ሴኔጋላዊ ወንዶችን ልጅ እንዲያዝሉ ያደረገችው የፎቶ ባለሙያ

Image copyright Marta Moreiras
አጭር የምስል መግለጫ የሲቪል መኃንዲሱ ቢራማና ልጁ ንዴዬ

በሴኔጋል መዲና ዳካር ጎዳናዎች ላይ ወንዶች ልጆቻቸውን በጀርባቸው አዝለው ፎቶ ማንሳቷ ይህንን ያህል ግርምት ይፈጥራል ብላ ባታስብም ከማህበረሰቡ ያገኘች አድናቆት እንዳስደመማት የፎቶ ባለሙያዋ ማርታ ሞሬይራስ ትናገራለች።

በጎዳናዎች ላይ ፎቶ በምታነሳበትም ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ባለው ሕዝብ ተከብባ የነበረ ሲሆን ይሄም ለሥራዋ አስቸጋሪ እንደነበር ስፔናዊቷ የፎቶግራፍ ባለሙያ ትናገራለች፤ "የሚያጨበጭቡ ነበሩ፤ በአንዳንድ አጋጣሚም የተሰሰበው ሕዝብ ከፍተኛ በመሆኑ ፎቶ ለማንሳት እክል ፈጥሮብኝ ነበር" ብላለች።

"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው"

አክላም "መንገድ ላይ ፎቶ ሳነሳ የሚያገኙኝ ሴቶች በሙሉ በደስታ ጨብጠውኝ 'እንዲህ ዓይነት ነገር በየቀኑ እኮ አያጋጥምም፤ እስቲ ባሌን ልደውልለት' ይሉኛል።

ሥራዎቿ በዚህ ዓመት የሶኒ ዓለም አቀፍ የፎቶ ሽልማት ላይ ለእጩነት ከተመረጡት መካከል ሲሆኑ ሃሳቡም የመጣላት ሴኔጋልን ከ11 ዓመታት በፊት በጎበኘችበት ወቅት ያነሳቻቸውን ፎቶዎች ስታገላብጥ አብዛኛው የፎቶዎቿ ስብስብም ሴቶች ልጆች አዝለው የሚያሳይ የነበረ ሲሆን፣ ያም ወንዶች ለምን እንደማያዝሉም ጥያቄ እንዳጫረባት ትናገራለች።

"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

ኩምባ ከልጇ ቢንታ ጋር Image copyright Marta Moreiras
አጭር የምስል መግለጫ ኩምባ ከልጇ ቢንታ ጋር

ሴኔጋል የሚገኙ ወንዶች ጓደኞቿም ጋር በመደወል ልጆቻቸውን ያዝሉ እንደሆነ በምትጠይቅበት ወቅትም ያገኘችው ምላሽም በቤት ውስጥ እንደሚይዙ ነገር ግን በአደባባይ በፍፁም እንደማያዝሉ ነው።

የፋይንናንስ አማካሪው ዴምባና ልጁ ኤሊ Image copyright Marta Moreiras
አጭር የምስል መግለጫ የፋይንናንስ አማካሪው ዴምባና ልጁ ኤሊ

ያደረገችው ጥናትና ቃለ መጠይቆች እንደሚያሳየው ዳካር በጣም ውድ ከሚባሉት ከተሞች አንዷ በመሆኗና ባልና ሚስቱም ውጭ ሥራ ስለሚሠሩ ባሎች ልጅ የመንከባከቡን ሚና እንደሚወጡ ነው።

ያነጋገረቻቸው ወንዶች እንደገለፁላት ከሆነ የቤት ውስጥ ሥራዎችን ተከፋፈለው ይሠራሉ። ብዙዎቹ ልጅ የመንከባከቡንም ሆነ፣ የማስጠናቱን ጉዳይ ለባለቤቶቻቸው እንደማይተዉና በከፍተኛ ሁኔታ ይሳተፋሉ።

አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው?

"ባለቤቴም እንደኔ ውጭ ትሠራለች፤ እና የቤቱን ሥራ እንዴት ብቻዋን ትወጣዋለች?" በሚልም አንደኛው አስተያየቱን ሰጥቷል።

"ምንም እንኳን ወንዶች በልጆች አስተዳደግ ላይ ቢሳተፉም አባቶች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ፣ ትምህርት ቤት ሲወስዷቸው ወይም ሲያጥቧቸው አይታዩም" ትላለች።

የቪዲዮ ባለሙያው ሼክና ልጁ ዞ Image copyright Marta Moreiras
አጭር የምስል መግለጫ የቪዲዮ ባለሙያው ሼክና ልጁ ዞ

ያነጋገረቻቸውን አባቶችም የአባትነት ሚናቸውን ሲወጡ በሚያጎላ መልኩ ፎቶ ማንሳትም ጀመረች።

የኮምፒውተር ባለሙያው ጁልስና ልጁ ጄድ Image copyright Marta Moreiras
አጭር የምስል መግለጫ የኮምፒውተር ባለሙያው ጁልስና ልጁ ጄድ

በመጀመሪያ ልጆቻቸውን አቅፈው ፎቶ ለመነሳት ሲስማሙ፤ አዝላችሁስ ብላ በምትጠይቅበት ወቅት በአብዛኛው ያገኘቸው ምላሽ ልጆች አዝለን ጎዳና ላይ አንወጣም የሚል ቢሆንም ማርታ ተስፋ ሳትቆርጥ ቀስ በቀስ ምቾት ሰጥቷቸው እንዲነሱ እንዳግባባቻቸው ትናገራለች።

የሙዚቃ ፕሮዲውሰሩ ሙላየና ልጆቹ ሐሰንና ማሊክ Image copyright Marta Moreiras
አጭር የምስል መግለጫ የሙዚቃ ፕሮዲውሰሩ ሙላየና ልጆቹ ሐሰንና ማሊክ

ፎቶዎቹን ለማንሳት እሰከ ሦስት ወር የፈጀባት ሲሆን ባለፈው ዓመትም በነበረው በጥበቡ ዓለም ከፍተኛ ስፍራ በሚሰጠው የዳካር ኮንቴምፖራሪ ዓውደ ርዕይም ላይ ሥራዎቿን አቅርባለች።

ሥራዎቿም በአውደ ርዕዩ ላይ መነጋገሪያ ሆነው ነበር።

የፎቶ ባለሙያው ማህሙድና ልጁ ዘካሪያ Image copyright Marta Moreiras
አጭር የምስል መግለጫ የፎቶ ባለሙያው ማህሙድና ልጁ ዘካሪያ

ፎቶዎቿ በማህበረሰቡ አመለካከት ላይ የተለየ ሃሳብን መፈንጠቅ የቻለ ሲሆን በተለይም ታዋቂው ራፐር ባዱ መሳተፍ ከፍተኛ ተፅዕኖን መፍጠር ችሏል።

ታዋቂው ራፐር ባዱና ልጁ ማህሙድ Image copyright Marta Moreiras
አጭር የምስል መግለጫ ታዋቂው ራፐር ባዱና ልጁ ማህሙድ

"በማህበረሰቡ ዘንድ ስመጥር የሆኑ ወንዶች መሳተፋቸው ለብዙዎች አርዓያ ከመሆኑም በላይ ወንዶች ልጆች ማዘላቸው ምንም ማለት አይደለም የሚለውን ውይይት ለመፍጠር ምክንያት ሆኗል" ትላለች ማርታ

ሌሎች ታዋቂ ሰዎችንም በፎቶዎቿ እንዲካተቱ ብትጠይቅም ለስማቸው ፈርተው አይሆንም እንዳሏትም ትናገራለች።

የእንጨት ዲዛይነሩ ስኮርፒዮንና ልጁ አፍሪካ Image copyright Marta Moreiras
አጭር የምስል መግለጫ የእንጨት ዲዛይነሩ ስኮርፒዮንና ልጁ አፍሪካ

ፎቶዎቹ የተገኙት ከማርታ ሞሬይራስ ነው

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ