አንዳንድ ጥያቄዎች ለ"108ኛው" የፖለቲካ ፓርቲ

የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አርማ

አዲስ ፓርቲ እየመጣ ነው። የምሥረታ ጉባኤው ጠቅላላ ጉባኤው ባለበት ተካሄደል። ኦዲትና ኮሚሽን ተመርጧል። የሥራ ድልድ ተደርጓል። ማዕከላዊ ኮሚቴና ሥራ አስፈጻሚ ተመርጧል። ከምርጫ ቦርድ ሠርተፍኬት ለመውሰድ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ለሚገኘው የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ መሥራችና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለወ/ሮ ነቢሃ መሐመድ አንዳንድ ጥያቄዎችን አንስተናል።

ቢቢሲ፡ እንደው 108ኛ ፓርቲ መሆን ምን ዓይነት ስሜት ይሰጣል? ያሳፍራል ወይስ . . .?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ሐሳብን በነጻነት መግለጽ እና የመደራጀት መብት ሀገሪቷ በሕገ መንግሥቱ ካጎናጸፈችን መብቶች አንዱና ዋንኛው ነው። ስለዚህ ዜጎች በርካታ ያልተፈቱላቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አሏቸው። ነጻነት አልተከበረም። ዜጋው በጠቅላላ እኩል ተጠቃሚ አይደለም።

"አጭሩ የሥልጣን ቆይታ የእኔ ነው" ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር)

ስለዚህ በእነዚህ ደረጃ ይሄንን ሊፈታ የሚችል የተደራጀ፣ ሁሉንም አካባቢ ያካተተ፣ በትምህርትም አጠቃላይ ክልሎችንም፣ ወረዳዎችንም፣ ቀበሌዎችንም፣ የጾታንም ስብጥር በጠበቀ፣ ወጣቱን ባካተተ...አገሪቱ ላይ የሚያወስፈልጋትን የነጻነት የፍትህ የእኩል ተጠቃሚነት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የተደራጀና የተጠናከረ አገራዊ ፓርቲ አለ ብለን በራሳችን በኩል ስለማናምን ያንን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አቅም አለን በሚል ነው [የመሠረትነው]።

ቢቢሲ፡ አሁን ያነሷቸው የነጻነት የእኩል ተጠቃሚነት ጉዳዮች እኮ 107ቱ ፓርቲዎችፕሮግራማቸው ላይ ያሉ ሐሳቦች ናቸው108ኛ መሆን ያስፈልጋል?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ በነገራችን ላይ በአብዛኛው 107 ፓርቲ እንበል እንጂ ዕውቅና የተሰጣቸው ፓርቲዎች 66ቱ ናቸው። የሁሉንም ብናይ ደግሞ በተወሰኑ አካባቢዎች የታጠሩ፣ ከተማ ላይ ብቻ የተወሰኑ፣ ወይንም ደግሞ የሆነን ብሔር መብት ለማስከበር የቆሙ ናቸው። ብዙዎቹ በአካባቢና በብሔረሰብ የተደራጁ ናቸው።

ቢቢሲ፡ ግን እኮ አገራዊ ፓርቲዎችም ብዙ አ?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ቁጥራቸው የተወሰኑ ናቸው።

ቢቢሲ፡ ሊሆን ይችላልግን አንሰዋል ይጨመር የሚያስብል አይደለም። ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ወደ ሁለት ስት ጠንካራ ፓርቲ ሰብሰብ ብላችሁ ገዢን ፓርቲ ብትገዳደሩ ይሻላል ባሉ ማግስት 108ኛ ፓርቲ ይዞ መምጣት ግን...

ወ/ሮ ነቢሃ፡ 108ኛ ፓርቲ ሆኖ አይደለም። አጠቃላይ 107 ከተመዘገቡት ውስጥ የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አለ። ምሥረታውን ነው ትናንትና ያካሄድነው እንጂ ከተመዘገቡት 107 ውስጥ 99ኛው የእኛ ነው። ያንን ማጣራት ትችላለህ።

ቢቢሲ፡ ግዴለም ተራ ቁጥር አያጣላንም። ነጥቡ አሁን ለምን ፓርቲ መመሥረት አስፈለገ ነው?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ አስፈላጊነቱ አገራችን ከገጠሟት ወቅታዊም ሆኑ የረዥም ጊዜ ችግሮች ለመላቀቅ የሁሉም ዜጎች የተናጠልና የጋራ ርብርብ ይጠይቃል። ከዚህ ውስጥ በዋናነት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ኃይሎች ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው የሚሆነው።

ቢቢሲ፡ ግን አሁን የፓርቲ እጥረት ኖሮ ነው እንዴ አገሪቱ እዚህ ችግር ውስጥ ያለችው? በፓርቲ ብዛት ችግር ይፈታል?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ፓርቲዎች መብዛታቸው ማነሳቸው ሳይሆን፤ ዋናው ሥራቸው ነው። አዲስ የተደራጁት ፓርቲዎች ቀርቶ አገሪቱን እየመራ ያለው ፓርቲ እንኳን የአገሪቱን ሕዝብ እኩል ተጠቃሚ እያደረገ አይደለም። ሁሉንም ክልሎች ሁሉንም ዜጎች እኩል ተጠቃሚ እያደረገ ስላይደለ የግድ ይሄ ፓርቲ መደራጀቱ ያስፈልጋል። ስለሆነም ይህ ፓርቲ የራሱ የሆነ የፖለቲካ ፕሮግራም ቀርጾ የራሱን የፖሊሲ ፕሮግራም ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ነው።

ቢቢሲ፡ በሌሎች ፓርቲዎች ቸል ተባሉ፣ ያልተካተቱ ነገር ግን የናንተ ፓርቲ በፖለቲካ ፕሮግራም የያዘው አንድ ጉዳይንይንገሩኝ እስኪ። ይሄ ልዩ የሚያደርገን ፕሮግራም ነው የምትሉት...

ወ/ሮ ነቢሃ፡ እኛ ከፖለቲካ ፕሮግራማችን ውስጥ የመንግሥት አወቃቀር፣ የሥርዓተ መንግሥቱ ቅርጽ፣ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለማችንን በደንብ አርገን አሁን ካሉት ፓርቲዎች በተለየ ሁኔታ ተንተን አድርገን ያስቀመጥንበት ሁኔታ አለ።

"የሠራዊቱ ሁኔታ ከፍተኛ የህሊና መረበሽ ውስጥ ከቶኛል" አቶ ነአምን ዘለቀ

ቢቢሲ፡ አሁን ያሉት ፓርቲዎች ተንተን አላደረጉትም?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ተንተን ሊያደርጉት ይችላሉ። ግን ደግሞ ማለት ነው። ይሄ ለይስሙላ የሚቋቋመ ፓርቲ አይደለም።

ቢቢሲ፡ ሌሎች ፓርቲዎች ለይስሙላ ነው የተቋቋሙት?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ለምሳሌ አሁን እየመራ ያለውን ፓርቲ እያየን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው። [ለማንናውም] እኛ የራሳችንን አቋም ነው አስቀምጠን፣ ፖለቲካችን ይሄን ይሄን ይመስላል ብለን አስቀምጠን፣ አገሪቷን ካለችበት ድህነትና ኋላ ቀርነት [ለማውጣት] አንዱ የበላይ አንዱ የበታች ከሚሆንበትን ሁኔታ ለማላቀቅ ነው፤ የምንሠራው የምንታገለው።

ቢቢሲ፡ ግን'ኮ ማንኛውም ፓርቲ ስለ እኩልነትና ስለ ነጻነት እንጂ ጭቆና ለማምጣት አይራም። በአደረጃጀት ደግሞ አገር አቀፍ ፓርቲዎች ይኖራሉ። ብሔር ተኮር ፓርቲዎች ይኖራሉ። እነዚህ ሁሉ ባሉበት አገር፣ በስም እንኳ የማናውቃቸው ፓርቲዎች ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ተጨማሪ ፓርቲ ይዞ መምጣት እንዴት ነው የሕዝብ ተቀባይነት ያስገኛል ብላችሁ ያሰባችሁት?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ በስም የማናውቃቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ ብለህ ስትል በስም የማታውቃቸው ፓርቲዎች ጭምር እንዳሉ እየገለጽክ ነው። ይህ የእኛን ፓርቲ ግን እያወቅከው ነው። ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በስም የሚታወቅ ነው። ሕገ መንግስቱ ደግሞ አትደራጁ ብሎ የሚያግድ የለም። 107 ፓርቲ በቂ ነው አይልም። [ፓርቲ አትመስርቱ] በቃ ብሎ የሚከለክለን የለም።

ቢቢሲ፡ መደራጀቱን ጥያቄ ውስጥ አልከተትኩም'ኮ። ፋይዳው ላይ ነው ጥያቄዬ

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ፋይዳውን ነበር እኮ እኔም እየነገርኩህ የነበረው።

ቢቢሲ፡ እስኪ በዚህ በዚህ ምክንያት ፓርቲዎች ይህንን ለሕዝብ ማድረስ ስላልቻሉ፤ ይህንን ክፍተት እንሸፍናለን ብላችሁ የምታነሱት የተለየ ነገር አለ?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ለምሳሌ የእኛ የፖለቲካ ርዕዮት ዓለም ከሌሎች ይለየናል ብለን የምንለው "ኮንሰርቫቲቭ ሊበራሊዝም" እናራምዳለን ብለን ነው የያዝነው፤ በዋናነት።

ቢቢሲ፡ ምን ማለት ነው እሱ?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ቅይጥ ሊበራሊዝም ማለት ነው።

"በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም" ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ

ቢቢሲ፡ ምንድነው እሱ በቀላል ቋንቋ ያስረዱን እስኪ?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ አሁን በኢኮኖሚ ዘርፍ ያሉትን ጉዳዮች መንግሥት በበላይነት ነው እየመራ ያለው። በዓለም ደረጃ መንግሥት በበላይነት የሚመራበት ሁኔታ አይደለም ያለው። በግለሰብም በቡድንም በጋራም ሆኖ አቅም ያላቸው መሥራት የሚችሉ ማንኛውንም አካል አካታች አድርጎ በኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሳይኖር እንዲሠሩት የማድረግ ሂደት ነው በዋናነት።

ቢቢሲ፡ ስለዚህ የምትከተሉት ቅይ ሊበራሊዝያሉኝ ይህንንነው ማለት ነው?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ አዎ ግዙፍ የሆኑ ፕሮጀክቶች ሊኖሩ ይችላሉ። በግሉ ሊሠሩ የማይችሉ ካሉ እነሱን መንግሥት ይሠራል። በተጨማሪ ደግሞ ጥቅማቸው ጥቃቅን የሆኑ ነገሮች ላይ መንግሥት ሊሠራበት ይችላል። አብዛኛውን ግን ለግሉ ወይም በጋራ ለሚሠሩት የሚሰጥ ነው እንጂ እራሱ ሙሉ በሙሉ እየገባበት የሚያንቀሳቅሰው አይደለም።

ቢቢሲ፡ ስለዚህ በኢኮኖሚ ውስጥ የመንግት እጅ ረዝሟል የሚል ቁጭት ነው ይህን ፓርቲ የፈጠረው?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ አንድም እሱ ነው። ሁለት ደግሞ ያልተሰሙ ድምጾች አሉ። የማን ከተባለ የዜጋው። እስከዛሬ የምናየው ነገር በገዢው ፓርቲ እየተመራ ያለው፤ አንድ አካባቢ የሆነ ሰው ብቻ ነው ተጠቃሚ እየሆነ ያለው። አገሪቷን እየመራ ያለውም ይኸው የአንድ አካባቢ ሰው ነው።

ቢቢሲ፡ ይሄ አየተጠቀመ ነው የሚሉትን የአንድአካባቢ ሕዝብ መጥቀስ ይቻላል?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ የፖለቲካ መሪዎች፣ የፓርቲ መሪዎች ናቸው እየተጠቀሙ ያሉት። ሕዝቡን እየጠቀሙ አይደለም። የአንድ የፖለቲካ መሪ የበላይ ሆኖ ነው ያለው። ስለዚህ እኛ የሁሉም ክልሎች ሕዝብ ተወካይ አገሪቷን እየመራ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ነገር መመንጨት ያለበት ከሕዝብ ነው [ብለን እናምናለን]። እኔ አውቅልኸለሁ ከማለት ከሕዝብ መምጣት አለበት ብለን እናምናለን።

ሲቀጥል ደግሞ ሥርዓተ መንግሥቱ በርዕሰ ብሔር የሚመራ፣ ቀጥታ በሕዝብ የሚመረጥ መሆን አለበት። ይሄን በተመለከተ የራሳችን የፖለቲካ ፕሮግራም አለን።

Image copyright Nebiha

ቢቢሲ፡ በቀጥታ ፕሬዚዳንት መምረጥ ምን ለውጥ ያመጣል?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ አንድ አገር ሲመራ የራሱ የሆነ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ይኖሩታል። ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መመንጨት ያለባቸው ከሕዝብ ነው። እኔ አውቅልኸለሁ ብዬ ፖሊሲ መቅረጽ የለብኝም። የሚመለከተውን አካል ማሳተፍ አለብኝ።

ኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጥሮ 86 የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች አሏት፤ የተለያየ እምነትና ባህል ያለበት አገር ነው። ስለዚህ እኔ እላይ ቁጭ ብዬ ታች ላለው ለጋምቤላው ለሶማሌው አውቅልኸለው ብዬ ልሠራለት አይገባም። አሳታፊ ሊሆን ይገባል።

ቢቢሲ፡ ግን እኮ በመንግሥት ሥርዓት ውስጥ አሳታፊነት በተለያየ መንገድ ሊገለጽና ሊወከል ይችላል። የሕዝብ ድምጽ በእንደራሴዎች ሊወከል የሚችበት አሰራርም አንዱ ነው

ወ/ሮ ነቢሃ፡ በሕዝብ ነው ምርጫ የሚደረገው እንጂ ፓርቲዎች ተሰባስበው መሆን የለበትም። የኢህአዴግን አወቃቀር አይተነዋል እኮ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአራቱም ብሔራዊ ድርጅቶች የበላይ የሆነው አንዱ በድምጽ ብልጫ ተወሰኖ ነው መሪ እንዲቀመጥ የሚደረገው እንጂ ከታች ሕዝቡ መርጦት አይደለም። ቀጥታ ከሕዝብ በኮሮጆ የሚመረጥ ነው መሆን ያለበት እንጂ አራት ፓርቲዎች የሚመርጡት መሆን የለበትም።

ቢቢሲ፡ ምን ያህል ሰዎች ፈረሙላችሁ?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ የ1ሺህ 500 ሰው የፊርማ ናሙና ከተሰበሰበ ያ የመጨረሻው ደረጃ ነው። እኛ ግን ከ2500 በላይ ፊርማ የማሰባሰብ ሥራ ሠርተናል፤ ከሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች።

ቢቢሲ፡ ሰዎች ምን ይሏችሁ ነበር ፊርማ ስትጠይቋቸው?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ምንድነው የተለየ ፕሮግራም ያላችሁ? የኢኮኖሚ ፕሮግራማችሁ ምንድነው ይሉን ነበር።

ቢቢሲ፡ በዚህ ሰዓት ፓርቲ ልንመሠርት ነው ስትሏቸው ደስተኞች ናቸው?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ በጣም ደስተኞች ናቸው። እጅግ በጣም። አይደለም ከዛሬ 2 እና 3 ወር ይቅርና ትናንትና [እሑድ] የምስረታ ጉባኤውን ስናካሄድ በሚዲያ የተከታተሉ ሰዎች ይሄን ፓርቲ ዓላማውን በደንብ አሳውቁን በጣም ደስ ይላል ብለውናል፤ ከወዲሁ። ነጻነትና እኩልነት የሚለውን ሲሰሙ...

ቢቢሲ፡ ፓርቲዎች ይመሠረታሉ፣ ልንሀድ ነው ይላሉይፈርሳሉ ወይ ይሰነጠቃሉ፣ ይከስማሉ... ይሄ ነው ሕዝቡ ስለ ፓርቲዎች ያለው መረጃ። እንዴት ነው በናንተ ሊደሰት የሚችለው? በስማችሁ ድምቀት ነው? ወይስ ሕዝቡ የፓርቲ ጥማቱን አልተወጣም ብላችሁ ነው የምታስቡት?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ የፓርቲ ጥማት ሳይሆን ትክክለኛ ምላሽ ሊሰጠው የሚችለውን ፓርቲ ከወዲሁ ፕሮግራሙ የያዘውን አይቶ ማወቅ ይፈልጋል። ፓርቲዎች ብዙ አሉ ግን ምንድነው ፕሮግራማቸው? ምንድነው ርዕዮተ ዓለማቸው? ምንድነው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው? የእኛ ይሄን ከመረዳት...

ቢቢሲ፡ ሕዝብ ርዕዮተ ለማችንተረድቶ ነው ከወዲሁ የወደደን እያሉኝ ነው?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ያናገርናቸው ፕሮግራሙን ያስተዋወቅናቸው ሰዎች በጣም ደስተኞች ናቸው። በርዕዮተ ዓለማችን፣ በፕሮግራማችን። እንዲፈርሙልን አባል እንዲሆኑልን የጠየቅናቸው ሰዎች ማለቴ ነው፤ በጣም ደስተኞች ናቸው።

ቢቢሲ፡ ይሄንን ፓርቲ ለመመረት ሐሳቡን ያመነጨው ማን ነው?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይል አሁንም እየሠራ ያለ፣ ትናንትናም በተሰጠው የምስጢር ድምጽ አሰጣጥ በአጋጣሚ ሆኖ የፓርቲው ሊቀመንበር የኾነው ዶ/ር አብዱልቃድር ይባላል።

ቢቢሲ፡ የፓርቲው መሪዎች እነማን ናቸው? ከዚህ በፊት ፓርቲ ፖለቲካ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ናቸው? ወይስ ሁላችሁም አዲስ ናችሁ?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ በነገራችን ላይ ከዚህ በፊት በተለያየ ፓርቲ ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦች አብረውን አሉ። ከዚህ በፊት በነበሩ ፓርቲዎች አባል ሆነው፣ መሥራችም ሆነው ነገር ግን እዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተገኙ አሉ። የራሳቸውን ተሞክሮ እንዲሰጡ የተደረገበት ሁኔታ አለ። በአብዛኛው የተማረ ነው ምሁሮች ናቸው ያሉት፤ ወጣትም አለበት።

ቢቢሲ፡ እነዚህ ሌላ ፓርቲ ውስጥ የነበሩት ከዚያ ወጥእናነት ጋ አመራር ሆኑ ማለት ነው?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ልምድ ያላቸው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነው የሆኑት።

ቢቢሲ፡ ስለዚህ ከፓርቲ ፓርቲ የሚዘዋወሩ ሰዎች ናቸው የሚመሩት ፓርቲያችሁን?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ልምድ ሊሰጡን አንድ ሁለት ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የገቡ አሉ እንጂ አብዛኛው ወጣት ነው።

ቢቢሲ፡ ለልምድ ሲባል ነው እነሱ የገቡት?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ እነሱ ልምድ በሚል ነው እንጂ የገቡት ፓርቲው ውስጥ ያሉ ወጣቶች የተለያየ ዕውቀት ያላቸው፣ የፖለቲካ ልምድ ያላቸው፣ በጣም የተማሩ፣ አቅም ያላቸው ዶክተሮች፣ የፖለቲካ ልምድ ያላቸው ሰዎች ናቸው ያሉበት ፓርቲው ውስጥ። እና በዛ ላይ ከሁሉም አካባቢ የተውጣጣ ነው። ከጋምቤላ አለ፣ ከአፋር አለ፣ ከሐረር፣ ከሶማሌ ከደቡብ ከአማራም አካባቢ አለ፤ ከትግራይም አለ። ሁሉንም የአገሪቱን ህብረተሰብ ያካተተ ነው ስብጥሩ።

ቢቢሲ፡ ስለዚህ ሁሉንም ብሔር ብሔረሶች ተወክለዋል ነው የሚሉት በሥራ አስፈጻሚው?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው ያልኩት። ሥራ አስፈጻሚማ 11 ነው ቁጥሩ።

ቢቢሲ፡ ጠቅላላ ጉባኤ ስንት ናችሁ?

ወ/ሮ ነቢ150 አባላት

ቢቢሲ፡ ስለዚህ ሁሉም ብሔረሰቦች ተወክለዋላ?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ይህ አገር አቀፍ ፓርቲ ነው። ሁሉም አካባቢ መሥራት አለብን በሚለው እሳቤ አንደኛ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ነው። ፍላጎትን መሠረት አድርገን ስንሄድ ግን ደግሞ ሁሉንም የአገሪቷን አካባቢዎች ማካተት አለበት በሚል ከሁሉም በፍቃደኝነት፣ በሞራል፣ በተነሳሽነት፣ በአቅምም፣ ጾታንም ጭምር ታሳቢ ያደረገ [እንዲሆን ተደርጓል]። ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ሴቶች ፓርቲው ውስጥ ገብተዋል።

ቢቢሲ፡ ብሔር ብሔረሰቦች ግን ሁሉም ተወክለዋል?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ አዎ ያልተወከለ የለም።

ቢቢሲ፡ እንግዲያውስ አንድ ጥያቄ ላንሳ። ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ከተወከሉ ለመሆኑ የኢትዮ ብሔር ብሔረሰቦች ስንት ናቸው? ብዙውን ጊዜ በደፈናው ከ85 በላይ ናቸው ስለሚባል ነው...

ወ/ሮ ነቢሃ፡ እ...ውክልና ሲባል ከሁሉም አካባቢ የተውጣጣ ነው እንጂ ለምሳሌ ኦሮሚያ ቁጥሩ ከፍተኛ ነው፤ ከአገሪቷ ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛል። እኛ ከሁሉም አካባቢ ወስደናል፣ ለሳምፕል የሚሆን ሰው ወስደናል። ሊሰራልን የሚችል ከሁሉም ብሔሮች...

ቢቢሲ፡ ለናሙና ነው የወሰዳችሁት?

ወ/ሮ ነቢ መሐመድመሥራት የሚችሉ አቅም ያላቸውን ወስደናል። እዚህ አዲስ አበባን ማዕከል አድርገን እዚህ ቁጭ ብለን ስለ አገሪቷ እናውቅልሀለን ማለት አንችልም።አንተ የምትለኝን ልናደርግ የምንችለው መንግሥት ስንመሠርት ነው።

ቢቢሲ፡ ናንተ የመሥራቾቹ ገቢ ወይም መተዳደሪያ ምንድነው?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ ሁላችንም በየራሳችንን የምንቀሳቀስ ነን። የግል ቢዝነስ የሚሠራ አለ፣ የመንግሥት ሠራተኛም አለ፣ ሥራ የሌለውም አለ። አብዛኛው ግን አቅም ያለው ነው፤ መንግሥት ቢሮም ተቀጥረው የሚሠሩ አሉ።

ቢቢሲ፡ እንጂ ፓርቲን እንደ አንድ የገቢ ምንጭ በማሰብ ሕዝብንም በዚያው እያገዙ ኑሮን ለመደጎም የተሰባሰበ አይደለም?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ በፍጹም። በፍጹም።

ቢቢሲ፡ መጪውን ምርጫ አሸንፋችሁ መንግሥት የምትመሰርቱ ይመስላችኋል?

ወ/ሮ ነቢሃ፡ በሚገባ! እርግጠኝነት።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ