ዓለም አቀፍ የወባ ቀን፡ ወባ ምንድን ነው? እንዴትስ እናስቁመው?

የምትናከስ ቢምቢ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ወባ የሚተላለፈው በታመሙ ቢምቢዎች ነው

ወባን እንዴት እናስቁመው?

ወባን መከላከል ቀላል ሆኖ ቢታይም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለ በሽታ ነው። የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት ወባ በየሁለት ደቂቃዎች አንድ ሕፃን ሲገድል በየዓመቱ ከ200 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ በወባ እንደሚያዙ ያሳያል።

ባለፉት አሥርት ዓመታት ውስጥ ለውጦች ቢመዘገቡም እ.አ.አ ከ2015 ወዲህ ግን ወደፊትም ወደ ኋላም እየሄድን አይደለም ይላል ያለፈው ዓመት የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት። ቁጥሩ ባለፉት ሦስት ዓመታት ምንም ዓይነት ለውጥ እንዳላሳየ ሪፖርቱ ያመለክታል።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ወባን መከላከል እና ማዳን ቀላል ነው

ዛሬ ዓለም አቀፍ የወባ ቀን ነው። ስለ ወባ ምን ማወቅ አለብዎት?

  • አራት ከተለያዩ ፕላስሞድየም በሚባሉ የፓራሳይት ዓይነቶች የሚተላለፍ ከባድና ሞት አስከታይ በሽታ ነው።
  • አራቱ ፓራሳይቶች፡ ፕላስሞድየም ፋልሲፓረም፣ ፕላስሞድየም ማላሪዬ፣ ፕላስሞድየም ኦቫሌ እና ፕላስሞድየም ቪቫክስ ናቸው።
  • በፓራሳይቶቹ በተያዙ ወባ አስተላላፊ እንስት ቢምቢዎች ከተነከሱ ወባዎች ይይዝዎታል።
  • በሽታውን መከላከልም ሆነ ማዳን ይቻላል።
  • እ.አ.አ በ2017 በ87 ሃገራት ወደ 219 ሚሊየን በወባ የተያዙ ሰዎች ነበሩ። (ከዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት)
  • እ.አ.አ በ2017 ብቻ በግምት በወባ የተያዙ 435 000 ሰዎች ሞተዋል።
  • አፍሪካ በወባ ምክንያት ከዓለም ከፍተኛው ሸክም ያለባት አህጉር ናት፡ በአጠቃላይ እ.አ.አ በ2017 92% የአፍሪካ ነዋሪዎች በወባ የተያዙ ሲሆን፤ 93% የሚሆኑት ደግሞ ሞተዋል።
  • በአጠቃላይ ለማላሪያ እ.አ.አ በ2017 የተሰበሰበው ገንዘብ 3.1 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል።

ምልክቶች

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ የሚል ስሜት እና እራስ ምታት

የወባ ምልክቶች ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ የሚል ስሜት እና እራስ ምታት ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ በቢምቢ ከተነከሱ ከ10 እስከ 15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ነው ምልክቶቹ የሚታዩት።

ምልክቶቹን ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም በታዩ በ24 ሰዓታት ውስጥ ካልታከመ ፕላስሞድየም ፋልሲፓረም የተሰኘው ፓራሳይት ወደ ከባድ፣ የማይታከምና ለሞት የሚዳርግ በሽታ የመሸጋገሩ ዕድል ሰፊ ነው።

ማንን ሊያጠቃ ይችላል?

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የታመመች ሕፃን

እ.አ.አ በ2017 የዓለም ግማሽ ያህል ነዋሪዎች በወባ ተይዘው ነበር።

ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት ተጠቂ የመሆናቸው ዕድል በጣም ሰፊ ነው። በፈረንጆቹ 2017 ብቻ በዓለም 61% ወይም 266 000 ሕፃናት በወባ ሞተዋል።

እርጉዝ ሴቶች እና የተፈጥሮዓዊ መከላከያቸው የተዳከመ ሰዎችም በወባ የመያዝ ዕድለቸው ከፍተኛ ነው።

ወባ በየት አካባቢዎች ይበዛል?

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ከምድር ወገብ በታች ያሉ ሃገራትና በተለይ አፍሪካ ተጋላጭ ናቸው

ብዙውን ጊዜ ከሳሐራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራት ተጋላጭ እንደሆኑ ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት ይገልፃል። በተጨማሪ ደቡብ ምሥራቅ እስያ፣ ምሥራቅ ሜዲትራኒያዊ፣ ምዕራብ ፓስፊክ ውስጥ እና በአሜሪካዎቹ ያሉ ሰዎች ተጋላጭ መሆናቸውንም ይገልፃል።

እ.አ.አ በ2017 ከተመዘገቡት በወባ ከተጠቁ ሰዎች መካከል ግማሹን ያስመዘገቡት አመስት ሃገራት ብቻ ነበሩ። እነርሱም ናይጄሪያ (25%)፣ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ (11%)፣ ሞዛምቢክ (5%)፣ ሕንድ (4%) እና ዩጋንዳ (4%) ናቸው።

እንዴት ይተላለፋል?

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ፓራሳይቱን ተሸካሚ የሆነች አስተላለፊ ቢምቢ

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎችን ማላሪያ የሚይዛቸው ፓራሳይት ተሸካሚና አስተላላፊ በሆነች ሴት አኖፌሌስ በተሰኘች ቢምቢ ሲነከሱ ነው። የአኖፌሌስ ቢምቢ ብቻ ከ400 ዘር በላይ ሲሆን ከእነሱ መካከል 30ዎቹ ብቻ ናቸው ወባ የሚያስተላልፉት።

ሁሉም የማላሪያ ተሸካሚና አስተላላፊ የሆኑ ቢምቢዎች ሌሊቱ ሊነጋጋ ሲል የሚናከሱ ናቸው።

አኖፌሌስ የተሰኙት ቢምቢዎች እንቁላሎቻቸውን በውሃ ላይ የሚወልዱ ሲሆኑ፤ እንቁላሎቹ ወደ እጭ ተቀይረው ሰብረው ሲወጡ ሙሉ በሙሉ ያደገ ቢምቢ ሆነው ይወጣሉ። ወላጅ ቢምቢዎች እንቁላሎቻቸውን ለማሳደግ ደም ይመግቧቸዋል ማለት።

መከላከያ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ብዙዎች የወባ መድሃኒት በተረጩ አጎበሮች መትረፍ ችለዋል

ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት መድሃኒት በተረጩ አጎበሮች ሥር መተኛት ከቢምቢዎቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ስለሚቀንስ በጣም ውጤማ መሆኑን ይናገራል። ከአጎበሩ በተጫመሪ ደግሞ የመኖሪያ ስፍራዎችን መድሃኒት መርጨትም ጠቃሚና አንደኛው የመከላከያ መንገድ መሆኑን ይናገራል።

በተለያየ ጊዜ መድሃኒቱን ከመርጨት ባሻገር ለሚጓዙ ሰዎች የሚዋጡ መድሃኒቶችን መውሰዱም በጣም ጠቃሚ የሆነ የወባ መከላከያ መንገድ እንደሆነ ይገለፃል።

ሕክምናው

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ በሽታውን ቶሎ መለየትና መታከም ጠቃሚ ነው

ጥርጣሬ ካለ ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ በግማሽ ሰዓት ውስጥ ውጤቱን ማወቅ እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ። አንድአንድ የሕክምና ማዕከላት ደግሞ ተገቢው መሣሪያ ካላቸው ከዚያም በታች እንደሚወስድባቸው ይናገራሉ።

በሽታውን በፍጥነት ለይቶ ማወቁ ወባው ከፍ ወዳለ ደረጃ ወይም ሞትን ወደ ማስከተል ሳይደርስ መከላከል ይቻላል።

ፕላስሞድየም ፋልሲፓረም ለተሰኘው ፓራሳይት አርቴሚሲኒን ያለው መድሃኒት ጥሩ መሆኑንም ይገልፃሉ።

መድሃኒት ተቋቋሚ ፓራሳይቶች

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ማላሪያ የያዘ ደም

ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት አኖፌሌስ የተሰኘው ቢምቢ የተባዮች መከላከያ መድሃኒቶችን ከመለማመዳቸው የተነሳ እየጠነከሩ መምጣታቸውን አስጠንቅቋል። ይህ ደግሞ ወባን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት እያኮላሸ መሆኑን አስታውቋል።

በቅርብ ጊዜ የወጣ ሪፖርት በ68 የተለያዩ ሃገራት ያሉ ቢምቢዎች በተለምዶ አገልግሎት ላይ ይውሉ የነበሩ አምስት መድሃኒቶች ተላምደው እንደማይሞቱ ይነግራል።

ከዚያም በተጨማሪ ፀረ-ወባ የሆኑ መድሃኒቶችም በልምምድ ምክንያት ሃይላቸው እየቀነሰ ነው።

ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት ወባን ለመከላከልና ለማዳን ያላቸው አቅም ሰፊ በመሆኑ መድሃኒቶች ላይ ብዙ ሥራ መሠራት አለበት ይላል።

የመድሃኒቱ መዳከም እንደታወቀ ጥናት ቢደረግ በፍጥነት ሌላ ውጤት የሚያመጣ ሊሠራ እንደሚችል ይናገራል።

DO NOT DELETE OR TRANSLATE! Digihub tracker for [48021789]

ተያያዥ ርዕሶች