ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነቶች ላይ ደርሰዋል

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ እና የኢትዯጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ Image copyright OFFICE OF THE PRIME MINISTER
አጭር የምስል መግለጫ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ እና የኢትዯጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ

ዛሬ ጠዋት መጋቢት 4 ኢትዮጵያና ፈረንሳይ በሂልተን ሆቴል የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

ሁለቱ ኃገራት ስምምነት ከደረሱባቸው ዘርፎች መካከል የፈረንሳይ ኢቬስትመንትን በኢትዮጵያ ለማበረታት፣ የኢትዮጵያን ምጣኔ ኃብት ለውጦችን ለማገዝ የሚደረጉ የገንዘብ ድጋፍና የባህልን ጥበቃ ይገኙበታል።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ሰራተኛ መሳይ ፈጠነ ለቢቢሲ እንደገለፀው ከሰአት እጥረት አንፃር ቃለ መጠይቅ ማድረግ አይቻልም ቢባልም ለተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

Image copyright OFFICE OF THE PRIME MINISTER
አጭር የምስል መግለጫ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ እና የኢትዯጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓቱን ሲታዘቡ

የስምምነቶቹ ፈራሚዎች ስም ዝርዝር ከዚህ በታች እንደሚከተለው ነው።

1) ደ/ር ዦ ኢቭ ለ ጋል እና ዶ/ር ሰለሞን በላይ ተሰማ የጠረፍ ትብብር ተፈራርመዋል

2) አቶ ቤርናር ኩሌ እና አቶ ተመስገን ጥላሁን ለሶምዲያ ፋብሪክ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል

3) አቶ ሮዶልፍ ሳዴ እና አቶ ሙሉጌታ አሰፋ ለጭነት ሎጂስቲክስ የሽርክና ንግድ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል

4) አቶ ሮዶልፍ ሳዴ እና አቶ ሮባ መገርሳ ለከፍተኛ ትምህርት ፈተናዎች የትብብር ፍላጎት ማሳያ ስምምነት

5) አቶ ቲዬሪ ዴዮ፣ ወ/ሮ ማሪ ላም ፍሬዶ እና አቶ ጥላሁን ታደሰ ለኮንስትራክሽን የትብብር ፍላጎት ማሳያ ስምምነት

6) አቶ ማክሲም ሳዳ እና አቶ ቴዎድሮስ አብራሃም ለቴሌቪዥን ፕሮግራም የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል

7) አቶ ፓትሪክ ጌሬንቶን እና አቶ ቴዎድሮስ አብርሃም ለትራንስፖርትና የጭነት ሎጂስቲክስ የሽርክና ንግድ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል

Image copyright OFFICE OF THE PRIME MINISTER
አጭር የምስል መግለጫ በሂልተን ሆቴል የተደረገው የ7 ስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓት

የስምምነቱ ፊርማ ታዛቢዎችም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው

1) የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሺዴ

2) የአውሮፓ የውጪ ፉዳይ ሚኒስትር አቶ ዦ ኢቭ ለ ድሪያ

3) የከፍተኛ ትምህርት ምርምርና ፈጠራ ሚኒስትር ወ/ሮ ፍሬዴሪክ ቪዳል

4) የኢትዮጵያ ግዛት ሚኒስትር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው

5) ከአስተዳደር ሚኒስቴርና ኢኮሎጂካል እና ተካታዊ ሽግግር ጋር የሚሠራው የፈረንሳይ ግዛት ሚኒስትር ወ/ሮ ብሩን ፕዋርሶ

6) ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ ትናንት መጋቢት 3 ቀን ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ነበር ኢትዮጵያ የገቡት።

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ከጎበኙ በኋላ ጉዟቸውን ወደ አዲስ አበባ ያቀኑ ሲሆን ዛሬ ከአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ጋር እንደሚገናኙም ተነግሯል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ