ኢቫንካ ትራምፕ አዲስ አበባ ናቸው

ኢቫንካና የሙያ ባህል አልባሳት ማምረቻ ማዕከል መስራች ሳራ አበራ Image copyright Amensisa Negera
አጭር የምስል መግለጫ ኢቫንካና የሙያ ባህል አልባሳት ማምረቻ ማዕከል መስራች ሳራ አበራ

የዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ሴት ልጅና የዋይት ሃውስ አማካሪ ኢቫንካ ትራምፕ የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ላይ ትኩረት ያደረገ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በአዲስ አበባ ጀምረዋል።

ኢቫንካ ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉብኝታቸው የመጀመሪያ ውሎ የባህላዊ አልባሳት ማምረቻ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በአሜሪካ መንግሥት የሚደገፍው እና በሥራ ቦታ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ የሚሰራው ፕሮጄክት እ.ኤ.አ 2025 ድረስ እያደጉ ባሉ ሃገራት ውስጥ የሚኖሩ 50 ሚሊዮን ሴቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

የዶናልድ ትራምፕ ልጅ በመጀመሪያ ቀን ውሏቸው በሴት የሚመራ የአልባሳት ማምረቻ ተቋምን ጎብኝተዋል።

የዓለማችን ሃብታም ሴቶች

ሰዎች ለምንድነው ምትሃት የሚወዱት?

"ኢትዮጵያ የከሸፈች ሀገር እየሆነች ነው" ሻለቃ ዳዊት

የትራምፕ አስተዳደር ፖሊሲ አፍሪካን በተመለከተ በሁለት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፤ ሽብርን መዋጋት እና የቻይናን ተጽእኖ በቅርብ መከታተል።

ትራምፕ አፍሪካን በሚመለከት ዘግየተው ይፋ ያደረጉት ይህ ፖሊሲ በበርካቶች ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም። ከዚህ ቀደም አሜሪካ ስታደርገው እንደቆየችው በአፍሪካ ዴሞክራሲ እንዲዳብር፣ ነጻ እና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ እና የሰብዓዊ መብት እንዲጠበቅ ትኩረት መሰጠት አለበት ይላሉ።

ከሁለት ወራት በፊት ይፋ የተደረገው 'ዓለም አቀፍ የሴቶች እድገት እና ብልጽግና' የተሰኘው ፕሮጄክት፣ ለሴቶች ዘረፈ ብዙ ስልጠናዎችን በመስጠት ጥሩ ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን እንዲያገኙ ይሰራል ተብሏል።

ኢቫንካ በመጀመሪያ ቀን ውሏቸው ሙያ ኢትዮጵያ የተሰኘ የአልባሳት ማምረቻ ድርጅትን ጎብኝተዋል። ድርጅቱ ከ16 ዓመታት በፊት የተመሰረተ ሲሆን ኢቫንካ ትራምፕን የድርጅቱ መስራት ሳራ አበራ አስጎብኝተዋቸዋል።

Image copyright Amensisa Negera
Image copyright Amensisa Negera
Image copyright US embassy in Ethiopia

ይህ ፕሮጀክት 'በዩ ኤስ አይ ዲ' የ50 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይደረግለታል።

ኢቫንካ ትራምፕ በኢትዮጵያ በቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

ኢቫንካ ከኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በመቀጠል ወደ አይቮሪኮስት በማቅናት የሴቶችን ኢኮኖሚ በማጠንከር ዙሪያ በሚዘጋጅ ጉባዔ ላይ ይሳተፋሉ።