የገጠር አስተማሪው አንድ ሚሊዮን ዶላር አሸነፉ

መምህር ፒተር ሽልማታቸውን በዱባይ ተገኝተው በተቀበሉበት ወቅት Image copyright Varkey Foundation

በኬንያ በአንድ ገጠር ውስጥ ሳይንስ አስተማሪ የሆኑት ፒተር ታፒቺ የዓለም ምርጡ አስተማሪ ተብለው ወደ 30 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የገንዘብ ሽልማት አሸንፈዋል። መምህሩ ድሀ ተማሪዎችን ከደመወዛቸው በመቀነስ ጭምር ያግዙ ነበር።

መምህር ፒተር ታፒቺ የ2019 የዓለም የምርጥ አስተማሪነት ውድድርን ነው ያሸነፉት። ጥቂት መጻሕፍት ባሉበትና በተማሪዎች በተጨናነቁ ክፍሎች እያስተማሩ ተማሪዎቻቸው ለመርዳት ያሳዩት ትጋት ብልጫን አስገኝቶላቸዋል።

እኚህ መምህር ልዩ የሚያደርጋቸው ታዲያ የደመወዛቸውን 80 እጅ ለተቸገሩ በተለይም ወላጅ አልባ ለሆኑ ተማሪዎቻቸው የደንብ ልብስና መጽሐፍ መግዣ መስጠታቸው ነው።

ሴት ተመራቂዎች ለምን ሥራ አያገኙም?

መምህሩ ፕዋኒ መንደር፣ ናኩሩ አውራጃ በሚገኘው ከሪኮ ሚክስድ ዴይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበር የሚያስተምሩት።

ተማሪዎቻቸውንም «የወደፊቱ ተስፋ በሳይንስ ነው፤ ጊዜው የአፍሪካ ነው» በሚል ያበረታቱ ነበር።

የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ የተካሄደው በዱባይ ሲሆን ለዚህ ሽልማት ከ179 አገራት አስር ሺ የሚሆኑ መምህራን እጩ ነበሩ።

የመምህሩን ያልተጠበቀ ድል ተከትሎ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ኡሁሩ ኬንያታ የእንኳን ደስ ያለዎት መልእክትን አስተላልፈዋል።

'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ?

በእርግጥ የአብራሪዎቹ ስልጠና ከአደጋው ጋር ይያያዛል?

ተያያዥ ርዕሶች