የትኞቹ ሃገራት ከፍተኛ ስደተኛ አላቸው?

ወደ አሜሪካ የሚጓዙ የደቡብ አሜሪካ ሃገራት ዜጎች Image copyright Getty Images

ምናልባት በዓለም ላይ ያሉ የስደት ገፊ ምክንያቶች አንዳንዶቹ አስደንጋጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ለመሆኑ በምድራችን ላይ ካለው ሕዝብ ከ4% በታች የሆኑ ሰዎች ብቻ ከትውልድ ቦታቸው እርቀው እንደሚኖሩ ያውቃሉ?

የዓለማችን ውድ እና ርካሽ ከተሞች ይፋ ሆኑ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ2017 ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከሆነ ከዚህ በታች ያሉት ሃገራት ከሌላ ሃገር የሚመጡ ዜጎችን በማስተናገድ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው። ምጥጥኑ የሚያሳየውም ስደተኞች ከአጠቃላይ ሕዝቡ ያላቸውን ድርሻ ነው።

ስደተኞች ከአጠቃላይ ሕዝብ አንጻር ያላቸው ድርሻ
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ 88.4
ሲንጋፖር 46
ሳኡዲ አረቢያ 37
ስዊዘርላንድ 29.6
አወስትራሊያ 28.8
ካናዳ 21.5
ኦስትሪያ 19
አሜሪካ 15.1
ጀርመን 14.8
እንግሊዝ 13.4
ስፔን 12.8
ሆላንድ 12.1

በአጠቃላይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ መሠረት በ2017 የስደተኞች መጠን 258 ሚሊዮን ብቻ ነበር። ይህም 3.4% የዓለምን ሕዝብ ድርሻ ይየዛል። ይህ አሃዝ የጨመረው ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ነው። ከ1990 በፊት ዓመታዊ የስደት መጠን 2̈.9% ፤ በ1965 ደግሞ 2̄.3% ነበር።

ጥናቱን ያከናወነው ፓሪስ የሚገኘው ናሽናል ኢንስቲቱት ኦፍ ዴሞግራፊክ ስተዲሰ አባል ፓይሶን እንደሚለው ውጤቱ ሊቀየር የሚችለው ምናልባትም ከ100 ዓመታት በኋላ እንጂ አሁን ባለው ሁኔታ ተጽዕኖው ብዙም አይደለም።

አምስት ነጥቦች ስለጌዲዮ ተፈናቃዮች

የ2015ቱ መረጃ እንደሚያሳየው አሜሪካ 49.8 ሚሊዮን ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ዜጎችን በማስተናገድ ከዓለም ቀዳሚ ነች። በመቶኛ ካየነው ግን ካሏት ነዋሪዎች 8 እጥፍ (88%) በማስተናገድ ከፍተኛ ምጥጥን ያላት ሃገር የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ነች። በሕዝብ ብዛት ግን አሜሪካ ብዙ ሕዝብ ተቀብላለች።

Image copyright Getty Images

አሁን ያሉት ፍልሰቶች

የፓይሶን ጥናት እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ከፍተኛ ስደት ያለው ከደቡብ ወደ ደቡብ ነው። ማለትም በአንዱ ታዳጊ ሃገር የተወለዱ ዜጎች ወደ ሌላ ታዳጊ ሃገር ይሰደዳሉ። በ2017 የእነዚህ ስደተኞች ቁጥር ከድሃ ሃገር ወደ ሃብታም ሃገር የሚሰደዱትን ቁጥር በልጧል። ፓይሶን እንደሚለው እስከ 1980 ድረስ የሰፔን ዜጎች በብዛት የሚሰደዱባት ሃገር ነበረች። አሁን ግን 13% የሚሆኑት ነዋሪዎቿ ከሌላ ሃገር የመጡ ናቸው።

'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ?

ለመሆኑ የትኞቹ ሃገራት ዜጎቻቸው በብዛት በሌላ ሃገር ይኖራሉ? የሚከተለው ሰንጠረዥ ምላሽ አለው።

የትኞቹ ሃገራት ዜጎቻቸው በብዛት በሌላ ሃገር ይኖራሉ?
ሕንድ 16.6 ሚሊዮን
ሜክሲኮ 13 ሚሊዮን
ሩሲያ 10.6 ሚሊዮን
ቻይና 10 ሚሊዮን
ባንግላዲሽ 7.5 ሚሊዮን
ሶሪያ 6.9 ሚሊዮን
ፓኪስታን 6 ሚሊዮን
ዪክሬን 5.9 ሚሊዮን
ፊሊፒንስ 5.7 ሚሊዮን
እንግሊዝ 4.9 ሚሊዮን
አፍጋኒስታን 4.8 ሚሊዮን

ከላይ ያለው ሰንጠረዥ የሚያሳየው የሕዝብ ብዛትን እንጂ በመቶኛ ያለውን ምጥጥን አይደለም።

በመቶኛ ካየነው 45 በመቶ ወይም 3.5 ሚሊዮን የሚሆነው ሕዝቧ ከግዛቷ ውጭ የሚኖርባት ሃገር ቦስኒያ ሄርዞጎቪና ነች። ኬፕ ቨርዴ እና አልባኒያም በዚህ ረገድ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሃገራት ናቸው። በአሁኑ ወቅት ስደተኞችን የሚቀበሉም የሚልኩም ሃገራት ስጋት እያስተናገዱ ነው። ለምሳሌ እንግሊዝ ከአውሮፓ ሕበረት እንድትወጣ የስደተኞቹ ጫና ቀላል የሚባል አይደለም። በሌሎች ሃገራትም ተመሳሳይ የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት ጫና ይደርሳል።

ተያያዥ ርዕሶች