የአሜሪካው ኩባንያ በኬንያ ካናቢስ ለማብቀል ፍቃድ አገኘ ተባለ

የካናቢስ ቅጠል Image copyright Eye Ubiquitous/Getty Images

አንድ የአሜሪካ ኩባንያ በኬንያ እጸፋርስ (ማሪዋና) አብቅዬ ለመሸጥ ፍቃድ አግኝቻለሁ አለ። "ማሪዋና ሕገወጥ በሆነባት ኬንያ ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል እያነጋገረ ነው" ሲል ቢዝነስ ዴይሊ የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል።

ይህ እርምጃ ኩባንያችንን ወደላቀ ደረጃ የሚወስድና በየዕለቱ እያበበ ያለውን የካናቢስ (እጸፋርስ) ቢዝነስ የሚያሳድግ ነው ብሏል ኩባንያው። የዚህ ኩባንያ የዓለም አቀፍ ንግድ ተጠሪ ሚስተር ሱቶን የኬንያ ባለሥልጣናትን አግኝተን በጉዳዩ ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።

"ጫትን ማገድ ፈፅሞ የሚቻል አይደለም" ዶ/ር ዘሪሁን መሃመድ

የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች

የኬንያ ባለሥልጣናት ግን በጭራሽ በዚህ ጉዳይ ላይ የምናውቀው ነገር የለም ብለዋል።

የኩባንያው ተጠሪ እንደሚሉት የሊዝ ስምምነቱ ለ25 ዓመታት የሚጸና ሲሆን ኬንያ በምድር ወገብ አካባቢ በመገኘቷ የአየር ሁኔታዋ ካናቢስ ለማብቀል እጅግ ምቹ ነው፤ ዓመቱን ሙሉ ምርት ይኖራል ብለዋል።

በአንዳንድ አሜሪካ ግዛቶችና በአውሮፓ ካናቢስን ሕጋዊ የማድረግ ሁኔታ የታየ ቢሆንም በአፍሪካ አገሮች ግን ይህ ሂደት አዝጋሚ ነው።

ደቡብ አፍሪካ ሕጓን በተወሰነ ደረጃ ያላላች ሲሆን ካናቢስን አዋቂዎች ገለል ባሉ ቦታዎች ቢጠቀሙ ችግር የለውም በሚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል።