ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹን በሙሉ አገደ

American Airlines Boeing 727 Max 8 Image copyright Joe Raedle

የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ አሰቃቂው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተከሰከሰበት ቦታ ላይ አዳዲስ መረጃዎች በመገኘቱ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹን በሙሉ አግዷል።

ኩባንያው እንዳሳወቀው ያሉትን 371 አውሮፕላኖቹን አግዷል።

የአሜሪካ ፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር እንደገለፀው አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ የተገኙ አዳዲስ መረጃዎችና የተጣሩ የሳተላይት ምስሎች አስተዳደሩ በጊዜያዊነት የእግድ ውሳኔውን እንዲያስተላልፍ አድርጎታል።

እንግሊዝ ቦይንግን ከበረራ ካገዱት ሃገራት ተቀላቀለች

በርካታ ቁጥር ያላቸው ሀገራት ቦይንግ 737-8 ማክስን ሲያግዱ አስተዳደሩ እምቢተኝነት ማሳየቱ የሚታወስ ነው።

እለተ እሁድ መጋቢት 1 ቀን ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር የነበረው ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ለ157 ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው

ከአምስት ወራት በፊት የኢንዶኔዥያ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737-8 ማክስ ተከስክሶ 189 ሰዎች ከሞቱበት አደጋ ቀጥሎ አስከፊው ነው ተብሏል።

የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር ያገኘው መረጃ ምንድን ነው?

አስተዳደሩ ከብሔራዊ የትራንስፖርት ጥበቃ ቦርድ ጋር በመተባበር አደጋውን የሚመረምር ቡድን የላኩ ሲሆን፤ የድርጅቱ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ዳን ኤልዌል በትናንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራው ዱካ ከላየን አየር መንገድ ጋር ተመሳሳይ ነው" በተጨማሪም የመከስከስ አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ የተገኙት መረጃዎች በላየን አየር መንገድ ከደረሰው ዕጣ ፈንታ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አሳይ ነው ብለዋል።

"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው አስተዳደሩ በአደጋው ስፍራ ላይ ባገኘው አዳዲስ እንዲሁም ቁሳዊ መረጃዎችን፤ ከሌሎች ቦታዎችም የተገኙ መረጃዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት አስቸኳይ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፍ ተናግረው ነበር።

ቦይንግ 737-8 ማክስን በማገድ አሜሪካና ብራዚል የእንግሊዝ፣ ቻይና፣ ህንድና አውስትራሊያን ፈለግ ተከትለዋል።

በትላንትናው እለት የካናዳ ትራንስፖርት ሚኒስትር ስለ አደጋው አዲስ መረጃ አግኝቻለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹን አግዳለች።

እንደ መረጃውም በቅርቡ የተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8ና ካናዳ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ ያሉት 737 ማክስ አውሮፕላኖች ተመሳሳይ የበረራ ሁኔታን ማሳየታቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ