የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሴት ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ ከፈተ

የባንኩ ሠራተኞች Image copyright Commercial Bank of Ethiopia FB

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አበባ፣ አትላስ አካባቢ በሴት ሠራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ መክፈቱን አስታወቀ።

ቅርንጫፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1400ኛው ቅርንጫፍ ሲሆን ከሥራ አስኪያጅ ጀምሮ በባንኩ አገልግሎት የሚሰጡት ሁሉም ሠራተኞቹ ሴቶች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

ሴቶች የተቆጣጠሩት የስፔን ካቢኔ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በልሁ ታከለ ሴቶች በአንድ አገር ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ ቢኖራቸውም የሚገባቸውን ቦታ ባለማግኘታቸው የሴቶችን ተሳትፎ ለማጎልበትና ለማበረታታት ሲባል ቅርንጫፉ እንደተከፈተ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

"ሴቶች ከወንዶች በተሻለ ደንበኞችን በጥሩ እንክብካቤ በማስተናገድ ከደንበኞቻችን ጋር ያለንን ግንኙነት ሲያጠናክሩ በተግባር አይተናል" የሚሉት አቶ በልሁ በሴቶች ብቻ የተቀላጠፈና የተደራጀ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ማሳየትም ሌላኛው ዓላማው ነው ብለዋል።

ቅርንጫፉ ከሌሎች ባንኮች የተለየ አገልግሎት ባይሰጥም የሴቶችን የሥራ ፈጠራና የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር የሴቶች የብድር አገልግሎት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ሠራተኞቹ ከተለያዩ የባንኩ ቅርንጫፎች የተውጣጡ እንደሆነም ታውቋል።

ቅርንጫፉ በኢንዱስትሪው ውስጥ ትልቅ ድርሻ ባላቸው አንጋፋ የባንክ ባለሙያ አቶ ለይኩን ብርሃኑ ተሰይሟል።

ተያያዥ ርዕሶች