የ82 ዓመቱ የአልጀሪያ መሪ አብደላዚዝ ቡተፍሊካ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል

ፕሬዝደንት አብደላዚዝ ቡተፍሊካ Image copyright AFP

የአልጄሪያው መሪ አብደላዚዝ ቡተፍሊካ ከዜጎቻቸው እየደረሰባቸው ያለውን ተቃውሞ ወደጎን በማለት ለአምስተኛ ጊዜ ለስልጣን መወዳደር እንደሚፈልጉ ያስታወቁ ሲሆን ሙሉ አምስት ዓመት ግን አልጨርስም ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ባስነበቡት ደብዳቤ በመጪው ሚያዚያ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚያሸንፉ ከሆነ ብሔራዊ መድረክ በማቋቋም እሳቸው የማይሳተፉበት አዲስ የምርጫ ስርአት እንደሚዘረጉ ገልጸዋል።

ነገር ግን ለአምስተኛ ጊዜ ስልጣን ለመያዝ ማሰባቸው ብዙሃኑን አልጄሪያዊ ከማስቆጣት አልፎ ላለፉት ቀናት ትልቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ምክንያት ሆኗል።

ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ

መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ

የ82 ዓመቱ ቡተፍሊካ ከፈረንጆቹ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸዋል። እሳቸው ግን ምንም አይነት ነገር ፕሬዝዳንት ከመሆን አያግደኝም እያሉ ይመስላል።

አሁንም ቢሆን ፕሬዝዳንቱ በሃገረ ስዊዘርላንድ የህክምና ክትትል እያደረጉ ሲሆን በአዛውንት አንመራም ያሉ በርካታ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ወጣቶች ትናንት በዋና ከተማዋ አልጀርስ ከባድ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።

በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ስድስት ተፎካካሪዎች ተቀባይነት ያገኙ ሲሆን የቀድሞው ጀነራል አሊ ጌድሪ አንዱ ናቸው።

እሳቸውም በአልጄሪያ ታይቶ የማይታወቅ አይነት ለውጥ አመጣለው እኔን ምረጡኝ ሲሉም ተደምጠዋል።

Image copyright EPA

የንግድ ሰው የሆኑት ራሺድ ኔካዝ ደግሞ ባልተለመደ መልኩ ብዙ ' የፌስቡክ' ተከታዮች ያሏቸው ሲሆን በአልጄሪያውያን ወጣቶች ዘንድ ተቀባይነትና ፍቅርን ማትረፍ ቢችሉም ለፕሬዝዳንትነት መወዳደር እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል።

ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግሞ የሃገሪቱን ሁኔታ በመቃወም ከምርጫው እራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል።

በፈረንጆቹ 1999 ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡተፍሊካ ከሚታወቁባቸው ጉዳዮች መካከል በሃገሪቱ ተከስቶ የነበረውንና የ100 ሺ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን የእርስ በርስ ጦርነት ማስቆማቸው ነው።

ኢራቅ ከአሜሪካ የበለጡ ሴት እንደራሴዎች አሏት

ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን?

ከ2011 ጀምሮ ደግሞ በአልጄሪያ የምግብ ዋጋ መጨመሩና የስራ አጦች ቁጥር ማሻቀብ ከባድ ተቃውሞ አስነስቶ ነበር።

ምንም እንኳን ብዙዎች ፕሬዝዳንቱ አርጅተዋል አሁን ካለው የፖለቲካ ስርአት ጋር አብረው መሄድ አይችሉም ቢሉም ሰሚ ያገኙ አይመስልም።

ቡተፍሊካ በመጪው ሚያዚያ ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ከሆነ የማሸነፋቸው ነገር እርግጥ ነው የሚሉም አልጠፉም።

ተያያዥ ርዕሶች