የኢትዮጵያዊያን እርጅና በስንት ዓመት ነው የሚጀምረው?

የእድሜ ባለጸጋ እናት Image copyright Getty Images

ፓፓ ኒው ጊኒ በተባለችው ሃገር የሚኖር አንድ የ45 ዓመት ጎልማሳ ፈረንሳይ ወይም ሲንጋፖር ውስጥ ካለ የ76 ዓመት ሽማግሌ ጋር ተመሳሳይ የእርጅና ስሜትና ድካም ያጋጥመዋል።

ከዓለም የዕድሜና የእርጅና ደረጃ ጋር ሲወዳደር ደግሞ ይህ ግለሰብ በአማካይ የ65 ዓመት ሰው ሊሰሙት የሚገቡ ስሜቶችን ነው የሚያስተናግደው።

ይህ ውጤት የተገኘው በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ያካተተ የጥናት ቡድን ባሳተመው የምርምር ውጤት ላይ ነው።

ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት

የምግብ ምርጫዎ ስለማንነትዎ ይናገራል?

ተመራማሪዎቹ ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ የ195 ሃገራት መረጃዎችን ያሰባሰቡ ሲሆን አንድ ሰው በአማካይ 65 ዓመት ሲሞላው እርጅና ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራል ይላሉ።

በጥናቱ መሠረትም ከእርጅና ጋር ተያይዘው የሚመጡ የልብ ህመም፣ የመስማት ችግር፣ ከመውደቅ ጋር ተያይዝው የሚመጡ ጉዳቶችና አጠቃላይ የጤና እክሎች የማጋጠም እድላቸው እንደምንኖርበት ሃገርና አካባቢ ይወሰናል።

ስለዚህ በትክክል በሚያረጁና ያለ ዕድሜያቸው በሚያረጁ ሰዎች መካከል እስከ 30 ዓመት የሚሆን ልዩነት ሊፈጠር ይችላል ይላል ጥናቱ።

ጥናቱ ከዚህ በተጨማሪ እርጅናን ከዕድሜ ጋር ብቻ ሳይሆን ከአጠቃላይ ጤንነት አንጻርም ተመልክቶታል። ይህ ደግሞ ከእርጅና ጋር ተያይዘው ከሚመጡ በሽታዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው።

በጥናቱ ዋና ተሳታፊ የነበሩት ዶክተር አንጌላ ዋይ ቻንግ እንደሚሉት ረጅም ዕድሜ መኖር ጥሩ አጋጣሚ የመሆኑን ያክል ይዞት የሚመጣው አደጋም አለ።

''በተለይ ደግሞ ባላደጉት ሃገራት የሚኖሩና ያልተመቻቸ ሕይወት ያላቸው በዕድሜ የገፉ ሰዎች ከራሳቸው አልፈው ለአጠቃላዩ ኅብረተሰብ አስጊ በሽታዎችን ይዘው ሊመጡ ይችላሉ።''

የዓለማችን ውድ እና ርካሽ ከተሞች ይፋ ሆኑ

ተመራማሪዎቹ የሰውን ልጅ አካላዊና አእምሯዊ አሠራር የሚያውኩ 92 ችግሮችን ለይተው ያስቀመጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ደግሞ ካንሰርና ከልብ ጋር የተያያዙ በሽታዎች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ ብለዋል።

በጥናቱ ላይ የእርጅና ስሌቶቹ የሚሠሩት ማኅበራዊ ጉዳዮችንና የሕዝብ ብዛትን ባማከለ መልኩ ሲሆን ለእያንዳንዱ ሃገር የተለያየ መለኪያ አስፈልጎ ነበር።

በዚህም መሠረት አጠቃላይ የገቢ ደረጃ፣ የትምህርት ደረጃና አማካይ የተዋልዶ ምጣኔም ቢሆን ከግምት ውስጥ ገብተዋል። እነዚህ ማሳያዎችን ከግምት ውስጥ አስገብቶ የተሠራው ጥናቱ እንደሚለው የእርጅናን ከባድ ምልክቶች ቶሎ ማስተዋል የሚጀምሩት በማደግ ላይ ባሉና ባላደጉ ሃገራት የሚኖሩ ዜጎች ናቸው።

የሃገራት ደረጃ ምን ይመስላል

በዚህ ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ ከዓለም ሀገራት ጋር ስትነጻጸር ሰዎች ያለዕድሜያቸው አያረጁም። እንደውም ከፍተኛ ከሚባሉት ሃገራት ተርታ ነው የምትመደበው።

የጥናት ዕትሙ ያካተታቸው ከዕድሜ ጋር የሚያያዙ የጤና እክሎች በዓለም ላይ ካሉ ሰዎችን ከሚገድሉ በሽታዎች ግምሹን ይይዛሉ።

ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን?

እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል?

ከዕድሜ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ሁሌም ቢሆን ያለ ጊዜ ጡረታ መውጣትን ስለሚያስከትሉ የሃገራት ሠራተኛ ኃይል ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራሉ። ይህ ደግሞ ለከፍተኛ የጤና አገልግሎት ወጪና አላስፈላጊ ብክነት ይዳርጋል።

ስለዚህ የሃገራት መሪዎችና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የእርጅና አሉታዊ ተጽእኖዎችን ለመቀነስ የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ አለባቸው ይላል ጥናቱ።

ተመራማሪዎቹ የእርጅና ምልከቶችን ከተቻለ ማስቀረት አልያም ዘግይተው እንዲመጡ የሚያስችሉ መንገዶችን ወደ ማፈላለጉ ፊታቸውን አዙረዋል።

መደረግ አለባቸው ብለው ካስቀመጧቸው ነገሮች መካከል ደግሞ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ እንደ ሲጋራ ያሉ ሱሶችን ማስወገድና የተደራጅ የህክምና አገልግሎት መፍጠር ይገኙባቸዋል።

ተያያዥ ርዕሶች