ፌስቡክ የነጭ ብሔረተኝነትናና የተገንጣይ አመለካከት አራማጆችን ሊያግድ ነው

ማርክ ዙከርበርግ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ

ፌስቡክ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ "የነጮችን ብሔርተኝነትና መለየትን የሚያሞግሱና የሚደግፉ" ፅሁፎችን ከፌስቡክና ከኢንስተገራም ገፆች ላይ እንደሚያግድ አሳወቀ።

ትልቁ የማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ የሽብርተኝነት ይዘት ያላቸውን ይዘቶች ከድህረገፁ ላይ ለመለየትና ለማስወገድ እንደሚሰራም ቃል ገብቷል።

ቁጣን የሚቀሰቅሱ አባባሎችን የሚፈልጉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ወደ የሚከላከሉ የበጎ አድራጎት ገጾች በመምራት ድግፍ እንዲያገኙ ያደርጋል።

ፌስቡክ የምንጠቀምበት ሰዓት ሊገደብ ነው

በኒውዚላንድ የሁለት መስኪዶች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች በቀጥታ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከተላለፈ በኋላ የማህበራዊ ሚዲያዎች ጫና በዝቶባቸዋል።

ፌስቡክ ከዚህ በፊት የነጮችን ብሔርተኝነት የሚያሳዩ ይዘቶችን እንደ ዘረኝነት ስለማይቆጥራቸው በገፁ ላይ እንዲገኙ ፈቅዶ ነበር።

"የአሜሪካ አክራሪ የነጮች ቡድንና በስፔን ያለው የባስክ ተገጣይ ቡድኖች አስፈላጊ የሰዎች ማንነት ክፍል እንደመሆኑት ሁሉ" የነጭ ብሔርተኝነትም ተቀባይነት ያለው እንደሆነ ይቀበል ነበር።

ነገር ግን ረቡዕ እለት ገፁ ላይ ባሰፈረው ፅሁፍ ፌስቡክ ለሦስት ወራት "ከህብረተሰብ አካላትና ምሁራን" ጋር ምክክር ካደረገ በኋላ የነጮችን ብሔርተኝነት ከነጮች የበላይነትና ከሌሎች የተደራጁ የጥላቻ ቡድኖች "መለየት" አይቻልም ብሏል።

'የለቀቀው ሰው ብቻ አደለም ተጠያቂ'

በኒውዚላንድ የተደረገውን ጥቃት ተከትሎ ብዙ መሪዎች የማህበራዊ ሚዲያዎች በገፆቻቸው ላይ ለሚለጠፏቸው ፅንፈኛ ይዘቶችን ሃላፊነት እንዲወስዱ አስጠንቅቀዋል።

የኒውዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ስለማህበራዊ ሚዲያዎች ስትናገር "መልዕክቱን የለቀቀው ሰው ብቻ ሳይሆን አሳታሚዎቹም" እንደዚህ አይነት ይዘቶች ሲለቀቁ ሃላፊነት አለባቸው ብለዋል።

የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የይለፍ ቃል ደህንነት አስተማማኝ አይደለም ተባለ

50 ሰዎችን የገደለው የኒውዚላንዱ ጥቃት ምስል ከማህበራዊ መድረኩ ላይ ከመውረዱ በፊት ከ4 ሺህ ጊዜ በላይ እንደታየ ፌስቡክ አስታውቋል።

ድርጅቱ በ24 ሰዓት ውስጥ የምስሉ 1.2 ሚሊዮን ቅጂዎችን ከመለቀቅ የከለከለ ሲሆን 300 ሺህ የሚሆኑትን ደግሞ ከድረ ገፁ ላይ አጥፍቷል።

የፈረንሳይ ሙስሊሞችን የሚወክል አንድ ቡድን ፌስቡክና ዩትዩብ ምስሉን በገፃቸው ስላስተላለፉ ከሷቸዋል።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ፌስቡክ ላይ ያለን ግላዊ መረጃን እንዴት መጠበቅ ይቻላል?

ተያያዥ ርዕሶች