የቬንዝዌላ ቀውስ፡ የተቃዋሚ መሪው ጓይዶ የጦሩን ድጋፍ እየተጠባበቁ ነው

ጓይዶ Image copyright Reuters

የቬንዝዌላው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ እና እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አድርገው የሾሙት ጓይዶ የጦሩን ድጋፍ የሚያገኙ ከሆነ የመንግሥት ለውጥ እንደሚኖር አሳታወቁ።

የቬንዝዌላ ጦር መሪዎች እስካሁን ለፕሬዝደንት ኒኮላስ ማዱሮ ታማኝ ሆነው ቆይተዋል።

የ90 በመቶ ቬንዝዌላውያን ድጋፍ አለኝ የሚሉት ጓይዶ ፕሬዝዳንትነታቸው በአሜሪካ እና ሌሎች ኃያላን ሃገራት ይሁንታን አግኝቷል።

ትናንት የቬንዝዌላ ባለስልጣናት የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ስላጋጠመ የሥራ ሰዓትን እንደሚያሳጥሩ እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያዊያን ቶሎ አያረጁም?

አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው?

"በመጨረሻ ላይ ሳትስመኝ መሄዷ ይቆጨኛል" እናት

ጓይዶ ለቢቢሲ ሲናገሩ በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙት የኃይል እና የውሃ አቅርቦት ማነስ ህዝቡ በማዱሮ አስተዳደር ላይ እምነት እንዲያጣ አድርጎታል ብለዋል።

''ዋና መዲናዋን ካራካስን ጨምሮ ወደ 20 በሚጠጉ አስተዳደሮች ውስጥ በማዱሮ አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ተከስቷል። ህዝቡ የመሠረተ ልማት አቅርቦቶች እንዲሟሉ እና ኒኮላስ ማዱሮ ስልጣናቸውን እንዲለቁ መልእክት እያስተላለፉ ነው'' ሲሉ ጓይዶ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የማዱሮ አስተዳደር እንደሚለው ከሆነ ግን የኃይል አቅርቦት ላይ ሆነ ተብሎ እክል እየተደረገበት ነው፤ ይህም በማዱሮ አስተዳደር ጫና ለማሳደር ነው ሲል ይከሳል።

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ቬንዝዌላውያን ተደጋጋሚ የሆነ የኃይል እና የውሃ አቅርቦት እጥረት ያጋጥማቸዋል

ጓይዶ እንደሚሉት ከሆነ ማዱሮ የጦሩ ድጋፍ እስካላቸው ድረስ ከስልጣን መነሳት አይችሉም።

''የጦሩን ድጋፍ ማግኘት በቬንዝዌላ ዲሞክራሲያዊ እና ሠላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር ለማድረግ እጅግ ወሳኝ ነው'' ሲሉ ተናግረዋል።

የሩስያ የጦር አውሮፕላኖች ቬኔዝዌላ ገቡ፤ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ተሰግቷል

ፕሬዝዳንት ማዱሮ የሩሲያ እና የቻይና ከፍተኛ ድጋፍ ሲኖራቸው፤ እራሳቸውን ፕሬዝደንት አድረገው የሾሙት ጓይዶ ደግሞ የአሜሪካ፣ የካናዳ፣ የእንግሊዝ እና የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ አላቸው።

በቅርቡ በርካታ መሣሪያዎችን እና ተዋጊዎችን የጫኑ የሩስያ የጦር አውሮፕላኖች ቬንዝዌላ መግባታቸው ይታወሳል።