ቤተሰቦች ስለሚመገቡት ምግብ ጤናማነት አብዝተው ይጨነቃሉ።

በሌሎች ሀገራት የሚኖሩ ቤተሰቦች ደግሞ ምግቡ ምንም ይሁን ምን ዋናው ነገር መጣፈጡ ነው ብለው ያስባሉ።

እርስዎ ጥሩ ምሳ በላሁ የሚሉት ምን ሲመገቡ ነው?

ምናልባት አንዳንዶች አትክልት የበዛበት ነገር ሊመርጡ ይችላሉ፤ ሌሎች ደግሞ ሥጋ ነክ የሆኑ ምግቦችን ሊያስቀድሙ ይችላሉ፤ በርገር አልያም ፒዛ የሚሉም አይጠፉም።

እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል?

የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት የምግቡ አይነት ብቻ ሳይሆን ስለምግቡ የምናወራበት መንገድና ባህላችን ጥሩ ወይም መጥፎ ብለን ለመለየት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

ባለሙያዎቹ እንዲያውም ምግብና ስለምግብ የሚደረጉ ውይይቶች የአንድን ማህበረሰብ ባህል፣ ማንነትና ፖለቲካዊ አቋም እስከመግለጽ ይደርሳሉ ይላሉ።

ተመራማሪዋ ማርታ ሲፍ ካረባይክ፣ ዴንማርክ ውስጥ ስላጋጠማት ነገር ስታወራ ተማሪዎች 'ሪይ' የተባለውን የዳቦ አይነት ለምሳ ይዘው እንዲመጡ ይመከራሉ ትላለች።

ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን?

ይህንን የማያደርጉ ከሆነ ግን ምግባቸው ጤናማ እንዳልሆነ በአስተማሪዎቻቸው ተነግሯቸው ለቤተሰቦቻቸው ማስጠነቀቂያ ይላካል ስትል ባህል በምግብ ላይ ያለውን ተጽእኖ ታስረዳለች።

''ይህ የሆነው 'ሪይ' የተባለው የዳቦ አይነት የተለየ ጤናማ ንጥረ ነገር በውስጡ ስለያዘ ሳይሆን ባህልና ማንነትን ለመግለጽ ስለሚጠቀሙበት ነው።''

Image copyright Getty Images

ሌላዋ ተመራማሪ ካትሊን ራይሊ ደግሞ በፈረንሳይ በነበራት ቆይታ አስገራሚ ነገር እንደታዘበች ትናገራለች።

የአንድ ማህበረሰብ አባላት ምግባቸው የማይጣፍጥ አልያም መጥፎ እንደሆነ ከተነገራቸው፣ ሰዎቹ ራሳቸው መጥፎ እንደተባሉና ባህላቸውም እንደተሰደበ ይቆጥሩታል።

እነዚህ ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ከፍ ያለ ቦታ ከሌሎች ለመለየትና አስጠብቆ ለማስቀጠል ከሚጠቀሟቸው መንገዶች መካከል የሚበሉት የምግብ አይነት በዋነኛነት ይጠቀሳል።

ምግቦቻ ለዓለም ያለንን አመለካከት የሚቀርጹት እንዴት ነው?

ማርታ ሲፍ ካረባይክ እንደምትለው ባለፉት አስር ዓመታት አሳማና የአሳማ ተዋጽኦዎችን አብዝቶ መጠቀም የዴንማርኮች መገለጫ እየሆነ መጥቷል።

አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች

ዴንማርክ ውስጥ በአንድ ወቅት ትምህርት ቤቶች የአሳማ ስጋን ከምግብ ዝርዝራቸው ውስጥ አስወጥተው ነበር። ይህ ደግሞ ከዓለም አቀፋዊነትና ስልጣኔ ጋር ተያይዞ እንደመጣ ይታሰባል።

ጉዳዩ ያሳሰበው የአንድ ግዛት ምክር ቤት ትምህርት ቤቶች የአሳማ ስጋን በምግብ ዝርዝራቸው ውስጥ እንዲያካትቱ የሚያስገድድ ሕግ አውጥቶም ነበር።

በሕጉ መሰረት ማንኛውም ተማሪ የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ቢሆን የዴንማርክ መገለጫ የሆኑ ምግቦች የመመገብ ግዴታ አለበት። የአሳማ ስጋ ደግሞ ዋነኛው ምግባቸው ነው።

Image copyright Getty Images

ስለዚህ ዴንማርካዊያን 'ሪይ' የተባለውን ዳቦ ሲመገቡ ስለጤናቸው በማሰብ ሲሆን የአሳማ ስጋን ሲበሉ ደግሞ ባህላቸውንና ማህበረሰባዊ እሴቶቻቸውን ከማስቀጠል አንጻር ነው።

ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች

ካትሊን ራይሊ እንደምትለው ድሮ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ምግብ ሳይሆን የተሻለ ሥራ ነበር። ዛሬ ዛሬ ግን ሰዎች የሚበሉትን ምግብ በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ቦታ እንደማሳያ ይጠቀሙታል።

ተያያዥ ርዕሶች