የኢትዮጵያና አሜሪካ የተለየ ግንኙነት እስከምን ድረስ?

የኢትዮጵያና የአሜሪካ ባንዲራ Image copyright Getty Images

ምናልባትም አሜሪካ አፍሪካ ውስጥ ካሏት ወዳጆች በጣም ቅርብ ከምትባለው ኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ያካተተ የአሜሪካ ልዑካን ቡድን ተመልሷል። እነዚህ ሁለት ሃገራት ግን እንዴት ጥብቅ ወዳጆች ሆኑ?

በአሜሪካ ከናይጄሪያውያን በመቀጠል ከፍተኛ የዲያስፖራ ቁጥር ያላት ኢትዮጵያ፤ በሃገር ቤት የሚደረጉ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችና የለውጥ እርምጃዎች ላይ ዲያስፖራው ተጽእኖ እስከማሳደር የሚደርስ ሃይል አለው።

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችንና የበይነ መረብ ዜና ማሰረጫዎችን በመጠቀም 11 ሺ ኪሎሜትሮች በላይ ርቃ ወደምትገኘው ሃገራቸው መረጃዎችን ያደርሳሉ።

አብዛኛቹም ጠንከር ያሉ ፖለቲካዊ መልእክቶችን ያስተላፉባቸዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ 6 ዋና ዋና ዕቅዶች

የጠቅላይ ሚንስትሩን የአንድ ዓመት የስልጣን ዘመን እንዴት ይመዝኑታል?

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዶላር ፍላጎትም ለብዙ ነገሮች መገለጫ ተደርጎ መወሰድ ይችላል። በኢትዮጵያና በኤርትራ ጉብኝት ሲያደርግ የነበረ ከፍተኛ የአሜሪካ የልዑካን ቡድንም በቅርቡ መመለሱ የሚታወስ ነው።

በኢትዮጵያ የተለያዩ ሚኒስትር መስሪያቤቶችና ፕሮጀክቶች ውስጥ ከፍተኛ የአሜሪካ ሃላፊዎች ተቀላቅለው እንደሚሰሩም በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይነር አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አምባሳደሩ በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ያጋጠመበትን ቦታ ሄደው የጎበኙ ሲሆን በምርመራ ስራወም ሃገራቸው ትብብር እንደምታደርግ ቃል ገብው ነበር።

'' ሌላ የአፍሪካ ሀገራት እንደዚህ አይነት ግንኙነት ከአሜሪካ ጋር የላቸውም።'' ይላል የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ የሚሰራው የአማራ ማህበር በአሜሪካ ዋና ሰብሳቢ ቴዎድሮስ ትርፌ።

ኢትዮጵያ በየትኛውም ሃገር ቅኝ ስላልተገዛች ይፋዊና በህግ ማእቀፍ የተደገፈ ግንኙነት ከአሜሪካ ጋር የጀመረችው በወቅቱ ወካይ የነበሩት ግለሰብ በአውሮፓውያኑ 1903 የስራ ደብዳቤያቸውን ለዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ሲያስረክቡ ነበር።

ከደህንነት ስራዎች ጋር በተያያዘ የምታገኘውን ድጋፍ ሳይጨምር ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የሚባለውን የገንዘብ ድጋፍ ከአሜሪካ ታገኛለች።

ባለፉት አምስት ዓመታትም ብቻ ከልማት ስራዎችና ሰብአዊ ድጋፍ ጋር በተያያዘ ሃገሪቱ 4 ቢሊዮን ዶላር ከአሜሪካ አግኝታለች።

በአውሮፓውያኑ 2017 በተሰበሰበ አንድ መረጃ መሰረት ደግሞ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እስከ 4.6 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ ወደ ሃገር ቤት የላኩ ሲሆን አብዛኛው ደግሞ የሚመጣው ከአሜሪካ ነው።

Image copyright ESFNA

የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች በአሜሪካ በጣም ስኬታማ ከሚባሉት መካከል ናቸው። ጠንካራ ሰራተኞችና የማህበረሰብ ልማት ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ስርአቶች ላይ የሚያተኩር እንደሆነ ለአስርታት ኢትዮጵያ ዲያስፖራዎችን በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ሲያጠና የነበረው ቦኒ ሆልኮምብ ይናገራል።

የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ?

የዲያስፖራ ፖለቲካ

ከአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች መካከል ከሃገር ሸሽተው የወጡ ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ምሁራን ይገኙበታል። እነዚህ ሰዎች ደግሞ የሃገሪቱ የዕለት ተዕለት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የማሳደር አቅም አላቸው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የለውጥ እንቅስቃሴ ደግሞ ለነዚህ ግለሰቦች ወደሃገር ቤት ለመመለስ በሩን ከፍቷል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራሮችና አባላት እንዲሁም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች በስደት ይኖሩበት ከነበረው አሜሪካ ወደ ሃገራቸው መመለሳቸው ለዚህ አንድ ማሳያ ነው።

በሃገር ቤት ያሉ ወጣቶችን በማስተባበርና መንግስት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማሳደር የሚታወቀው ጀዋር መሃመድም አሁን በሃገሪቱ ለመጣው ለውጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ብዙዎች ያምናሉ።

ባለፉት ዓመታት ሲደረጉ በነበሩ ተቃውሞዎችና የተደራጁ እንቅስቃሴዎች የአሜሪካ ዲያስፖራዎች ሚና የላቀ ነበር። ለአሜሪካ መንግስትም ሆነ ለተለያዩ ዓለማቀፍ የሰብአዊ ተሟጋች ድርጅቶች ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

ኤች አር 128 የተሰኘውና ባለስልጣናት እስከአሁን ላደረሱት ጥፋት በፍርድ ቤት ፍርዳቸውን እንዲያገኙ፣ ብሎም እንደሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ከኢትዮጵያ የተዘረፈው ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆን የሚጠይቀው የውሳኔ ሃሳብ ለአሜሪካ ሴኔት ሲቀርብም የአሜሪካ ተጽዕኖ በኢትዮጵያ ላይ ምን ያክል እንደሆነ ግልጽ አድርጎታል።

የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት ጥሩም መጥፎም የሚባሉ ጊዜያትን አሳልፏል።

አሜሪካ የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዋነኛ አጋር የነበረች ሲሆን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያና የአሜሪካ ወታደሮች ጎን ለጎን በመሆን የኮርያ ጦርነት ላይ ተዋግዋል።

ነገር ግን በአውሮፓውያኑ 1974 ወታደረዊ መፈንቅለ መንግስት ተደርጎ ደርግ ስልጣን ሲይዝ ኢትዮጵያ ወዳጅነቷን ከአሜሪካ ወደ ሩሲያ አዙራ ነበር።

ከ17 ዓመታት በኋላ የደርግ መንግስት ወድቆ ኢህአዴግ ስልጣን ሲይዝ የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት ወደ ቀድሞ ስፍራው ተመልሷል።

በተለይ ደግሞ ከመስከረም አስራ አንዱ የሽብር ጥቃት በኋላ አሜሪካ ኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ አጋር አድርጋታለች።

አሜሪካ የኦሳማ ቢን ላደን ልጅ ያለበትን ለጠቆመኝ 1 ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ አለች

የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት መግለጫ ምን ይላል?

ምክንያቱም በቀጠናው ያለውን የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ ለመቆጣጥር ኢትዮጵያ ወሳኝ የሆነ መልክአ ምድርና ቅርበት አላት።

አምባሳደር ራይነር እንደሚሉት ''ኢትዮጵያ ሰፊና ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ከመሆኗም በተጨማሪ በከፍተኛ ፍጥነት እኣደገ ኣለ ኢኮኖሚ ባለቤት ናት። በተጨማሪም የቀጠናውን ሰላም ከማረጋገት አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዳላት እናስባለን።''

አሁን አሁን ግን ከፕሬዝዳንት ትራምፕ መምጣት በኋላ አሜሪካ ፊቷን ከሽብር መከላከል ወደ ቻይና እያዞረች ይመስላል። ይህ ደግ ከአፍሪካ ሃገራት ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ሊቀይረው እንደሚችል ይታመናል።