የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ስለ ንግድ ባንክ እርዳታ ምን ይላሉ?

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች

በአማራ ክልል የሚገኙ ከ90 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።

በዚሁ መሰረት ተቋማትና ግለሰቦች እጃቸውን እየዘረጉ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች በተለያየ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ይሆን ዘንድ ገንዘብ ለግሷል።

ንግድ ባንክ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ የመደበው መቶ ሚሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች የመደበው 4.789 ሚሊዮን ብር ሲሆን የክልሉ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ይህን እርዳታ አልቀበልም ማለቱ ብዙ አስብሏል፤ ብዙዎችንም አነጋግሯል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ለችግር ተዳረግን አሉ

ለተፈናቃዮች የሚውል የእርዳታና የድጋፍ ያለህ እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት እንዴት እርዳታ አያስፈልገኝም ይባላል? ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው እርዳታውን እንደማይቀበል ማሳወቁን ተከትሎ ብዙዎች ያነሱት ጥያቄ ነው።

የክልሉ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር "ምክንያታችን ለንግድ ባንክ ካለን ክብር የመነጨ ምላሽ ነው የሰጠነው" ይላሉ። ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የድጋፍ ጥያቄ አቅርበን ነበር የሚሉት ሰብሳቢው ንግድ ባንክ በመላ አገሪቱ ያሉ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ እንደሚፈልግ እንደገለፀላቸው ያነሳሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ከተለያዩ ባንኮች ከ5 ሚሊዮን ብር ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ተቀብለዋል። ይሁን እንጂ ከንግድ ባንክ ያገኙት የድጋፍ ክፍፍል የችግር መጠን ያላገናዘበና ከሚፈለገው በታች ሆኖ ስላገኙት ድጋፉን ላለመቀበል መወሰናቸውን ይናገራሉ።

"የድጋፍ አሰጣጡ ቀመር ስላልገባን ይህንን ድጋፍ ተቀብለን የንግድ ባንክን ክብር ከምንነካ፣ ይህ ዝቅተኛ ድጋፍ ለአማራ ህዝብ የሚመጥን ባለመሆኑ አለመቀበል ይሻላል" በሚል ከውሳኔው ላይ እንደደረሱ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት

ንግድ ባንክ እርዳታውን የበጀተበትን ቀመር አለማወቅ ብቻም ሳይሆን ቀመር መስራትም አያስፈልገው ነበር ሲሉ ይከራከራሉ አቶ አገኘሁ።

እሳቸው እንደሚሉት ንግድ ባንክ ማድረግ የነበረበት የመደበውን የእርዳታ ገንዘብ ለዚሁ ዓላማ በመንግሥት ለተቋቋመው ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በመስጠት ኮሚሽኑ በተፈናቃይ ልክና በጉዳት መጠን ለክልሎች እንዲያከፋፍል መተው ነበር።

ያነጋገርናቸው በአማራ ክልል ጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ አንዳንድ ተፈናቃዮች በበኩላቸው ያገኙትን ድጋፍ ይዘው ወደ ቀያቸው የመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ከመሆኑ አንፃር ይህን የንግድ ባንክ ድጋፍ አልቀበልም ማለት ትክክል እንዳልሆነ ገልፀውልናል።

"ይህ ነገር ስህተት ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ሰዎች አደጋ ላይ ነው ያሉት። ለምሳሌ እንደ ግራር አውራጃ ብዙ ሰዎች ቤታቸው ተቃጥሏል፣ ንብረታቸው ወድሟል፣ አምስትም አስር ብርም ቢደርሳቸው ለእነሱ ጥቅም ነው ብዬ ነው የማስበው" ስትል ሳሮን ባይሳ የተባለች ተፈናቃይ ለቢቢሲ ተናግራለች።

ቻይና 300 የኤርባስ አውሮፕላኖችን ልትገዛ ነው

ይህ ውሳኔ ያለምክንያት እንዳልሆነ የሚገምቱ ተፈናቃዮችም ያሉ ሲሆን የዚህ አይነት ስሜት ካላቸው ሌላኛው ተፈናቃይ አንዱዓለም ነበይ "መቼም ከውስጡ የሆነ ነገር ይኖረዋል እንጂ ህብረተሰቡ በችግር ላይ ነው ያለው፤ እርዳታው ተፈላጊ ነው" ብለውናል።

በክልሉ ነፍሰጡር እናቶች፣ ህፃናትና አዛውንት ተፈናቃዮች ከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ቢቢሲ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በርካታ ተፈናቃዮች በሚገኙበት በአይምባ መጠለያ ተገኝቶ ዘገባ ሰርቶ ነበር።

የአሜሪካው ኩባንያ በኬንያ ካናቢስ ለማብቀል ፍቃድ አገኘ ተባለ

በክልሉ ተፈናቃዮች ያሉበትን ፈታኝ ሁኔታ በመገንዘብ እርዳታውን አልቀበልም ያለው የድጋፍ አሰባሳቢው ኮሚቴ ላይ 'ኩራት ወይስ ዳቦ ?' የሚል ጠንካራ ትችት የሰነዘሩም እንዳሉ ያነሳንላቸው የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አገኘሁም የዚህ አይነቱ ሃሳብ "የፅንፈኞችና ለአማራ ክልል ህዝብ ንቀት ያላቸው ሰዎች ሃሳብ ነው" በማለት ጠንከር ያለ ምላሽ ይሰጣሉ።

"የአማራ ህዝብ አይኮራም፤ ኮርቶም አያውቅም። ከኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በእኩልነት የሚያምን ህዝብ ነው" ይላሉ።

የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴውን መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰጠው ምላሽ እንደሌለ አቶ አገኘሁ ጨምረው ተናግረዋል።

ተያያዥ ርዕሶች