የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በአፍሪካ እየተበራከተ ይሆን?

የሱዳን ወታደሮች Image copyright Getty Images

የሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦማር አል-በሸር ከህዝባዊ ተቃውሞ በኋላ በሃገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት ተፈጽሞባቸዋል።

ስልጣን ላይ የሚገኘው ጦር እንደሚለው ከሆነ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ሃገሪቱን ያስተዳድራል።

ለዘመናት በስልጣን ላይ ያሉት ስድስቱ መሪዎች

ኦማር አል-በሽር: ከየት ወደየት?

እአአ 1989 ኦማር አል-በሽር እራሳቸው መንበረ ስልጣኑን የያዙት በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ነበር። ከኦማር አል-በሽር በፊትም በሱዳን በርካታ መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደ ሲሆን፤ ዓላማቸውን ማሳካት ያልቻሉ በርካታ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎችም ነበሩ።

አፍሪካ እስካሁን ምን ያክል መፈንቅለ መንግሥቶችን አስተናግዳለች? የትኛዋ አፍሪካዊት ሃገር ብዙ በኃይል የመጡ መንግሥታትን አስተናግዳለች?

ሱዳን ከሁሉም የአፍሪካ ሃገራት በላይ በርካታ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎችን በታሪኳ አሳልፋላች። የኦማር አል-በሽርን ጨምሮ 4 የተሳኩ እና 15 ያልተሳኩ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂደዋል።

መፈንቅለ መንግሥት መቼ ነው መፈንቅለ መንግሥት ሚባለው?

የፖለቲካ ተመራማሪዎች የሆኑት አሜሪካውያኑ ጆናታን ፖዌል እና ክላይተን ቲይን መዝገበው እንደያዙት ባለፉት 70 ዓመታት በጠቅላላ 206 መንግሥታትን በኃይል ለመገልበጥ የተደረጉ ሙከራዎች ነበሩ።

እኒህ የፖለቲካ ምሁሮች መፈንቅለ መንግሥትን ''በጦር ወይም በመንግሥት ስልጣን ላይ በሚገኙ ሲቪሎች አማካኝነት በግልጽ እና ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ስልጣን ላይ የሚገኙ መሪዎችን ከስልጣን ማስነሳት'' ሲሉ ይገልጹታል።

ይሁን እንጂ ከህዝባዊ ተቃውሞዎች በኋላ መሪዎችን በኃይል ከስልጣን የሚያባርሩት የጦር ጀነራሎች በዚህ ''የመፈንቅለ መንግሥት'' ትርጓሜ አይስማሙም።

የሱዳን ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወታደሩ ያስቀመጠውን ሰዓት እላፊ ጣሱ

ከህዝባዊ ተቃውሞ በኋላ መሪዎች በኃይል ስልጣን እንዲለቁ የሚያስገድዱት የጦር ጀነራሎች መፈንቅለ መንግሥት አላከናወንም ይላሉ። ለምሳሌ ከሁለት ዓመታት በፊት በዚምባብዌ ከከፍተኛ ተቃውሞ በኋላ የቀድሞ ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ የ37 ዓመታት የስልጣን ዘመን ማብቃቱን በቴሌቪዥን ያወጁት የጦር ጀነራል እየተካሄደ ያለው መፈንቅለ መንግሥት አይደለም ብለዋል።

ፖውል እና ክላይተን መፈንቅለ መንግሥት ስኬታማ ነው የሚባለው ለ7 ቀናት ያክል መቆየት ከቻለ ነው ይላሉ።

እስካሁን በአፍሪካ 105 ያልተሳኩ እና 100 የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥቶች ተካሂደዋል። ምዕራባዊቷ አፍሪካ ሃገር ቡርኪና ፋሶ 7 የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥቶች በማስተናገድ ትመራለች።

በአፍሪካ ምን ያህል ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂደዋል?

በእርግጥም አፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቶችን አስተናግዳለች፤ ነገር ግን በኃይል የሚደረጉ የመንግሥት ለውጦች እየቀነሱ ነው።

ከ1960 እስከ 2000 (እኤአ) ባሉት 40 ዓመታት ውስጥ የተካሄዱ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች መጠን በሚገርም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው። በዚህም በየአስር ዓመቱ 40 የሚጠጉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች ተደርገዋል።

ከዚያ በኋላ ግን ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። በ2000 የመጀመሪያ አስር ዓመታት ውስጥ 22 ሙከራዎች የተደረጉ ሲሆን ባለንበት አስር ዓመታት ውስጥ ግን ቁጥሩ 17 ደርሷል።

የሱዳን ተቃውሞ ተጋግሎ አምስት ቀናት ተቆጥረዋል

በሱዳን የኦማር አል-በሽር ተቃዋሚዎች አደባባይ ወጥተዋል

ሃገራቱ ነጻ ከወጡ በኋላ የገጠማቸውን አለመረጋጋት በመጥቀስ የመፈንቅለ መንግሥቱ አሃዙ ብዙም የሚያስደንቅ እንዳልሆነ ጆናታን ፓወል ይናገራል።

"የአፍሪካ ሃገራት ድህነትና የተዳከመ ኢኮኖሚን የመሳሰሉ ለበርካታ መፈንቅለ መንግሥቶች መፈጠር አመቺ የሆኑ ሁኔታዎች ይስተዋላሉ። በተጨማሪም አንዲት ሃገር አንድ መፈንቅለ መንግሥት ካስተናገደች ሌሎች መፈንቅለ መንግሥቶች ተከትለው መከሰታቸው የተለመደ ነው።"

በታሪክ እንደታየውም በአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ወታደራዊው ኃይል በስልጣን ሽግግር፣ በሃገር ውስጥ ጉዳዮችና በደህንነት መስኮች ላይ በአጠቃላይ ቁልፍ ሚናን ይጫወታሉ።

ዓለም አቀፋዊው ገጽታ

በዓለም ደረጃ ከ1952 (እኤአ) አንስቶ የተካሄዱ አጠቃላይ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አሃዝ 476 ነው።

ከዚህ አንጻር አፍሪካ ከሌሎች አህጉሮች በተለየ በርካታ መፈንቅለ መንግሥቶችን አስተናግዳለች።

ከአፍሪካ በመቀጠል ደግሞ በደቡብ አሜሪካ 95 ያህል የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች ተካሂደው 40ዎቹ ብቻ የተሳኩ ነበሩ።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ተቃውሞ በሁጎ ቻቬዝ ላይ በተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ላይ

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ በደቡብ አሜሪካ ውስጥ የተካሄዱ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች ቁጥር ቀንሷል። የመጨረሻውም ቬንዝዌላ ውስጥ በ2002 (እኤአ) በሁጎ ቻቬዝ ላይ ተሞክሮ ሳይሳካ የቀረው ነው።

ፓውል እንደሚለው በላቲን አሜሪካ ሃገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ ሰፊ ተሳትፎ የነበራቸው የአሜሪካና የሶቪየት ኅብረት ፍጥጫ ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት በኋላ መገታቱና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በ1994 ሄይቲ ላይ እንዳደረገው መፈንቅለ መንግሥት ፈጻሚዎችን ማዕቀብ በመጣል እውቅና ስለሚነፍጋቸው የወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ቁጥር እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ