የራሱን የዘር ፍሬ ተጠቅሞ 49 እናቶችን ያስረገዘው የህክምና ባለሙያ

ልጆች Image copyright Reuters

በኔዘርላንድስ የሚገኝ አንድ የስነ-ተዋልዶ ህክምና ባለሙያ የእራሱን የዘር ፍሬ በመጠቀም 49 እናቶችን ማስረገዙ ተረጋገጠ። እናቶቹ ከተለያዩ ፈቃደኛ ከሆኑ የዘር ፍሬ ለጋሾች ለመውሰድ ቢስማሙም ያለእነሱ እውቀት ይህ የስነ-ተዋልዶው ህክምና ባለሙያ የእራሱን የዘር ፍሬ ተጠቅሟል ተብሏል።

ይህ ከሁለት ዓመት በፊት ህይወቱ ያለፈው ዶክተር ኔዘርላንድ ውስጥ በሚገኘው ክሊኒኩ ከ30 ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

የዘረምል ምርመራ ውጤት እንዳረጋገጠውም የህክምና ባለሙያው ጃን ካርባት የ49 ልጆች አባት ሆኖ ተገኝቷል።

ከ49ኙ ልጆች መካከል አንዷ የሆነችው ጆይ ''ከዚህ በኋላ አባቴ ማነው ስለሚለው ማሰብ ማቆም እችላለሁ። አባቴ ከሁለት ዓመት በፊት ህይወቱ አልፏል'' ስትል እውነታውን ተቀብላዋለች። ''ከ11 ዓመታት ፍለጋ በኋላ አሁን በሰላም ህይወቴን መምራት እችላለው። አሁን ሰላም አግኝቼያለው።''

ጨው በየዓመቱ 3 ሚሊዮን ሰዎችን ይገድላል

አራት ንቦች የሰው ልጅ አይን ውስጥ ተገኙ

49ኙን ልጆች ወክሎ ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የህግ ባለሙያ ቲም ቡዌተርስ ደግሞ ጉዳዩ በፍር ቤት ተይዞ ለረጅም ዓመታት በመቆየቱ የአሁኑ የምርመራ ውጤትና ፍርድ ቤቱ ማረጋገጫ አስደስቶኛል በማለት ስሜቱን ገልጿል።

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ አብዛኛዎቹ ልጆች የተወለዱት እአአ 1980ዎቹ ውስጥ ነው።

አሁን በህይወት የሌሉት ዶክተር ካራባት በፈረንጆቹ 2017 ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ክስ ቀርቦበት ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን በወቅቱ አንደ ተከሳሹን የሚመስል አንድ ልጅ ለፍርድ ቤቱ እንደ ማሳያ ቀርቦ ነበር።

ዶክተሩም በ89 ዓመታቸው ነበር በቁጥጥር ስር ዋሉት።

ኢትዮጵያዊያን ቶሎ አያረጁም?

በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው

በወቅቱም ፍርድ ቤቱ የዘረመል ምርመራ እንዲካሄድ ትእዛዝ አስተላልፎ የነበረ ሲሆን የፍርድ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ግን ውጤቱ ለህዝብም ሆነ ለ49ኙ ልጆች ይፋ እንዳይሆን ተበይኖ ነበር።

ባሳለፍነው የካቲት ወር ፍርድ ቤቱ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ ባሳወቀው መሰረት የዘረ መል ምርመራው ውጤት ይፋ ሆኗል።