አሜሪካ፡ በቁንጅና ውድድር ያሸነፉት ጥቁር ሴቶች

ከግራ ወደ ቀኝ ካሌግ ጋሪስ፣ ቸስሊ ክርይስት፣ ኒያ ፍራንክሊን Image copyright Instagram
አጭር የምስል መግለጫ ከግራ ወደ ቀኝ ካሌግ ጋሪስ፣ ቸስሊ ክርይስት፣ ኒያ ፍራንክሊን

በዚህ ዓመት በአሜሪካ በተካሄደው የቁንጅና ውድድር ላይ ያሸነፉት ሦስቱም ሴቶች ጥቁሮች ናቸው። የ25 ዓመቷ ኒያ ፍራንክሊን ባለፈው መስከረም ወር የተመረጠች ሲሆን የ18 ዓመቷ ካሊን ጋሪስ እርሷን በመከተል፤ በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል በሚገኙት ዘርፍ ወ/ሪት አሜሪካ ተብላ ተመርጣለች። ቸስሊ ክርይስት ደግሞ ወ/ሪት ዩ ኤስ ኤ ተብላ አሸናፊ ሆናለች።

የእነርሱ ማሸነፍ በዘረኝነትና በአድሏዊነት ለአስርት ዓመታት የዘለቀውን አስተሳሰብ በማስወገድ ረገድ ትርጉም ተሰጥቶታል።

ፕሬዚዳንቱ የቁንጅና አሸናፊዋን በተፈጥሮ ፀጉሯ ልታጌጥ ይገባል ሲሉ ተቹ

"ውድድሩን ማሸነፌ አካታችነት፣ ልዩነት፣ ጥንካሬ እና የሴቶች ብቃት ላይ የነበረውን የተዛባ አስተሳሰብ ለመቀየር የሚያስችል ነው" በማለት ከአሸናፊዎቿ አንዷ የሆነችው ወ/ሪት ክሪስት ሽልማቷን ስትቀበል ተናግራለች።

ክሪስት በሰሜን ካሮሊና ግዛት የህግ ባለሙያ ስትሆን በእስረኞች ላይ የሚደርስ ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራርን በመሟገትም ትታወቃለች።

ሌላኛዋ አሸናፊም ወ/ሪት ፍራንክሊን እንዲሁ የኦፔራ ሙዚቃ አቀንቃኝ ስትሆን ሆፕ በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅትም ጥበብ ለማህበራዊ ለውጥ ያለውን አስተዋፅኦ ታስተዋውቃለች።

ከዚህም በተጨማሪ በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል የምትገኘው ወ/ሪት ጋሪስ እና ክሪስት የራሳቸውን ተፈጥሯዊ ፀጉር አጊጠው ነበር መድረክ ላይ የታዩት።

በአውሮፓውያኑ 2020 ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሴናተር ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ካማላ ሃሪስ ውድድሩን አስመልክተው "ለእነዚህ ወጣትና ስኬታማ ሴቶች ህልማቸውን ለማሳካት በጣም ወሳኝ የሆነ ጊዜ ነው" ሲሉ በኢንስታግራም ሃሳባቸውን አስፍረዋል።

ሩሲያዊው ቄስ በባለቤታቸው "ሀጥያት" ለስደት ተዳረጉ

በአውሮፓውያኑ 1983 ቬኔሳ ዊሊያም የቁንጅና ውድድርን በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ነበረች።

ወ/ሪት ዊሊያምስ ወ/ሪት አሜሪካ ተብላ የቁንጅና ዘውዱን ከጫነች በኋላ እስከ አውሮፓውያኑ 1990 ድረስ ሌላ አሸናፊ የሆነች ጥቁር ሴት አልነበረችም። በአውሮፓውያኑ 1990 ግን ሌላ ጥቁር አሜሪካዊት ማሸነፍ ችላለች።

ወ/ሪት አሜሪካ ውድድር ከቀዳሚዎቹ የቁንጅና ውደድሮች አንዱ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 1921 ነበር የተጀመረው። ወ/ሪት ዩ ኤስ ኤ ደግሞ በአውሮፓውያኑ 1950 ተጀመረ። ከዚያም በዚሁ ተመሳሳይ ዓመት በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሴቶች የቁንጅና ውድድር ተጀምሯል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ