ስራቸው ለሞት የዳረጋቸው ጋዜጠኞች

ዳፊን ካሩና ጋሊዚያ Image copyright Reuters

ቢያንስ በሶስት ወይም በየአራት ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ግለሰብ ከእናቴ ሞት ጋር በተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ወደ ቤታችን ይመጣል። ቤተሰባችን ይህንን ግለሰብ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየው ከስድስት ዓመት በፊት እናታችንን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲመጣ ነበር።

እናቴ በወቅቱ ማልታ ውስጥ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እየተወዳደሩ ስለነበሩት ግለሰብ ቀልድ አዘልና ፖለቲካዊ መልእክት ያለው ጽሁፍ አቅርባ የነበረ ሲሆን አንድ ሰው ቅሬታውን ለፖሊስ አሳውቆ ነበር።

የጋዜጠኛው አስክሬን 'በአሲድ እንዲሟሟ ተደርጓል'

'ለሼህ አላሙዲ መፈታት የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር'

በዛው ቀን ምሽትም ይሄ ሁሌም ወደቤታችን የሚመጣው ፖሊስ ከፍርድ ቤት የተጻፍ ደብዳቤ ይዞ በሌሊት መጣ። እናቴን በቁጥጥር ስር አውሎ ይዟት ሄደ። የቀረበባትም ክስ በህገወጥ መንገድ ሃሳብን መግለጽ ነበር።

ከሰአታት በኋላም መለቀቋን የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ተመለከትኩ። በወቅቱ የአባቴን ቲሸርት ለብሳ የነበረ ሲሆን ጸጉሯም ቢሆን እንደተንጨባረረ ነበር። ነገር ግን ወደቤት እንኳን ሳትመጣ ስለደረሰባት ነገርና ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ መጻፏን ቀጠለች።

እናቴ በተገደለችበት ቀን አንድ የመንግስት ሚኒስትር የባንክ ደብተሯን እንዳታንቀሳቅስ አግዶባት ስለነበር እሱን ለማስተካከል ወደ ባንክ ቤት ሄደች። ነገር ግን ከባንክ ወጥታ ወደመኪናዋ ስትገባ ግማሽ ኪሎግራም የሚመዝን ተቀጣጣይ ፈንጂ ከመኪናዋ ስር ተቀምጦ ነበር።

የ53 ዓመቷ ዳፍኒ ካሩዋና ጋሊዚያ የተጠመደው ቦምብ ፈንድቶ እዛው ህይወቷ አለፈ። ይህንን ታሪክ የሚተርከው ማቲውና ወንድሙ ፖል ያለእናት ቀሩ።

በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበረው መንግስት ደጋፊዎች በእናቴ መሞት የተሰማቸውን ደስታ በይፋ ይገልጹ ነበር ይላል ማቲው። ሌሎችቸ ደግሞ በገዛ ፈቃዷ ህይወቷን እንዳጣች ይናገሩ ነበር። እናቴ ግን ለማልታ ነጻነት እየታገለች ነው ህይወቷ ያለፈው።

የዳፍኒ ካሩዋና ጋሊዚያ አሟሟት

  • ጥቅምት 2017 መኪናዋ ውስጥ በተጠመደ ፈንጂ ህይወቷ አለፈ
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ መስካት ግድያውን አረመኔያዊ በማለት አወገዙት። ቤተሰቦቿም ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን በቀብር ስነስርአቱ ላይ እንዳይገኙ አገዱ።
  • ታህሳስ 2017 ከዳፍኒ ግድያ ጋር በተያያዘ ሶስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
  • ሃምሌ 2018 ዳፍኒ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ባለቤታቸው ላይ አቅርባው የነበረውን የሙስና ክስ የሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገው።

የዓለማቀፍ ፕሬስ ነጻነት ቀን

  • የዓለማቀፉ ፕሬስ ነጻነት ቀን መከበር የጀመረው የተባበሩት መንግስታት በአውሮፓውያኑ 1993 በየዓመቱ ሚያዝያ ወር ላይ እንዲከበር ከወሰነ በኋላ ነው።
  • የዘንድሮው በአል ዋና ነጥብም ጋዜጠኝነት፣ ምርጫና የተሳሳተ መረጃ ላይ ያተኮረ ነው።
  • የቀኑ መከበር ዋና አላማ የነጻ ፕሬስ ሁኔታዎችን ማስከበርና መገምገም ሲሆን በጋዜጠኝነታቸው ብቻ የተገደሉትን ማስታወስንም ያካትታል።
  • ባለፈው ዓመት ብቻ በሰሯቸው የምርመራ ዘገባዎችና በጦርነቶች ምከንያት 95 ጋዜጠⶉች ህይወታቸውን አጥተዋል።

ጋዜጠኝነትና በህይወት ላይ ስለሚደርስ አደጋ ሲወራ ደግሞ በሁላችንም ጭንቅላት ቀድሞ የሚመጣው በቅርቡ ቱርክ ውስጥ የተገደለው የሳኡዲ ዜግነት ያለው ጋዜጠኛ ጃማል ሃሾግጂ ነው።

ጀማል በሳዑዲ ዝነኛ ጋዜጠኛ ነበር፤ የሶቪየት ሕብረት የአፍጋኒስታን ወረራን በዝርዝር ዘግቧል። እንደ ኦሳማ ቢን ላደን ከመሳሰሉ ግለሰቦች ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
በቅርቡ ለመጋባት እቅድ እንደነበራቸው የምትናገረው የኻሾግጂ እጮኛ ከባድ ሃዘን ውስጥ ናት።

ለበርካታ አስርት ዓመታት ለሳዑዲ ንጉሳውያን ቤተሰብ የቅርብ ሰው ነበር፤ የሳዑዲ መንግሥት የመገናኛ ብዙሃን አማካሪ ሆኖም ሰርቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከሳዑዲ መንግሥት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ሃገር ጥሎ ወደ አሜሪካ ተሰደደ። በጽሑፎቹም የሳዑዲ አረቢያውን ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማንን ይተች ነበር።

ዕጽ በማዘዋወር የተጠረጠረችው ናይጄሪያዊት ከእስር ተለቀቀች

ኢስታንቡል በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ቆንስላ ውስጥ እንደተገደለ የታመነው ሃሾግጂ ወደ ቅጥር ግቢው እንደገባ ነበር ታንቆ የተገደለው ይላል የቱርክ መንግስት የሰጠው መግለጫ።

ከዚያም የጋዜጠኛው በድን አካል ተቆራርጦ እንዲጠፋ ተደርጓል።

በወቅቱም የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን «ሃሾግጂ እንደ አደገኛና አክራሪ ኢስላሚስት ነው የማየው» ብለው ተናግረው ነበር። የሃሾግጂ ቤተሰቦች ግን ጃማል የማንኛውም አክራሪ ቡድን አባል እንዳልነበር ገልፀዋል።

«ጃማል ሃሾግጂ ምንም ዓይነት አደጋ ሊያመጣ የሚችል ሰው አልነበረም፤ እሱን አደገኛ ማለት እንደመሳለቅ ነው» የሚል መግለጫም አውጥተው ነበር።