ዘንድሮ በዓለም ላይ የኩፍኝ ወረርሽኝ በሦስት እጥፍ ጨምሯል- የተባበሩት መንግሥታት

የሚከተብ ሕፃን Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት መረጃዎች እንደሚያሳዩት "በአስደንጋጭ መልኩ እየተዛመተ" መሆኑን ነው

በዓለማችን ላይ በ2019 የመጀመሪያ ሦስት ወራት ብቻ የተመዘገቡ የኩፍኝ ሕሙማን ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀር በሦስት እጥፍ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ተናገረ።

ይህ የተባበሩት መንግሥታት አካል የሆነው ድርጅት እንዳስታወቀው ያሉት መረጃዎች መላው ዓለም የኩፍኝ ወረርሽኝ ሊያጋጥመው እንደሚችል የሚያሳዩ ናቸው።

ወረርሽኙ በአፍሪካ በ700 በመቶ ጭማሪ ነው ያጋጠመው።

በኢትዮጵያ የኩፍኝ ክትባት ያልተከተቡ ህፃናት ቁጥር ከፍተኛ ነው

አለማችን የኩፍኝ ወረርሽኝ እንደሚያሰጋት አለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ

ድርጅቱ አክሎም ትክክለኛው የታማሚዎች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ ይችላል ሲል ስጋቱን አስቀምጧል፤ ለዚህም ምክንያት ብሎ ያቀረበው በዓለም ላይ ከ10 ታማሚዎች መካከል ሪፖርት የሚደረገው የአንዱ ብቻ መሆኑን ነው።

ኩፍኝ ተላላፊ የሆነ በሽታ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ለከፋ የጤና ችግር ሊያጋልጥ ይችላል።

በወረርሽኙ ክፉኛ ከተጠቁ ሃገራት መካከል ዩክሬን፣ ማዳጋስካር፣ እና ሕንድ ይገኙበታል። በማዳጋስካር ብቻ ከመስከረም ወር ጀምሮ 800 ሰዎች በኩፍኝ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ወረርሽኙ ብራዚልን፣ ፓኪስታንና የመንንም "በርካታ ታዳጊ ሕፃናትን ለሞት በመዳረግ" አጥቅቷል።

እያነጋገረ ያለው የአማራ ክልል የቤተሰብ ዕቅድ ደብዳቤ

በአሜሪካና በታይላንድ በከፍተኛ ቁጥር ክትባት የማዳረስ ሥራ እየተሠራ መሆኑ ተዘግቧል።

የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ ኩፍኝ ተገቢውን ክትባት ከተሰጠ "ልንከላከለው የምንችለው" ወረርሽኝ ቢሆንም የክትባት መድኃኒት እጥረት አለ ብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅትን የሚያስተዳድሩት ቴዎድሮስ አድሃኖምና ባልደረባቸው ለሲኤን ኤን እንደተናገሩት ዓለም በኩፍኝ ወረርሽኝ ስጋት ውስጥ ናት፤ ለዚህም ስለ ክትባቱ እርስ በእርሳቸው የሚጋጩና የተሳሳቱ መረጃዎች የእራሳቸውን አስተዋፅዖ አድርገዋል ብለዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ