የቀድሞው የፈረንሳይ ሰላይ ሞቶ ተገኘ

ሰላዩ ዳኒኤል Image copyright AFP

የቀድሞው የፈረንሳይ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ክንፍ ባልደረባ እንደነበረ የሚጠረጠረው ዳኒኤል ፎረስቲር ሬሳው ከጄኔቫ ኃይቅ ራቅ ብሎ በሚገኝ የመኪና ማቆምያ ጋራዥ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱን ፖሊስ ገለጸ።

ጭንቅላቱም በአምስት ጥይት ተበሳስቷል።

ዳኒኤል ለፈረንሳይ የስለላ መሥሪያ ቤት በደኅንነት መኮንንነት ማገልገሉ ይገመታል።

የፈረንሳይ ፖሊስ እንዳለው የዳኒኤል ፎረስቲር ግድያ የተጠናና በጥንቃቄ የተፈጸመ ነው።

ባለፈው መስከረም ዳኒኤል የቀድመውን የኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዝዳንት ልዩ ዘብ ጄኔራል የነበሩትን ፈርዲናንድ አምባኦን አሲሮ በመግደል ተጠርጥሮ ነበር።

ጄኔራል ፈርዲናንድ አምባኦ ያን ጊዜ የፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሳኦ ነጉሶ ተቀናቃኝ እንደነበሩ ይነገራል። ጄኔራል አሞባኦ በፈረንሳይ ለ20 ዓመታት ኖረዋል።

እስራኤል የቀድሞ ሚኒስትሯን በኢራን ሰላይነት ፍርድ ቤት አቆመች

የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን

የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ?

ዳኒኤል በእርግጥ ሰላይ ነበር?

ዳኒኤል በርካታ የስለላ መጻሕፍትን የጻፈ ሰው ነው። ነገር ግን አንድም ጊዜ ቢሆን በጄኔራል ፈርዲናንድ አምባኦ ግድያ እጁ እንዳለበት አምኖ አያውቅም። ፖሊስ ግን የቀድመውን ሰላይ ዳኒኤልን ሞት ከዚሁ የጄኔራል ፈርዲናድ አምባኦ አወዛጋቢ ግድያ ጋር እንደሚያያዝ ይጠረጥራል።

ዳኒኤል በጄኔራሉ ግድያ ክስ ተመሥርቶበት ክሱን በመከታተል ላይ ነበር። የዳኒኤል ጠበቃ በዳኒኤል ላይ ክሱ ከተመሰረተበት በኋላ የዳኒ ሕይወት አደጋ ላይ እንደሆነ ጠቁመው ነበር። በተለይም የዳኒኤል ማንነት በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ከተዘዋወረ በኋላ ሕይወቱ በሰው እጅ ሊጠፋ እንደሚችል ግምት ተይዞ ነበር።

ዳኒኤል የሚኖርባት ሉሲንገስ የምትባል ከተማ ከንቲባ ዣን ሉክ ሶላ በአንድ ወቅት ስለ ዳኒኤል ሲናገሩ "ብዙ የስለላ መጻሕፍት የደረሰ ሰው ነው፤ እሱ ምን እንደፈጸመ ግን አንድም ቀን ነግሮን የሚያውቅ አይመስለኝም" ብለው ነበር።

"በከተማችን የተረጋጋ ኑሮ መስርቶ ሲኖር ነበር። በቀደም ለታ እንኳ አዳራሽ ምረቃ ሥራ ሲያግዘኝ ነበር" ብለዋል ከንቲባው።

የፈረንሳዩ ጋዜጣ ሉ ሙንድ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ዳኒኤል ጄኔራል ሞባኦን ለመግደል ከተዋቀረው መቺ ኃይል ውስጥ አንዱ እንደነበር አምኖ ያውቃል።