ከክራይስትቸርች የመስጊድ ጥቃት በተአምር የተረፈው ኢትዮጵያዊ

አብዱልቃድ አባቦራ Image copyright አብዱልቃድ አባቦራ

በተለይ በኒውዚላንድ ዋነኛ ርዕስ ሆኖ እንዲህ አይነቱን አሰቃቂ ድርጊት ለመከላከል የሀገሪቱ መንግሥት በጦር መሳሪያ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ህግን እስከማውጣት የሚያደርስ ውሳኔ ላይ ደርሷል።

በዚህ ጥቃት የተገደሉትና ጉዳት የደረሰባቸው የተለያየ ሀገር ዜግነት ያላቸው ሰዎች ሲሆኑ ሁለት ኢትዮጵያዊያንም ከባድ የመቁሰል አደጋ እንዳጋጠማቸው ለማረጋገጥ ችለናል።

በእለቱ የአርብ የጸሎት ሥነ ሥርዓትን ለመካፈል ወደ መስጊዱ ሄደው ያሁሉ እልቂት በአንድ ታጣቂ ሲፈጸም በቅር የተመለከቱና ከጥቃቱ በተአምር የተረፉት ሌላው ኢትዮጵያዊ አቶ አብዱልቃድ አባቦራ በኒውዝላንድ የክራይስትቸርች ከተማ ነዋሪ ናቸው።

'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ?

ክስተቱንም ሲያስታውሱ " በዕለቱ የሳምንቱን አስተምሮ እየተከታተልን እያለን ከኋላችን በመግቢያው ኮሪደር በኩል ተኩስ ሰማን። ግን የሆነ ኤሌክትሪክ ኮንታክት ፈጥሮ ወይም ህጻናት በርችት የሚጫወቱ ነበር የመሰለን። ምክንያቱም ኒውዝላንድ ውስጥ በፍጹም እንደዚህ አይነት ነገር አንጠብቅም" ይላሉ።

ከዚያም በድጋሚ የተኩስ ድምጽና እሳት ወደ ውስጥ ከኮሪደሩ ሲገባ እንደተመለከቱና ከፊለፊታቸውም ሰዎቹም ሲወድቁ ተመለከቱ። የተኩሱም ውርጅብኝ እሳቸው ወዳሉበት እቀረበ መጣ። በዚህ ጊዜ መስጊዱ ውስጥ የነበሩ ሰዎች በሙሉ መስኮቶቹንና በሮቹን ሰባብረው መውጣት ጀመሩ። ማምለጥ የሚችለው በሙሉ አመለጠ።

ነገር ግን እሳቸው በነበሩበት ስፍራ በኩል በኩል ምንም አይነት በርም ሆነ መስኮት አልነበረም። ታጣቂው እየተኮሰ ወደ ክፍሉ ሲገባ የመጀመሪያው ረድፍ ላይ ሰለነበሩ አቶ አብዱልቃድ ፊትለፊት ተመልክተውታል። የያዘው የጦር መሳሪያም አውቶማቲክ ጠመንጃ እንደነበረና ጥይት ሲያልቅበት ካርታውን እየቀየረ ''በግራም በቀኝም እየዞረ ማጨድ ነው በቃ፤ አጨደን አጨደን'' ይላሉ።

ተኳሹ ማንንም ከማንም ሳይመርጥ ባገኘው ላይ እየተኮሰ ይጥላል። "በዙሪያው ያሉትን ሰዎቹን ረፍርፎ ከጨረሰ በኋላ ነብሱ ያልወጣውን፤ የሚተነፍሰውን ደግሞ እየዞረ አንድ በአንድ ገደላቸው። ወደ 15 ደቂቃ ሙሉ ነው ይተኩስ የነበረው።"

ከተገደሉት አንዱ የማዕድን ኩባንያው ባለቤት ነበር

አቶ አብዱልቃድ ይህን ሁሉ ክስተት የሚመለከቱት በሞት ተከበው ባሉበት የመስጊዱ አንድ ጥግ ላይ ሆነው ነበር። "እኔ በአጋጣሚ ለመሮጥ ስላልቻልኩኝ ከፊቴ አንድ ቁርአን የሚቀመጥበት የመጽሃፍት መደርደሪያ ነበረ። እሱን ሳብኩትና እላዬ ላይ ጣልኩት። ከጭንቅላቴ እስከ ወገቤ ተሸፍኘኜ ስለነበረ ገዳዩ አላየኝም" ይላሉ።

መስጊዱ ውስጥ የተኩስ ሩምታ ሲዘንብ መውጫ አጥተው ነፍሳቸውን ማትረፍ ካልቻሉት መካከል አቶ አብዱልቃድ እና የመስጊዱ ኢማም ብቻ ነበሩ ምንም ሳንነካ ከመአቱ የተረፉት። "ለአርብ ጸሎት ከመጡት አርባ ሰዎች ወዲያው ነው ህይወታቸው ያለፈው። ሌሎች አርባ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል።"

በዚህ ሁሉ የጥይት ውርጂብኝ መካከል በዙሪያቸው የነበሩትን ሰዎች ህይወት የቀጠፈው ሞት እየቀረባቸው በመጣ ጊዜ አቶ አብዱልቃድ ከመጽሃፍ መደርደሪያው ስር ሆነው ይሰማቸው የነበረውን ሲያስታውሱ " በቃ ያው እየተገደልን መሆኑን ሳውቅ፤ ለካ ሰው እንደዚህ ነው የሚሞተው ብዬ አሰብኩ። አንዳንድ ጊዜ በዜና የምመለከተው ነገር እኔም ላይ እንደተፈጠረ ገባኝ" ይላሉ።

Image copyright Abdulkadir Ababora

ከሁሉ በላይ ግን የሁለት ሳምንት አራስ የሆነችው ባለቤታቸው እና ትመህርት ቤት ያሉት ሁለቱ ልጆቻቸው ደጋግመው በጭንቅላታቸው ይመላለሱ እንደነበር ገልጸው ምንም ማድረግ ስላልቻሉ "ትንፋሼን ዋጥ አድርጌ ወደ ጸሎት ገባሁ። ምክንያቱም እንደምሞት እርግጠኛ ነበርኩኝ።"

ተኩሱ አልቆመም ከአጠገባቸው በግራም በቀኝም የሞቱ ሰዎች በደም ተነክረው ወድቀው ይታያቸዋል፤ የተኩሱ ድምጽ መስጊዱን አሁንም እያናወጠው ነው። ስለዚህ ይህ እጣ እሳቸውንም እንደሚደርሳቸው እርግጠኛ ነበሩ።

ከጸሎቱ ጉን ለጎንም ወደሃገር ቤት ያስባሉ ስለእናታቸው፤ "እናቴም አለች፤ እሷንም አሰብኳት። እኔ ብቻ ነን የምረዳት፤ በቃ እንዴት ትሆናለች የሚልም ነገር አሰብኩኝ። ከሞት ጋር በተፋጠጥኩበት በመጨረሻው ደቂቃ ላይ" ይላሉ።

ታጣቂው መጀመሪያ ላይ መስጊዱ ውስጥ ተኩስ የከፈተው በያዘው አውቶማቲክ ጠመንጃ ሦስት ጊዜ ካርታውን እየቀየረ ነበር። ከዚያ በኋላ ደግሞ ከፊል አውቶማቲክ መሳሪያ አውጥቶ የተረፉትን መግደል ቀጠለ።

ከመስጊዱ አምልጠው እየሮጡ የነበሩት ላይ ሳይቀር "በመስኮት በኩል ወደ ውጪ ተኩሶ ይተኩስ ነበር። ከውስጥ ሁላችንንም ገድሎ የጨረሰ ሲመስለው ሮጦ ከመስጊዱ ወጣ። እሱ ወደ ውጪ ሲወጣ አርፍደው የሚመጡ የነበሩ ሌሎች ምዕመናንን አገኛቸው። እነሱንም እዛው መግቢያው ላይ ተኩሶ ገደላቸው።"

"የሠራዊቱ ሁኔታ ከፍተኛ የህሊና መረበሽ ውስጥ ከቶኛል" አቶ ነአምን ዘለቀ

አቶ አብዱልቃድር አባቦራ ሃምሳ የሚደርሱ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው ገዳይ በቅርብ እርቀት ሆነው መትረፋቸውን እንደተአምር ነው የሚመለከቱት።

በጥቃቱ ከሞቱት ባሻገር በርካቶች ቆስለዋል የሚያውቋቸው ሁለት ኢትዮጵያዊያንም ከባድ የመቁሰል ጉዳት እንደደተሰባቸው ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ላይ ናቸው።

በሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ላይ ስለደረሰው የጉዳት መጠንም ሲናገሩ "አንደኛው ጀርባው ላይ ነው የተመታው። ጥይቱ በሳምባው ውስጥ አልፎ፤ በትከሻው ወጥቷል። እሱ በጣም አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነበረ" የሚተነፍሰውም በህክምና መሳሪያ ድጋፍ እንደነበረና አሁን በራሱ መተንፈስ ጀምሮ የጤንነቱ ሁኔታ እየተሻሻለ ነው።" ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ደግሞ እግሩን ነው በጥይት የተመታው። ቀዶ ህክምና እንደተደረገለትና አሁንም ሆስፒታል እንደሆ ተናግረዋል።

ከጥቃቱ በኋላ አቶ አብዱልቃድር ቁጥሩን እንዴት አድርገው እንደመቱት ባያስታውሱም ቀድመው የደወሉት ወደ ባለቤታቸው ነበረ። በአጋጣሚም የሚያውቁት ታክሲ የሚነዳ ግለሰብና አግኝቷቸው ወደቤታቸው እንዳደረሳቸው ያስታውሳሉ።

ኒውዚላንድ ውስጥ እንዲህ አይነቱ ጥቃት ተፈጽሞ ስለማያውቅ ፖሊሶች ጥቃቱ የተፈጸመው በሃገሬው ተወላጅ ይሆናል ብለው ስላላሰቡ አቶ አብዱልቃድር እና ጥቂት በመስጊዱ ዙሪያ የነበሩ ሰዎች ለምርመራ ከፖሊሶች ጋር ቆይተው ነበር። "እኛን ለተወሰነ ጊዜ አቆይተውን ነበር።እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ድረስ እዛው ቆየን። ፎቶ አነሱን፤ ሙሉ መረጃችንን ወሰዱና ለቀቁን" ብለዋል።

የትኞቹ ሃገራት ከፍተኛ ስደተኛ አላቸው?

"ቤቴ ገብቼ ባለቤቴን ሳገኛት ምንም መናገር አልቻልኩም እንዲሁ ተቃቅፈን ማልቀስ ባቻ ነበር። እስከሚቀጥለው ቀን ድረስ አእምሮዬ ልክ አልነበረም። ይኸው እስካሁን ምንም እንቅልፍ አልተኛም። እስከዛሬ ድረስም ሥራ አልሄድኩም ሲሉ በጥቃቱ እለት ካሳለፉት ሰቆቃ እስካሁን መውጣት እንዳልቻሉ ይናገራሉ።

ይህንን አሰቃቂ ክስተት መርሳት ከባድ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ አብዱልቃድር በደም ተጨማልቁት ምንጣፎች የተሰባበሩት መስታወቶችና በሮች ደጋግመው በአይነ ህሊናቸው ይመላለሳሉ። "በዚህ ሳምንአርብ የት እንደምንሰገድ አላቀውቅም" ይላሉ።

ነገር ግን ከዚያ ሁሉ መአት በመትረፋቸው ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ። "እኔ አሁን አዲስ ህይወት እንደምኖር ነው የምቆጥረው። እንደገና እንደተወለደ ሰው ነው የምቆጥረው። በዚህ ዓለም ሁለተኛ ዕድል እንዳገኘሁ ነው የምቆጥረው።"ባለፈው አርብ መጋቢት 6/2011 ዓ.ም ኒውዚላንድ ክራይስትቸርች ከተማ ውስጥ በሚገኝ መስጊድ ውስጥ አንድ ታጣቂ የፈጸመው ጥቃት የ50 ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈ በኋላ ጉዳዩ እስከ ዛሬ ድረስ የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።