የዓለማችን ሃብታም ሴቶች

ማኬንዚ ቤዞስ Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ማኬንዚ ቤዞስ

የዓለማችን ሃብታሙ ግለሰብ ከባለቤቱ ጋር ፍቺ ሲፈጽም የሚካፈሉት ገንዘብ ከፍተኛ ሊሆን እነደሚችል ማሰብ አይከበድም። ባለፈው ሳምንት አማዞን የተባለው የበይነ መረብ መገበያያ መስራችና ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ከባለቤቱ ማኬንዚ ጋር ፍቺ ሲፈጽም የሆነውም ይሄው ነው።

የሴቶችና ወንዶች የኢኮኖሚ እኩልነት እንዴት ይስፈን?

በስምምነታቸው መሰረት ማኬንዚ የአማዞንን 4 በመቶ የሃብት ድርሻ የምትወስድ ሲሆን ድርሻዋ እስከ 35.6 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ዋጋ ይኖረዋል። ይህ ደግሞ ብቻውን የዓለማችን ሦስተኛዋ ሃብታም ሴት ያደርጋታል ማለት ነው። በአጠቃላይ ግን ከዓለማችን 24ኛዋ ሃብታም ሰው መሆን ችላለች።

ነገር ግን በዓለማችን ላይ ያሉት የናጠጡ ሃብታም ሴቶች እነማን ናቸው?

ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና

1) ፍራንሷዝ ቤተንኩር ሜየርስ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ፍራንሷዝ ቤተንኩር ሜየርስ

የተጣራ ሃብት: 49.3 ቢሊየን ዶላር ሲሆን እንደ ፎርብስ መጽሄት ከሆነ የዓለማችን 15ኛ ሃብታም ሴት ነች።

ይህች የ65 ዓመት ፈረንሳያዊት 'ሎሪያል' የተባለው የመዋቢያ እቃዎች አምራች ድርጅት ወራሽ ስትሆን የድርጅቱን 33 በመቶ ድርሻ የግሏ ማድረግ ችላለች። ፍራንሷዝ ቤተንኩር ሜየርስ በፈረንጆቹ 2017 ነበር የ94 ዓመት እናቷ ሊሊየን ቤተንኩር ህይወቷ ሲያልፍ ድርጅቱን የወረሰችው።

ፍራንሷዝ ቤተንኩር ሜየርስ የታወቀች ምሁር ስትሆን በብዙ ኮፒ የተሸጡ ሁለት መጽሃፎችንም ማሳተም ችላለች።

2) አሊስ ዋልተን

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ አሊስ ዋልተን

የተጣራ ሃብት: 44.4 ቢሊየን ዶላር ባለቤት ስትሆን በዓለማችን 17ኛ ሃብታም ነች።

የ69 ዓመቷ አሜሪካዊት 'ዋልማርት' የተባለው ታዋቂ ሱፐርማርኬት መስራች ሳም ዋልተን ልጅ ነች። ነገር ግን ከሁለቱ ወንድሞቿ በተለየ መልኩ የቤተሰቡን የንግድ ሥራ ወደ ጎን በማለት ወደ ጥበብ ሥራዎች ፊቷን አዙራለች። በአሁኑ ሰዓትም 'ክሪስታል ብሪጅስ ሚዩዚየም ኦፍ አሜሪካን አርትስ' የተባለ ድርጅት ዋና ኅላፊ ሆና እየሰራች ነው።

በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ

3) ማኬንዚ ቤዞስ

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ጄፍና ማኬንዚ ቤዞስ

የተጣራ ሃብት : ቢያንስ 35.6 ቢሊየን ዶላር የሚሰደርስ ሃብት እንዳላት የሚገመት ሲሆን ከባለቤቷ ጋር ፍቺ ስትፈጽም ከአማዞን ድርሻ ያገኘችው ነው። ምናልባትም ከዚህ በኋላ ሃብት ሊኖራት እንደሚችል ይገመታል።

የ48 ዓመቷ ማኬንዚ ከባለቤቷ ጄፍ ቤዞስ አራት ልጆችን ያፈራች ሲሆን በፈረንጆቹ 1993 ነበር ትዳራቸውን የመሰረቱት።

4) ሊን ማርስ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ጃከሊን ማርስ

የተጣራ ሃብት:በ23.9 ቢሊየን ዶላር የዓለማችን 33ኛ ሃብታም ሰው ነች። የ79 ዓመቷ ቢሊየነር ማርስ የተባለው ድርጅት አንድ ሦስተኛ ድርሻ ባለቤት ስትሆን በድርጅቱ ውስጥ ለ20 ዓመታት አገልግላለች።

ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት

5) ያን ሁዊያን

የተጣራ ሃብት: 22.1 ቢሊየን ዶላር። በቻይና አንደኛ ሴት ቢሊየነር፣ የዓለማችን 42ኛ ባለሃብትና በሴቶች 5ኛ ሃብታም ሴት ነች። የ37 ዓመት ጎልማሳ የሆነችው ያን የቻይና በግንባታ ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሯል ተብሎ የሚጠራው 'ካንትሪ ጋርደን ሆልዲንግስ' አብዛኛው ድርሻ ባለቤት ነች።

የኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ ምሩቋ ያን 57 በመቶ የሚሆነውን የድርጅቱን ድርሻ ከአባቷ ነው የወረሰችው።

6) ሱዛን ክላተን

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሱዛን ክላተን

የተጣራ ሃብት: 21 ቢሊየን ዶላር ሲሆን የዓለማችን 46ኛ ሃብታም ነች።

የ56 ዓመቷ ሱዛን ክላተን ጀርመናዊ ዜግነት ያላት ሲሆን በመኪና ማምረትና የመድሃኒት ምርቶችን በመሸጥ ላይ የተመሰረተ የንግድ ዘርፍ ውስጥ ነው ተሰማርታ የምትገኘው።

የሴት ልጅ ግርዛት ምንድነው? የት እና ለምን ይፈጸማል?

የድርጅቱ መስራች የሆኑት ቤተሰቦቿ ህይወታቸው ሲያልፍ 50 በመቶ የሚሆነውን የመድሃኒት ድርጅት ድርሻ መውረስ ችላለች። ከዚህ በተጨማሪ እሷና ወንድሟ የታዋቂው መኪና አምራች ድርጅት 'ቢኤምደብልዩ' 50 በመቶ ድርሻም አላቸው።

7) ላውረን ፖወል ጆብስ

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ሎሪን ፖወል ጆብስ

የተጣራ ሃብት: 18.6 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሃብት ያላት ይህች ሴት በዓለማችን 54ኛ ሃብታም ሰው ናት።

የአፕል ፈጣሪ ስቲቭ ጆብስ ባለቤት የነበረችው ላውረን ባለቤቷ ህይወቱ ካለፈ ወዲህ የድርጅቱን ጥቂት የማይባል ድርሻ በመውረስ 20 ቢሊየን ዶላር የግሏ ማድረግ ችላለች።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የ55 ዓመቷ ጎልማሳ በጋዜጠኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ስትሰራ ቆይታለች።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ