አሥመራ፡ ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ

Image copyright Milena Belloni

ጦርነትና ከዓለም መድረክ መነጠልን ጨምሮ በሌሎችም በርካታ ምክንያቶች ታስቦባቸው ባይሆንም ኤርትራን ለብስክሌትና ለብስክሌተኞች ምቹ ስፍራ እንድትሆን አድርጓታል።

አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ

ጉዞ ከአዲስ አበባ ወደ አሥመራ በፎቶ

አሥመራ 500 ሺህ ብቻ ነዋሪዎች ሲኖሯት ዝቅተኛ ደሞዝ፣ ከፍተኛ ቀረጥና የነዳጅ እጥረት ከተማዋ ትንሽ ተሽከርካሪ እንዲኖራት ምክንያት ናቸው። ብዙ ጊዜ የሚታዩት ሰዎችም በተለየ የእድሜ ክልል ውስጥ ናቸው።

ብስክሌት የሚጋልብ ሰው Image copyright Milena Belloni
በአህያ የሚጎተት ጋሪ በአሥመራ Image copyright Milena Belloni

የአሥመራ መንገዶች በአንፃራዊነት ከመኪና ብቻ አይደለም ነፃ የሆኑት። ሃገሪቱ ዜጎች እንደሚሉት ኤርትራዊያን ባለፉት 20 ዓመታት አካባቢያዊ ግጭት በፈጠረው ጫናና የግዳጅ ብሔራዊ አገልግሎትን ሸሽተው በርካታ ወጣቶች ሃገራቸውን ጥለው ተሰደዋል።

ነጻነት ጎዳና፤ አሥመራ

አሥመራ በተለያዩ ምክንያቶች በመኪና ከተጨናነቁ ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች የተለየ መልክ አላት። ይህ አስገራሚ ከሆነው የከተማዋ አየር ንብረት ጋር ተጨምሮ ብስክሌተኞች በከተማዋ እንዲያንዣብቡ ድንቅ ስፍራ ሆናለች። የ25 ዓመቱ ወጣትም "ብስክሌት መጋለብ አንዱ ባህላችን ሆኗል" በማለት ይገልፃል።

ብስክሌት የሚጋልብ ሰው Image copyright Milena Belloni

የአሥመራ የኪነ ሕንፃ ስብስብም በቅርብ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን እ.አ.አ. ከ1897 እስከ 1943 የቆየው የጣልያን ቅኝ ግዛት ትሩፋቶች ነው።

የአሥመራ ጎዳና Image copyright Milena Belloni

የብስክሌት መጠገኛ ሱቆች አሥመራ ውስጥ በስፋት ይገኛሉ። ከ30 ዓመታት ጦርነት በኋላ ከኢትዮጵያ ተነጥላ ሉዓላዊት ሃገር የሆነችው ኤርትራ ከነጻነት በኋላ በገጠማት ከዓለም አቀፍ ግንኙነት መገለል ምክንያት ብስክሌትም ሆነ የመለዋወጫ አካላትን ወደ ሃገሪቷ ማስገባት እጅግ በጣም ውድ እንዲሆን አድርጎታል።

የብስክሌት መጠገኛ ሱቅ Image copyright Milena Belloni

ኤርትራዊያን በቀለምም ሆነ በዓይነታቸው የተለያዩ ዓይነት ብስክሌቶችን ይነዳሉ። የተራራ ብስክሌቶች፣ የከተማ ብስክሌቶችና የውድድር ብስክሌቶች ይጠቀሳሉ። ኤርትራዊያን ከህፃን እስከ አዋቂ፣ ሴቶችና ወንዶች፣ አትሌቶችና የቤት እመቤቶች ሁሉም ብስክሌትን ተላምደዋል።

ብስክሌት የሚጋልብ ሰውና የብስክሌት መጠገኛ ሱቅ Image copyright Milena Belloni
Presentational white space

የህዝብ አውቶብስ የሚጠቀሙ ነዋሪዎች ከመጠን በላይ የተጨናነቀው አውቶብስ ላይ ከመግባታቸው በፊት ለረጅም ሰዓታት ቆመው መጠበቅ አለባቸው። "አውቶብሶች በጣም ጥቂትና ያገጁ ናቸው። በአስመራ ብስክሌት ህይወትን ነው የሚያድነው" ትላለች የ30 ዓመቷ ሰላም።

የአውቶብስ ጣቢያና ነጋዴዎች Image copyright Milena Belloni

መንግሥት የአካባቢ ጥበቃን ለረጅም ጊዜ ሲቀሰቅስ ቆይቷል። የፕላስቲክ ምርትንና አጠቃቀምን መቀነስ፣ ደንን ማልማት፣ የሃገሪቷን አረንጓዴ ቦታዎች መንከባከብና የቻይናና የዱባይ ብስክሌቶችን መጠቀም ከወሰዳቸው አንዳንድ እርምጃዎች መካከል ናቸው።

ብስክሌቶችና የአሥመራ ነዋሪዎች Image copyright Milena Belloni

ለብዙ ኤርትራዊያን መኪኖች ቢኖሩ እንኳን እንደ ብስክሌት ዋጋ ተመጣጣኝ አይደሉም።

ብስክሌት የሚጋልብ ሰው Image copyright Milena Belloni

ከኢትዮጵያ ጋር በቅርብ በተደረገው የሰላም ስምምነት አማካኝነት ድንበሩ በ20 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከፍቷል። አሁን ርካሽ የኢትዮጵያ ሸቀጣ ሸቀጦች በሃገሪቷ ሙሉ ይሸጣሉ፤ ይህም የኑሮ ውድነቱን እያቀለለ ነው።

ሰዎችና ብስክሌቶች በአሥመራ ጎዳና ላይ Image copyright Milena Belloni

የግጭት፣ ከዓለም መገለልና የተባበሩት መንግሥታት ማዕቀብ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ባለፈው ህዳር ቢያበቁም፤ በኤርትራ አሁንም የብዙ ምርቶች እጥረት አለ። የነዳጅ እጥረት መኪኖች ለረጅም ሰዓታት እንዲቆሙ በማድረግ ሰዎች በእግራቸው ከመሄድና ብስክሌት ከመንዳት ሌላ ብዙ ምርጫ እንዳይኖራቸው አድርጓል።

አህያና ብስክሌቶች በአሥመራ ከተማ መንገድ ላይ Image copyright Milena Belloni

ብስክሌት መንዳት በኤርትራዊያን ዘንድ በጣም የታወቀ ስፖርት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በጣልያዊያን የተዋወቀው የብስክሌት ውድድር ለኤርትራ ህዝብ የኩራት ምንጭ ነው። ሞሳና ድበሳይን ያካተተው የሃገሪቱ ብሔራዊ ቡድን በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች በጣም ስኬታማ ነው።

ሞሳና ድበሳይን Image copyright Getty Images

በቅርብ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገው ግንኙነት ብዙ ኤርትራዊያን የሃገራቸው ኢኮኖሚ በፍጥነት እንደሚያድግና የዕለት ከዕለት ኑሯቸውን እንደሚያቀልላቸው ተስፋ ያደርጋሉ።

x Image copyright Milena Belloni

በአንትሮፖሎጂስት ሚሊና ቤሎኒ እና በጋዜጠኛ ጄምስ ጄፍሪ

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ