ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹ በሙሉ እስከ ግንቦት እግድ ተጣለባቸው

American Airlines Boeing 727 Max 8 Image copyright Joe Raedle

እሁድ ዕለት በኢትዮጵያ አየር መንገድ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ ቦይንግ 737- ማክስ 8ና 9 አውሮፕላኖቹ ቢያንስ እስከ ግንቦት ድረስ እንዲታገዱ የአሜሪካ ፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር ውሳኔን አስተላልፏል።

የአሜሪካ ተቆጣጣሪዎች እንዳሳወቁት ሶፍትዌሮቹ ተገጥመው እስኪሞከሩ ድረስ መብረር አይችሉም ተብሏል።

ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹን በሙሉ አገደ

እለተ እሁድ መጋቢት 1 ቀን ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር የነበረው ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ከ35 አገራት ለመጡ 157 ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል።

"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ

ከአምስት ወራት በፊት የኢንዶኔዥያ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737-8 ማክስ ተከስክሶ 189 ሰዎች ከሞቱበት አደጋ ቀጥሎ አስከፊው ነው ተብሏል።

በዘርፉ ላይ ያሉ አስተያየት ሰጭዎች ከአደጋው ቦታ ላይ የተወሰዱ መረጃዎችንና የሳተላይት ምስሎችን በማጤን በኢትዮጵያ አየር መንገድና ከስድስት ወራት በፊት በኢንዶኔዥያ የደረሰው ግንኙነትና ተመሳሳይነት እንዳለው ነው።

"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ

በተጨማሪም የመከስከስ አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ የተገኙት መረጃዎች በላየን አየር መንገድ ከደረሰው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አሳይ ነው ብለዋል።

የአሜሪካ ተወካይ ሪክ ላርሰን እንደገለፁት መተግበሪያውን (ሶፍትዌሩን) ለማሻሻል ጥቂት ሳምንታት እንደሚወስድና በአውሮፕላኖቹ ላይ ለመግጠምም ቢያንስ እሰከ መጋቢት ድረስ ይቆያ።

"እናቱ ስታየኝ 'ልጄ ያሬድ ይመጣል' እያለች ታለቅስ ነበር"- በናይሮቢ የካፒቴኑ ጸጉር አስተካካይ

እሁድ እለት የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቦይንግ 737-ማክስ 8 የበረራ ቁጥር ET 302 አውሮፕላን መረጃ ሳጥን በፈረንሳይ አገር እንዲመረመር በትናንትናው ዕለት ወደ ፓሪስ መወሰዱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትዊተር ገጿ አስፍራለች።

ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጀርመንን የጠየቀችው በጎርጎሳውያኑ 2010 ሊባኖስ ላይ በደረሰው አደጋ የምርምሩን ስራ በሰራችው ፈረንሳይ ኢትዮጵያ ደስተኛ ባለመሆኗ ነው።

Image copyright Getty Images