"በቻይና በእስር ላይ የምትገኘው ናዝራዊት ክስ አልተመሰረተባትም" የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር

የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው
አጭር የምስል መግለጫ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው

የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ''ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ላይ የቀረበ ክስ የለም" ሲሉ ተናገሩ።

አቶ ነብያት ጨምረውም በኢትዮጵያ በሙያቸው ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞች ባለመኖራቸው በቀጣዩ ዓመት የሚካሄደውን የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን በኢትዮጵያ የሚከበር ይሆናል ብለዋል።

ቦይንግ የአደጋውን የምርመራ ውጤት ተቀበለ

የ737-8 ማክስ መከስከስ ለቦይንግ ምን ማለት ነው?

በሌላ በኩል በቻይና አደንዛዥ ዕጽ ስታዘዋውር በቁጥጥር ሥር ውላለች ስለተባለች ኢትዮጵያዊት ናዝራዊት አበራ ጉዳይ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በቅርብ እየተከታተለው እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህ መሰረት በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ቆንስላ ጽ/ቤት ከሚመለከታቸው የቻይና የመንግሥት አካላት ጋር መረጃ እየተለዋወጡ እንደሆነ አስረድተዋል። እስካሁንም የቆንስላ ጽ/ቤቱ ተወካይ ናዝራዊት ተይዛ ወደምትገኘበት ጉዋንዡ ከተማ በማቅናት ሶስት ግዜ እንደጎበኟት ያስታወሱት አቶ ነብያት የፊታችን ማክሰኞም እንደሚጎበኟት አሳውቀዋል።

''እስካሁን የቻይና አቃቤ ሕግ ክስ አልመሰረተባትም፤ በናዝራዊት ላይ ክስ እንደተመሰረተባት የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው'' ብለዋል አቶ ነብያት።

ጄፍ ቤዞስ በ35 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ ትዳሩን ለማፍረስ ተስማማበሌላ በኩል በአረብ ሃገራት የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዜጎችን በተመለከተ በተሰሩ የዲፕሎማሲ ሥራዎች የዜጎችን መብት የሚያስከብሩ እና ለእስር የተዳረጉ ከእስር እንዲለቀቁ ስለሚቻልበት ሁኔታ ከስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል። እስካሁንም ከሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር፣ ጆርዳን እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ጋር ስምምነት ተደርሷል። በተጨማሪም ወደ 70ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ወደ ሃገር እንዲመለሱ መደረጉን ጠቅሰዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ