ኦሮሚያ ክልል ዘገባው ሃሰት በመሆኑ ኢሳትን እከሳለሁ ብሏል

ESAT LOGO Image copyright ESAT

ትናንት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሃሰተኛ ዜናዎችን በማሰራጨት ኢሳትን እንደሚከስ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ሃላፊው እንዳሉት ኢሳት በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን በሺህዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች በሃይል እየተፈናቀሉ፤ ሴቶችም መደፈራቸውን ሪፖርት አድርጓል።

ዘገባው ግን ሃሰት ነው ሲሉ አቶ አድማሱ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በተለይም በቄለም ወለጋ ዞን በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የተደረገ ጥቃት አለመኖሩን ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ

ነገሩን ወደ ህግ ለመውሰድ ከውሳኔ ላይ የደረሱት በቄለም ወለጋ ዞን ኢሳት ተፈፀሙ ብሎ የዘገባቸው ነገሮች አለመደረጋቸውን በማረጋገጣቸው እንደሆነም አቶ አድማሱ ገልፀዋል።

"በቄለም ወለጋ ዞን የሚገኙ የአማራ ብሄር ተወላጆች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ጫና እየተደረገባቸው ነው" የሚለው የመጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም ዘገባው በጥቆማ ላይ ተመስርቶ በማጣራት የተሰራ እንደሆነ የኢሳት ስራ አስኪያጅ የሆነው ታማኝ በየነ ለቢቢሲ ተናግሯል።

ያልጠገገው የሀዋሳ ቁስል

"እኛ ከህዝብ ያገኘነውን ዜና መርምረን ነው የምናቀርበው። ስለዚህ ዜናችን ትክክል ነው" በማለት የሚያገኟቸውን መረጃዎች በሚገባ መርምረውና አረጋግጠው እንደሚዘግቡም ታማኝ ገልጿል።

ኢሳት በዘገባው ለምን የክልሉን መንግስት አስተያየት አላካተተም? የሚል ጥያቄ የቀረበለት ታማኝ "ሞክረናል ምላሽ የሚሰጥ ጠፋ እንጂ ፤ ባለስልጣኖችም ተጠይቀዋል" የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

ኢሳት ያደረገው ይህ ጥረት አለመሳካቱን ግን በዘገባው አላካተተም።

ተያያዥ ርዕሶች