በኢንተርኔት የፍቅር ጓደኛ ለማግኘት የሚረዱ ሰባት ነጥቦች

ቢጫ ቀሚስ የለበሰች ወጣት ሴት በእጇ ስልክ ይዛ ፤ እየሳቀች ስትራመድ ያሳያል Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የፍቅር ጓደኛ ለማግኘት የሚያስችለውን መተግበሪያ መጠቀም ጥሩ ነው፤ ነገርግን የፍቅር ጓደኛ በመፈለጋችሁ ደስተኛ መሆናችሁንም እርግጠኛ መሆን አለባችሁ

የከንፈር ወዳጅ አሊያም ውሃ አጣጫችን በተለያዩ አጋጣሚዎች አግኝተን ይሆናል። ሰዎች የሕይወታቸውን ሕይወት ለመፈለግ የተለያዩ ዘዴዎችን ሲጠቀሙ ማየቱም የተለመደ ነው። ቴክኖሎጂ በዘመነበት በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የፍቅር ጓደኞቻቸውን ለመፈለግ ኢንተርኔትን እንደሚጠቀሙ ታውቋል።

በኢንተርኔት የሚደረጉ የፍቅር ግንኙነት መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዓለማችን 91 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የፍቅር ጓደኛ ለመፈለግ የሚያስችሉ መተግበሪያዎችን ይጠቀማሉ፤ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ግንኙነቱ እንዲቀጥል ሲያደርጉ አይታዩም።

በእንግሊዝ ዩ ጎቭ በተሰኘ የህዝብ አስተያየትና የመረጃ ካምፓኒ ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት ምንም እንኳን 10 በመቶ የሚሆነው የእንግሊዝ ነዋሪ የፍቅር ጓደኛ መፈለጊያ መተግበሪያዎችን ቢጠቀምም አብረው የሚዘልቁት ከግማሽ የሚያንሱት ናቸው።

የጂግጂጋ ነዋሪ ጥንዶች ስጋት ላይ ነን እያሉ ነው

ሶሻል ሚድያ በተጠቃሚዎች ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ?

ፍቅር እና ግንኙነት ከቲንደር አብዮት በኋላ

በሱሴክስ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁርና የፍቅር ጓደኝነት አማካሪ የሆኑት ዞ ሰትሪምፔል እውነተኛ የፍቅር ጓደኛችንን ለመፈለግ የሚረዱ ሰባት ነጥቦችን አስቀምጠዋል

1.ወዳችሁና ፈቅዳችሁ እንጂ ተገዳችሁ በግንነት ውስጥ አትቆዩ

የተዋወቃችሁትን የፍቅር ጓደኛ ካልወደዳችሁትና እንዳልወደዳችሁት ከተሰማችሁ መቀጠሉ አስፈላጊ አይደለም። ያንን ሰው ካልወደዳችሁት ዳግም አታግኙት። እስኪ ልየው/ልያት እያሉ መሞከር አስቸጋሪ ነው፤ አንዳንዴ ስሜታችንን ይጎዳል። ስለ ራሳችን አሊያም ለሌሎች ያለን አመለካከትንም አሉታዊ እንዲሆን ያደርጉታል።

2. ልባችንን እንከተል ስሜቱን ካልተጋራችሁት አሊያም ግንኙነቱን ካልወደዳችሁት ተዉት። ግንኙነቱን ለማቆም ከወሰናችሁ ወዲያ ወለም ዘለም አትበሉ። ምንም እንኳን የእኔ ጥፋት ሊሆን ይችላል ብለን ልናስብ እንችላለን፤ ነገር ግን የዚያኛው ሰውም ስህተት ሊሆን ይችላል።

Image copyright Getty Images

3. መልዕክቶችን ወደ መለዋወጥተሻገራችሁ፤ ጥቂት መልዕክቶች ብዙ እንደሆኑ አስቡ፡

ብዙ ጊዜ በብዛትና በተደጋጋሚ መልዕክት የሚልክልን ሰው ስለ እኛ ያሰበ ሊመስለን ይችላል። ነገር ግን ስለ ብዛቱ ሳይሆን ስለ ጥራቱ ተጨነቁ። ከብዙ ያልረቡ የሃሳብ ልውውጦች ጥቂት ጥሩ የሃሳብ ልውውጦች መልካም ስሜት እንዲሰማችሁ ያደርጋል።

በአንድ ጊዜ ከ100 ሰዎች ጋር ልናወራ እንችላለን፤ ነገር ግን ከመረጣችሁትና ከወደዳችሁት ሰው ጋር ብቻ አውሩ። ወደፊት አብሯችሁ ሊዘልቅ ከሚችል ሰው ጋር ማውራቱ የተሻለ ነው።

4. ፍቅረኛ መፈለግ የቁጥር ጨዋታ ነው በመሆኑም በርካታ ሰዎች ያሉበትን ምረጡ፡

ብቻውን በበርሃ ውስጥ እንዳለ ሰው ከመሆን ይልቅ በብዙ ሰዎች ተከበቡ። ከዚያም አንዱን መርጣችሁ ከእርሱ ጋር በፍቅር የመውደቅ እድል ይኖራችኋል። በመሆኑም አልማዙን ለማግኘት አፈሩን ማግኘት አለባችሁ። አቋራጭ መንገድም የለም።

5.መጀመሪያ ተራ ጓደነትን ማሰብ ስለ ፍቅር ጓደኝነት ስናስብ መጀመሪያ ስለ ጓደኝነት ማሰብ ግድ ይላል። በጓደኝነት የተጀመረ ግንኙነት መጨረሻውም ያማረ ይሆናል ፤ ወደ የህይወት አጋርነት የመቀየር አዝማሚያው ሰፊ ነው።

ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች

6. ደረቅ አትሁኑምን እንደሚማርካችሁና እንደማይማርካችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ። ይሁን እንጂ 'ከዋክብቶችን ስትቆጥር ጨረቃውን ታጣለህ' እንደሚባለው ምርጫችሁን በጣም ካጠባባችሁት እናንተን አጥብቆ የሚፈልገውን ሰው ልታጡት ትችላላችሁ። ውሃ አጣጭን በሂሳብ ስሌት ማግኘት አይቻልምና።

7. ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባችሁ አትዘንጉ

በተለይ በድረ ገፅ የሚመሰረቱ ግንኙነቶች ደስታን ሊሰጧችሁ ይችላሉ፤ ነገር ግን ምርምርና ጥንቃቄ ማድረጋችሁን ማቆም የለባችሁም። በጥርጣሬና በጥንቃቄ ነገሮችን መከታታል ያስፈልጋል።

በአብዛኛው የበይነ መረብ የፍቅር ጓደኛ መተግበሪያዎች ችግር የምትመርጡትን ሰው እንጂ የእርሱን ጓደኛ አሊያም ዘመድ አዝማድ የማወቅ እድሉ አይኖርም። የጋራ ጓደኛ ስለማይኖር ስለዛ ሰው ማንነት ከሌላ ወገን ለመስማትና ለማወቅ እድል አይሰጥም።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ