የቦስኒያ ጦርነት፡ በጦርነት ወድሞ የነበረው አላድዛ መስጊድ ተከፈተ

አላድዛ መስጊድ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ አላድዛ መስጊድ ሙሉ በሙሉ ከወደመ ከዓመታት በኋላ እንደገና ተገንብቷል

በአውሮፓውያኑ ከ1992-1995 በቦስኒያ በተካሄደው ጦርነት የወደመው የአላድዝ መስጊድ ጥገና ተደርጎለት ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ እንደገና ተከፈተ።

ቦስኒያ በሚገኘው በዚህ መስጊድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመገኘት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን ታድመዋል።

በፎካ ከተማ የሚገኘው አላድዛ መስጊድ በቦስኒያ እና ሰርቢያ መካከል የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ በማሰብ ነበር ኢላማ የተደረገው።

በፆም ወቅት ሰውነታችን ውስጥ ምን ይካሄዳል?

በ16 ኛው ክፍለዘመን በኦቶማን የኪነ ህንፃ ጠበብቶች የተሠራ እንደሆነ የሚነገርለት መስጊዱ በጦርነቱ ከወደመ በኋላ መልሶ ለመገንባት ዓመታትን የወሰደ ሲሆን ቱርክን ጨምሮ ሌሎች አገራት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። በጦርነቱ በፈንጂ እስኪወድምም ድረስ አገልግሎት ይሰጥ ነበር ተብሏል።

በፍንዳታው የወደቀው ዋናው የመስጊዱ አካል በድንጋይ የተገነባ ሲሆን በአደጋው የፈራረሱትንና የተዳፈኑት በቁፋሮ እንዲወጡ ተደርገዋል።

በጦርነቱ ወቅት በፎካ ከተማ ሰርቢያን ያልሆኑ ሰዎች ግድያ ይፈፀምባቸው ነበር። በዚህም ሳቢያ ይህ አካባቢ ሰርቢንጂ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2004 የቦስኒያ ፍርድ ቤት የቀድሞ ስሟ እንዲመለስላት ውሳኔ አስተላልፈዋል።

የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ 'ጀሐነም' ሲጋለጥ

ታዲያ በዛሬው ዕለት በቦስኒያ የሚገኙ ህዝበ ሙስሊሞችም የመስጊዱን በድጋሜ መከፈት በድምቀት እያከበሩ ይገኛሉ።

" ዛሬ ሰዎች በዚህ አካባቢ ሰላም እንዳገኙና ደህንነታቸው እንደተመለሰላቸው ለማየት ችለናል " ሲሉ የቡድኑ መሪ ሁሴን ካቫዞቪቸ በዝግጅቱ ላይ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

የቱርክ የባህል ሚንስትር መህምት ኑሪ ኢርሶይ በበኩላቸው "ጥላቻና ዘረኝነት ቁሳቁስን ሊያወድም ይችላል፤ ነገርግን የነበረን ባህልና ኃይማኖት ማጥፋት ግን አይችልም " ብለዋል በዝግጅቱ ላይ።

በቦስኒያ የአሜሪካ መልዕክተኛም "ይህ መስጊድ ለወደፊቱን ትውልድ ተስፋን የሚሰጥና የሚያስተሳስር ነው" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ባለፈው ዓመት የቀድሞው የቦስኒያ ሰርብ ወታደር ፈንጂ በመቅበር ተሳትፈሃል ተብሎ ክስ እንደቀረበበት ይታወሳል።

ፎካ ከተማ ከጦርነቱ በፊት ካላት 41 ሺህ ገደማ የህዝብ ብዛት ግማሽ ያህሉ ሙስሊም ሲሆኑ አሁን ግን ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ ያነሰ እንደሆነ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ