የወንድ የእርግዝና መከላከያ፤ ለምን እስካሁን ዘገየ?

የወንድ የዘር ፍሬ Image copyright Getty Images

የወንዶች የእርግዝና መከላከያ የመጀመሪያ የሙከራ ሂደቱን ማለፉን ባለሙያዎች ተናገሩ። በየቀኑ የሚወሰደው የመከላከያ አይነት ወንዶች የዘር ፈሳሽ እንዳያመነጩ የሚያደርግ ነው።

ይህም አሁን ላይ ጥቅም ላይ እየዋሉ ካሉት ኮንዶምና ቫዝክቶሚ በተጨማሪ ሌላ አማራጭ ነው ተብሏል። ነገር ግን ሃኪሞች እንደሚሉት ምርቱን በተሟላ ሁኔታ አጠናቅቆ ለገበያ ለማቅረብ ምናልባትም አስርት ዓመታትን ሊጠይቅ ይችላል።

ለምን እስካሁን አልነበረም?

የሴቶች የእርግዝና መከላከያ የተጀመረው ከ50 ዓመታት በፊት በሀገረ እንግሊዝ ነበር። ምነው ታዲያ የወንዶችን የእርግዝና መከላከያ ለመስራት ለምን ይህን ያህል ጊዜ ወሰደ? የሚለው ዋናው ጥያቄ ነው።

አንዳንዶቹ ይህ ያልሆነው ምናልባትም ወንዶች ስለማይፈልጉ ነው የሚሉ ቢኖሩም በሌላ በኩል ደግሞ ስለጉዳዩ የተጠየቁ ወንዶች ቢኖር ኖሮ መከላከያውን እንጠቀም ነበር ብለዋል።

ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው?

በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው

ሌላኛው ነገር ደግሞ ሴቶች ራሳቸው ወንድ የእርግዝና መከላከያ ወስጃለሁ ቢላቸው ያምኑ ይሆን? ወይ የሚለውም ነው።

ሩስኪን ዪኒቨርሲቲ በ2011 እንግሊዝ ውስጥ ባደረገው ጥናት መሰረት ከ134 ሴቶች 70 የሚሆኑት ወንድ የፍቅር ጓደኞቻቸው የእርግዝና መከላከያ መውሰዳቸውን ይዘነጋሉ ብለው ይሰጋሉ።

የወንዶችን የእርግዝና መከላከያ በወሲባዊ ግንኙነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳይኖረው መጠንቀቅ ያስፈልግ ስለነበር ነው ጉዳዩ ጊዜ የወሰደው የሚል አስተያየት የሰነዘሩም አሉ።

የወንድ የዘር ፈሳሽ ማመንጨትን በተመለከተ

መካን ያልሆነ ወንድ በሆርሞኖች አማካኝነት እየታገዘ በተከታታይ የዘር ፈሳሽ ያመነጫል። የእርግዝና መከላከያ ይህን ሂደት ሊያዛባ ይችላል ውይ? የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር።

ተመራማሪዎች እንደሚሉት ግን አሁን በኤልኤ ባዮሜድ እና በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲዎች የተደረገው ጥናት ውጤታማ ነው። በ40 ወንዶች ላይ የመጀመሪያ ሙከራ ተደርጎ ያለችግር ውጤታማ መሆኑን ኒውኦርሊንስ ውስጥ በተካሄደው ውይይት ላይ ተገልጿል።

«የወሊድ መቆጣጠሪያን ወዲያ በሉት»፦ ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ

ከሙከራው በኋላ የተወሰኑ የጎንዮሽ ጉዳቶች ተገኝተዋል። የእርግዝና መከላከያን ከወሰዱት ወንዶች መካከል አምስቱ የወሲብ አቅማቸው ቀንሷል፤ ሁለቱ ደግሞ የብልት መቆም ችግር አጋጥሟቸዋል። በአጠቃላይ ግን የወሲብ ተነሳሽነት ላይ ችግር አልተገኘም።

የጥናቱ መሪ ክሪስቲና ዋንግና ጓደኞቿ "ሙከራችን የሚያሳየው ሁለቱን ሆርሞኖች አንድ ሥራ ላይ እንዲተባበሩ ማድረግን ነው። የዘር ፈሳሽን ማመንጨት ይቀንሳል፤ በአንጻሩ ለወሲብ ያለው ተነሳሽነት እንዳለ ይቀጥላል" ብለዋል።

የስሜት መዘበራረቅን በተመለከተ

ሌሎች ሳይንቲስቶች በየወሩ የሚወሰድ የእርግዝና መከላከያ በማዘጋጀት ላይ ነበሩ። ነገር ግን የመጀመሪያውን ዙር ካጠናቀቁ በኋላ ሁለተኛውን ሙከራ አቁመዋል።

ምክንያታቸው ደግሞ የስሜት መዘበራረቅና ድብርትን ያመጣል የሚል ነው። በጥናታቸውም የዘር ፈሳሽን እንቅስቃሴ የሚገድብ ምናልባትም ከወንድ ብልት እንዳይወጣም ሊያደርግ ይችላል ብለዋል።

እናም ቫዛልጀል (vasalgel) የተሰኘ በሁለቱ የወንድ የዘር ፍሬዎች የሚወጋና የዘር ፈሳሽን ከግራና ቀኝ ፍሬዎች ወደ ብልት የሚወስድ ህክምና ተጀምሯል። ነገር ግን እስካሁን ትግበራው በእንስሳት ላይ ብቻ የተገደበ ቢሆንም ውጤታማ በመሆኑ ተመራማሪዎች ሰው ላይ ለመጀመር ተዘጋጅተዋል።

የገበያ ሁኔታን በተመለከተ

ፕሮፌሰር ሪቻርድ አንደርሰን ይህን ምርምር በእንግሊዝ ከሚያደርጉት መካከል አንዱ ናቸው።እሳቸው እንደሚሉት ፋርማሲዎች ይህን የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ለመሸጥ ፍላጎታቸው አነስተኛ ነው ምክንያታቸው ደግሞ ወንዶችና ሴት ጓደኞቻቸው በዚህ ጉዳይ ላይ እምነት የላቸውም ሚል ነው።

"ያለውን የገበያ ሁኔታ በደንብ ለማሳመን የተደረገ ጥረት ያለ አይመስለኝም" ይላሉ ፕሮፌሰሩ።

ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት ተመራማሪዎቹ በእርዳታና በምርምር በጀት ላይ የተንጠለጠለ ሥራ ነው የሚሰሩት። ምክንያቱም በዘርፉ ያለው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ አነስተኛ በመሆኑ ነው።

ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና

በሼፊልድ ዩኒቨርሲቲ የአንድሮሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት አለን ፒሴይ "እስካሁን የወንዶች የእርግዝና መከላከያ በደንብ አልተሰራበትም ስለዚህ አዳዲስ ሥራዎችን መስራት ይኖርብናል" ብለዋል።

ቁልፉ ጥያቄ ፋርማሲዎች በበቂ ሁኔታ ያከፋፍሉታል ወይ? የሚለው ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ። እሳቸው እንደሚሉት እስካሁን ፋርማሲዎች ለዚህ ጉዳይ ፍላጎት አያሳዩም ፤ ትኩረታቸውም ለቢዝነሳቸው ነው።

ተያያዥ ርዕሶች