ሀሰት የመሆኑ ዕድል ከፍተኛ መሆኑን እያወቁ፤ ሰዎች ለምንድነው ምትሃት የሚወዱት?

ምትሀተኛ Image copyright Getty Images

ባለሙያዎች ምትሃት ሲሰሩ መመልከት የምንወደው ለምንድነው? ሁሉም ሰው እየተሸወደ እንደሆነና እየተከሰተ ያለው ነገር ውሽት የመሆን እድሉ ክፍተኛ እንደሆነ እያወቀ እንኳን ከመመልከትና ከመደነቅ አይቦዝንም።

በሚያስገርም ሁኔታ እንግሊዝ ለንደን በሚገኝ ጎልድስሚዝ የተባለ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ምትሃትን የሚያጠናና ከስነልቦና ትምህርት ጋር አጣምሮ ምርምር የሚካሄድበት የቤተ ሙከራ ክፍል አለው።

ይህ ቤተ ሙከራ ዋና አላማው ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ምትሃትን መመርመርና ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት ነው። የቤተ ሙከራው ዋና ሃላፊ የሆነው ዶክተር ጉስታቭ ኩህን እንደሚለው ምትሃት የጭንቅላት ትኩረትና ሽወዳን አጣምሮ የያዘ የስነ ልቦና የበላይነት ነው።

ወንዶች ከሴቶች በበለጠ ለምን እራሳቸውን ያጠፋሉ?

ኢትዮጵያ የተካተተችበት ከባድ የአእምሮ ህመሞች ላይ ጥናት እየተደረገ ነው

ስለዚህም ምትሃት ከስነልቦና፣ ነገሮቸን ከመረዳት አቅም፣ ትኩረትና መረጃዎችን ከማቀነባበር ችሎታዎቻችን ጋር ቀጥተኛ የሆነ ዝምድና አለው።

''ምትሃት ማለት ሰዎች ነገሮችን የሚረዱበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ማለት ነው'' ይላል ዶክተር ጉስታቭ ኩህን።

ምትሃት እንዴት እንደሚሰራ ማወቅ ማለት ደግሞ ምንም አይነት ነገር ብንመለከት አለመገረም ማለት እንደሆነ ያስረዳል።

ሰዎች ወደተሳሳተ ቦታ እንዲመለከቱ ማድረግ ወይም ባለሙያዎቹ 'ሚስዳይሬክሽን' የሚሉት ማለት ነው፤ የምትሃት ወሳኙ ቦታ ነው። የምትሃቱን ዋና ምንጭ ለማግኘት ሲሉ ተመልካቾች ሁሌም ቢሆን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ወደሚሉት ቦታ ደጋግመው ይመለከታሉ።

ይህ ደግሞ ለምትሃተኛው ነገሮችን ቀላል ያደርግለታል።

ምክንያቱም እነሱ ወደየትኛዎቹ አቅጣጫዎች ትኩረታቸውን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ስለሚያውቅ ማስተዋል በማይችሉበት ሁኔታ ምትሃቱን ይሰራና ያስደምማቸዋል።

በምትሃት አስተምሮት መሰረት ምንም እንኳን አንድ ነገር ውሸት መሆኑን ብንገነዘብም የሆነ ጥያቄ የሚፈጥርና ትኩረታችንን የሚሰርቅ ነገር አለው። ስለዚህ ምትሃት ልክ በአሁኑ ሰአት ሃሰተኛ ዜናዎች ትኩረታችን የሚስቡትን አይነት ተጽዕኖ ይፈጥርብናል።

''ታላላቅ ምትሃተኞች ዓለምን ጉድ ያሰኙ የተለያዩ ተግባራትን ይፈጽማሉ። ነገር ግን አብዛኛው ሰው እነዚህ ምትሃተኞች በልምምድ ያገኙት ችሎታ እንደሆነ ማሰብ አይፈልግም። በቤተ ሙከራውም ለማስተማር የምንሞክረው ይህንኑ ነው።'' ሲል ስለ ትምህርት አሰጣጡ ያስረዳል ዶክተር ጉስታቭ ኩህን።

ምትሃት በራስ መተማመን ጥግ እንደመሆኑ መጠን ምትሃትን የሚሰሩ ሰዎች ከማንኛውም ሰው ጋር በቀላሉ መግባባትም ሆነ ማስደመም ይችሉበታል።

ሃና ላውረንስ በዩኒቨርሲቲው ስነልቦና የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ነች። እሷ እንደምትለው በቤተ ሙከራው ያገኘችው የምትሃት እውቀት ብዙ ሰዎችን እንድትተዋወቅና በራስ መተማመኗ እንዲጨምር አግዟታል።

የሙዚቃ ሕክምና በኢትዮጵያ

የወንድ የእርግዝና መከላከያ፤ ለምን እስካሁን ዘገየ?

እኛን የማይገቡን ነገሮች ሁሌም ቢሆን ትኩረታችንን ይስባሉ። ስለዚህ ለጥያቄዎቻችን መልስ በምንፈልግበት ሰአት አእምሯችን በተጽዕኖ ውስጥ ስለሚወድቅ የመሸወድ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

ነገር ግን ይላል ዶክተር ጉስታቭ ኩህን ልክ አስፈሪ ፊልሞችን ሲኒማ ቤት ገብተን ስንመለከት የምንንዝናናበት ዋነኛ ምክንያት እውነት እንዳልሆነ ስለምናውቅና እኛ ላይ ሊደርስብን እንደማይችል ስለምናውቅ ነው።

''የምትሃትም ሃሳብ እንደዚሁ ነው። በትክክለኛው ዓለም አንድ ሰው ለመሁለት ሲከፈል ብንመለከት የሚዘገንንና የሚየዓስጨንቅ ስሜት ውስት እንገባለን። ነገር ግን በምትሃት መልክ ሲቀርብልን ያዝናናናል።