መሐመድ አዴሞ "የግሉ ሚዲያ ላይ ስጋት አለኝ"

መሀመድ አዴሞ

አቶ መሐመድ አደሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር ወደ ስልጣን እንደመጣ ቀድመው ወደ ሀገር ቤት ከገቡ የዳያስፖራ አባላት መካከል አንዱ ናቸው። ከዚያም በኋላ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የክልሉን መገናኛ ብዙሃ ድርጅትን በኅላፊነት እንዲመሩ ኅላፊነት ሰጥቷቸዋል።

ይህ ግን ረጅም ጊዜ አልቆየም፤ ከኅላፊነታቸው መነሳታቸው ተሰማ። የአቶ መሐመድ ከስልጣን መነሳትን ተከትሎ በሌሎች ኅላፊነቶች ሊመደቡ እንደሚችል ሲወራ ከርሟል።

እኛም ናይሮቢ በሚገኘው ቢሯችን በተገኙበት ወቅት በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ አጭር ቆይታ አድርገናል።

ወደ ሀገር ቤት ሲመን ጠብቀው ምን አገ?

ከሀገር ርቆ ሲኖር ይላሉ አቶ መሐመድ "ሁሉንም ነገር በወሬ ነው የምትሰማው። ስለሀገርህ የምታየውና የምትሰማው ነገር የተለያየ ነው" በማለት ወደ ሀገራቸው ሲመጡ አእምሯቸውንም ልባቸውንም ከፍተው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለማየት መምጣታቸውን ያስረዳሉ። "ብዙ ለማውራት ሳይሆን ብዙ ለማድመጥ ወስኜ ነበር ጓዜን ጠቅልዬ ሀገር ቤት የገበሁት" ሲሉም ያጠናክሩታል።

"ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት

አዲስ አበባ እግራቸው ሲረግጥ ይሰሙ ከነበረው ነገር በተቃራኒውን ማግኘታቸውን የሚናገሩት አቶ መሐመድ፤ ከዚህ በፊት የሚያውቋቸው ነገሮች በአጠቃላይ ተቀይረው በአዲስ መልክ፣ አዲስ ስሜት ተላብሰው እንዳገኟቸው አልሸሸጉም።

"አዲስ አበባ የሚቀበለኝ ሰው ባይኖር ኖሮ፣ የት እንደምሄድ፣ የት እንደምገባ ማወቅ በጭራሽ አልችልም ነበር" ሲሉ በጊዜው የተፈጠረባቸውን አግራሞት አጋርተውናል።

ይህ የለውጥ መንፈስ ግን መናገሻ ከተማዋን ብቻ ሳይሆን ክልሎችንም ያዳረሰ እንደነበር በተጓዙበት ሁሉ አስተውለዋል። "ብዙ ሰው ተስፋ ማድረግ ጀምሮ ነበር" ያሉት አቶ መሐመድ እርሳቸው አዲስ አበባ ሲደርሱ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር የጫጉላ ጊዜው አለማለቁን ያስታውሳሉ።

በወቅቱም ዜጎች ደስተኛ ሆነው ከደስታቸው በላይ ደግሞ ብዙ ተስፋ ኖሯቸው ማየታቸው ልባቸውን ሳያሞቀው አልቀረም። ከደስታው ባሻገር በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አንደበትና ልብ ውስጥ አይተው የሚመሰክሩት ተስፋ ማድረግና ብሩህ ነገር የማሰብ ጅማሮንም አይዘነጉም።

የዓለማችን ሃብታም ሴቶች

"ዜጎች ተስፋ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ትልቅ መነሳሳት ነበራቸው" በማለት የኢትዮጵያ ወጣት ለረጅም ጊዜ ያጣው ሁለት ነገሮችን እንደሆነ በማስረጃ አስደግፈው ያስረዳሉ። ቀዳሚው ተስፋ የሚሰጠው ሲሆን ተከታዩ ደግሞ ተስፋ ሰጥቶት ለተሻለ ነገር የሚያነሳሳው መሪ በማለት።

"ወደ ሥራ፣ ወደ አንድነት የሚመራው ነበር የጠፋው። ይህ አሁንም አለ። ያኔ እኔ በመጣሁበት ወቅት ደግሞ ገና ትኩስ ስለነበር የሚደንቅ ጊዜ ነበር፤ ለእኔ። ከጠበኩት በላይ ነበር የሰዉ ነፃነት" ይላሉ አቶ መሐመድ።

የመንግሥት ስልጣን

አቶ መሐመድ ከተሰጣቸው ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክን የማስተዳደር ኅላፊነት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ከተነሱ በኋላ አሁን እረፍት ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ። ከተሾሙበት ለምን እንደተነሱ ሲጠየቁም ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር ተነጋግረውና ተማምነው መሆኑን ይጠቅሳሉ።

በርግጥ ኅላፊነቱ ሲሰጣቸው ሚዲያውን የሕዝብ ድምፅ ለማድረግ፣ ተሰሚነት እንዲኖረው ለማድረግ አልመው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ላለፉት አራት ዓመታት የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትወርክን በቦርድ ሊቀመንበርነት ከመሩ ወዲህ ጥሩ ሥራ ተሰርቶ ነበር የሚሉት አቶ መሐመድ ያንን ለማስቀጠል ብርቱ ፍላጎት ነበራቸው።

ብዙ ሥራም ሰርተናል ሲሉ በስልጣን ላይ የቆዩበት ጊዜ ማጠር ከውጤታማነት እንዳላናጠባቸው ይጠቅሳሉ። በምሳሌ ሲያስረዱም በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪዎች በክልሉ ውስጥ የሚሰራውን እና እየሆነ ያለውን በተሻለ መንገድ እንዲረዱ ለማድረግ፤ አሁን የአንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የሆነውን ፕሮግራም ወደ ሦስት ሰዓት ለማሳደግ፤ ከዚያም ወደ ስድስት ሰዓት፤ በዓመት ውስጥ ደግሞም ራሱን የቻለ የሙሉ ቀን የቲቪ ፕሮግራም ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ሰርተናል" ይላሉ።

ገዢው የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ወደ ሌላ ቦታ ተዘዋውረው ቢሰሩ ከዚህ ቦታ የተሻለ ሊያበረክቱት የሚችሉት አስተዋፅኦ መኖሩን ጠቅሶ እንደነገራቸው የሚያስረዱት አቶ መሐመድ ቀጣይ መዳረሻቸው በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ስር በዲፕሎማትነት መሆኑን አልሸሸጉም።

በወሲብ ፊልሞች ሱሰኛ የሆኑ ወጣት ሴቶች

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን በወጣት ኃይል የተደራጀ፣ ብዝኀነት በሚታይበት፣ ሙያው ያላቸውና ከዚህ በፊት ከሀገር ወጥተው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ልምድ ባላቸው ሰዎች የማዋቀር ሀሳብ ስላለ ነው ወደዚያ እንድዘዋወር የጠየቁኝ በማለት ከኃላፊነታቸው ፈልገወው ሳይሆን በፓርቲው ጥያቄ እንደተነሱ አቶ መሐመድ ይናገራሉ።

"በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ዲፕሎማት ሆኜ እንድሰራ ፍላጎት አለ። ለዚያ ነው ከቦታው የቀየሩኝ። በርግጥ ስምምነት ላይ አልደረስንም። እኔ ጋዜጠኝነቱ ላይ የመቆየት ፍላጎት አለኝ። የእነርሱም መከራከሪያ ግን አሳማኝ ነው። የትምህርት ዝግጅቴም ለዚያ ይረዳኛል። ገና እየተነጋገርን ስለሆነ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ስለዚህ በጊዜ ሂደት ማየት ይሻላል" ሲሉ ያለውን ሁኔታ ይገልፁታል።

ከኅላፊነት ሲነሱ ተከዳሁ የሚል ስሜት ተሰምቷቸው እንደሆነ ተጠይቀው በጭራሽ ሲል መልሰዋል። "ኢትዮጵያ ሽግግር ላይ ናት። የሽግግር ወቅት ደግሞ ብዙ ችግሮች አሉበት" የሚሉት አቶ መሐመድ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር በሚገባ መነጋገራቸውን ከእርሳቸውና በዙሪያቸው ካሉት አመራሮች ጋር ምንም ችግር እንደሌለ ያስረዳሉ። ከኋላ ያሉ ያሏቸው ግለሰቦች አንዳንድ ፍራቻዎች እንደነበሯቸው ነገር ግን ከኅላፊነት መነሳታቸውን አንደ ክህደት እንዳላዩት ያረጋግጣሉ።

የጠቅላይ ሚንስትሩን የአንድ ዓመት የስልጣን ዘመን እንዴት ይመዝኑታል?

"እዚያ ብቆይ በጣም ደስተኛ ነበርኩ፤ እቅዶቼ ብዙ ነበሩ። ነገር ግን እንደ ኢትዮጵያዊ የምፈልገው ዐብይ ሲሄድ የሚኖር ተቋም መገንባት ነው። አሁን የሚያስፈልገን ተቋም መገንባት ነው። እዚያ ላይ ደግሞ ግልፅ ውይይት አድርገን ስለተለያየን እንደመከዳትና እንደ ክፋትም አልቆጠርኩትም።"

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙአቶ መድ አይን

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ከቀጠናው አንፃር እንኳ ቢታዩ ከደረጃ በታች ነው የሚገኙት የሚሉት አቶ መሐመድ የመንግሥት ልሳን ሆኖ መኖሩንና ነፃ ሚዲያ ገንብቶ ለመስራትም መወዳደሪያ ሜዳው ምቹ እንዳልነበረ ይጠቅሳሉ።

"ለግል መገናኛ ብዙሃንም ማስታወቂያ ማግኘት ፈተና ነው። ስለዚህ የግል ሚዲያው ቀጭጮ ነው ያለው" የሚሉት አቶ መሐመድ ዶ/ር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ከአክቲቪስትነትና ከጋዜጠኝነት አንዱን መርጠው እንዲሰሩ በግልፅ ጥሪ ማቅረባቸው እስከዛሬ ከነበሩት መሪዎች በተለየ የመጀመሪያው መሪ ያደርጋቸዋል ሲሉ ይጠቅሳሉ።

የመደመር እሳቤ ከአንድ ዓመት በኋላ

ከዚያም አልፎ ይላሉ የሕዝብ ሚዲያውን ጨምሮ ከመንግሥት ቁጥጥር ወጥቶ የሕዝብን ጥያቄ የሚያነሳ፣ የሕዝብ ልሳን ሆኖ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል በማለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደር የታዩ በጎ ነገሮችን ይጠቅሳሉ።

አስተዳደሩ የመገናኛ ብዙሃን በዚያ አቅጣጫ እንዲሄዱ እየሰራ እንደሆነ የሚያምኑት አቶ መሐመድ የሚዲያ ሕግ እየተረቀቀ መሆኑን፣ የሚዲያ ካውንስል ለማቋቋም መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥያቄ እንደቀረበለት በመጥቀስ ለውጡን ታሪካዊ ሲሉ ያሞካሻሉ።

አቶ መሐመድ 'የእኔ ስጋት' የሚሉት ግን አላጡም። ስጋቴ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እየተጠቀምንበት ነወይ የሚል ነው? በማለት ራሳቸውን ከጠየቁ በኋላ "በተለይ በግል ሚዲያው አካባቢ" ሲሉ ለጥያቄያቸው አፅንኦት ይሰጣሉ።

የመንግሥት ሚዲያ አካባቢ ያለው ችግር ለውጥና ቀጣይነት መካከል ያለ ነው የሚሉት አቶ መሐመድ "ነገሮችን ለመቀየር ጊዜ ይወስዳል። በዚያ ውስጥ ሰዎች ምን ያህል ተቺ ዘገባ ማቅረብ እንደሚችሉ? ምን ያህል በነፃነት መስራት እንደሚችሉ፤ ስርአቱን እየፈተሹ እየሄዱ ይመስለኛል" ሲሉ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ላይ ያላቸውን ግምገማ ያቀርባሉ።

"የግሉ ሚዲያ ላይ ግን ይህ የነፃነት አየር ሲከፈት ሁሉም ሰው አንድ ጥግ ይዞ በወሬ፣ በሐሰተኛ ዘገባ ሕዝቡን ጠርዝ እንዲረግጥ እያደረገው ይመስለኛል" ሲሉ ይተቻሉ።

ሕዝብ ስለመሪው ምን እንደሚያስብ እንዴት እንወቅ?

አቶ መሐመድ የእነዚህ የግል የመገናኛ ብዙሃን ተግባር ላይ ያላቸውን ስጋት ሲያቀርቡም "ወደ መንግሥት ቁጥጥር እንዳይመልሰን" ይላሉ። አክለውም የግል መገናኛ ብዙሃን ራሳቸውን ቢፈትሹ ተገቢ መሆኑን ያሰምሩበታል።

በተለይ ደግሞ ይላሉ አቶ መሐመድ "የመገናኛ ብዙሃን ራስን ሳንሱር ማድረግ ሳይሆን የአቻ ግምገማ ወይም ራስን መፈተሽ ያስፈልጋቸዋል። ጥግ ሳይረግጡ፣ መረጃና እውነታ ላይ ተመስርተው ቢሰሩ መልካም ነው። ከአስተያየት (opinion) ሰጪ ጋዜጠኝነት መውጣት ያስፈልጋል" ሲሉም ይመክራሉ።

ማንም ሰው አንድ ነገር መቃወም ከፈለገ ጋዜጣ ከፍቶ፣ የፓርቲ ወይም የአንድ አስተሳሰብ አልያም የብሔር ጥግ ይዞ እርስ በእርስ ከመነቋቆር ይልቅ በመደማመጥ መነጋገርና መወያየት ያስፈልጋል ይላሉ አቶ መሐመድ።

እንደሚዲያ ሰዎች ቁጭ ብሎ መነጋገርን፣ መወያየትን የሚመክሩት አቶ መሐመድ "መንግሥትን ወደ አንድ ጥግ ከገፋነው ጨቋኝ እየሆነ እንዳይሄድ ስጋት አለኝ" በማለት የመገናኛ ብዙሃን ፎረም ወይም ካውንስል ቢፈጠር ከመንግሥት ቁጥጥር ራስን በራስ መፈተሹ እንደሚሻል ይመክራሉ።

ሌላው መገናኛ ብዙሃኑ ላይ ያይዋቸውን ህፀፆችንም ሲዘረዝሩ "አሁን ያለው ችግር የልሂቃኑ ችግር ነው። ልሂቃኑ በጋራ መግባባት ሳይችሉ ነው የቀሩት። ይህንን ወደ ህዝቡ እያመጣነው ይመስለኛል" በማለት እዚህ ላይ ማህባራዊ ሚዲያውም ድርሻ አለው ሲሉ ይገልፃሉ።

ወደ ቀድሞው መመለስ ቀላል ነው የሚሉት አቶ መሐመድ "አሉባልታ፣ ሹክሹክታ፣ ወሬ ላይ የተመሰረተን ዘገባ እየሰሩ መተማመንን ከማጥፋት እና ሀገራችንን ከምናጠፋ ሙያዊ ሥነ ምግባሩን የጠበቀ ጋዜጠኝነት በመተግበር የሚያግባቡንን ነገሮች ፈልገን እርሱ ላይ ካተኮርን ወደፊት መሄድ እንችላለን" ሲሉ ይመክራሉ።