የአልጄሪያ ተቃውሞ፡ ቦተፍሊካ አዲስ መንግሥት ሰየሙ

አብዱላዚዝ ቦተፍሊካ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የ82 ዓመቱ አዛውንት ቦተፍሊካ አልጄሪያን እአአ ከ1999 ጀምሮ ሲመሩ ቆይተዋል።

ከስልጣናቸው እንዲነሱ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ የገጠማቸው የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብድላዚዝ ቦተፍሊካ ከፍተኛ ሊባል የሚችል የካቢኔ ሹም ሽር ማድረጋቸውን አስታወቁ።

ብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ከአጠቃላዩ 27 ሚንስትሮች ሀያ አንዱ በሌሎች እንዲተኩ ሆነዋል ሲል ተናግሯል።

ኖርዲን ዴዶይን የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው እንደሚቆዩ በዘገባው ተጠቅሷል።

ፕሬዚደንት ቦተፍሊካ ከስድስት ዓመት በፊት ስትሮክ ካጋጠማቸው ወዲህ መናገርም ሆነ ቆመው መሄድ አይችሉም። ፕሬዝዳንቱ ከስልጣናቸው እንዲነሱ የሚጠይቁ በርካታ አልጄሪያውያን ተቃዋሚዎች መናገር እና መራመድ የማይችል ሰው እንዴት ሊመራን ይችላል ሲሉ ይጠይቃሉ።

አልጀሪያውያን ለስድስት አመታት ያላዩዋቸውን መሪ ይውረዱ እያሉ ነው

አምስት ነጥቦች ስለጌዲዮ ተፈናቃዮች

የደቡብ ክልል፡ ውስብስቡ የዐብይ ፈተና

ቦተፍሊካ ስትሮክ ካጋጠማቸው ወዲህ በአደባባይ አብዝተው አይታዩም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚታመነው አሊ ሃዳድ የተሰኙ አልጄሪያዊ ቱጃር ወደ ጎረቤት ሃገር ቱኒዚያ ሊሻገሩ ሲሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ አሊ ሃዳድ

አሊ ሃዳድ መልከ መልካም ከሚባሉ የአልጄሪያ ቱጃሮች መካከል ስማቸው የሚጠቀስ ሲሆን ለፕሬዚደንት ቦተፍሊካም ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ይታወቃሉ።

የአልጄሪያ መገናኛ ብዙሃን እንደሚሉት ከሆነ አሊ ሃዳድ የእንግሊዝ ፓስፖርት እና ከፍተኛ መጠን ያለው ጥሬ ገንዘብ ይዘው ወደ ቱኒዚያ ለመሻገር ጥረት ሲያደርጉ እሁድ ጠዋት ላይ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

አሊ ሃዳድ በምን ምክንያት በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የታወቀ ነገር የለም።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ