አሲያ ቢቢ፡ ከዓመታት እስር በኋላ ፓኪስታንን ለቃ ወጣች

አሲያ ቢቢ
አጭር የምስል መግለጫ አሲያ ቢቢ ክስ ከተመሰረተባት በኋላ ዓመታትን በእስር አሳልፋለች

በእስልምና ኃይማኖት ላይ ስድብ ሰንዝረሻል ተብላ ክስ የተመሰረተባት ፓኪስታኒያዊቷ ክርስቲያን አሲያ ቢቢ ከእስር ከተለቀቀች በኋላ ፓኪስታንን ለቃ መውጣቷን ባለስልጣናት አረጋገጡ።

ፓኪስታን ክርስትያኗን ቢቢን ከእስር ለቀቀች

አሲያ ቢቢ ሙልታን በአውሮፓውያኑ 2010 ነበር እስልምና ኃይማኖትንና ነብዩ መሐመድ ላይ ስድብ ሰንዝረሻል በሚል የተከሰሰችው።

ዓመታትን በእስር ያሳለፈችው ግለሰቧ እንደምትለቀቅ ከተሰማ በኋላ በርካቶች የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። የፓኪስታን መንግሥት ከእስር ብትለቀቅም ከሀገር እንዳትወጣ እንዲከለከል በፍርድ ቤት እንደሚጠይቅ ተናግሮ ነበር።

በርካቶች አሲያ ቢቢ የእስልምና ኃይማኖትን ተሳድባለች በማለት በስቅላት እንድትገደል የሚጠይቁ ነበሩ።

የአንድ እስላማዊ ቡድን መሪ ሶስቱም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞች "ሊገደሉ ይገባል" ሲል ተናግሮ የነበረ ሲሆን በጠንካራ ተቃውሞው የሚታወቀው ቲ ሊፒ ፓርቲ የቢቢ መለቀቅ ከመንግሥት ጋር ያለን ስምምነት መፍረስ ምልክት ነው ሲል መናገሩ የሚታወስ ነው።

ቢሆንም በአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱ የተነሳላት ባለፈው ዓመት የነበረ ሲሆን የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በአክራሪዎች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ሐገራት ለአሲያ ቢቢ ጥገኝነት ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነው ነበር።

ተቃዋሚዎቿ ፊት ፎቶ የተነሳችው ሙስሊም ሴት

አሲያ ቢቢ ፍርድ ቤት በቀረበችበት ችሎቶች ላይ ሁሉ ጥፋተኛ እንዳልሆነች ስትናገር ቆይታለች።

አሲያ ቢቢ ተብላ የምትታወቀው አሲያ ኖሬ ፓኪስታንን ለቃ የምትወጣበት መንገድ እሰከሚመቻችላት ድረስም ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ ስፍራ እዚያው ፓኪስታን ውስጥ ስትኖር ነበር።

"መንግሥት የሚደግፈው የሙስሊሙን ሕብረተሠብ ነው" ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

የፓኪስታን ባለስልጣናት አሲያ ቢቢ ፓኪስታንን ለቃ እንደወጣች ዛሬ የገለፁ ሲሆን የሄደችበትን አገር ግን ግልፅ አላደረጉም። ይሁን እንጂ ጠበቃዋ ሳይፍ ኡል ማሉክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ኢሲያ ቢቢ ካናዳ ገብታለች። ልጆቿም በካናዳ ጥገኝነት ተሰጥቷቸዋል።

የ48 ዓመቷ አሲያ ቢቢ የአራት ልጆች እናት ስትሆን ኃይማኖት ላይ ስድብ በመሰንዘር የሞት ፍርድ ተፈርዶባት የነበረች የመጀመሪያዋ ሴት ናት።

በፓኪስታን ከአውሮፓውያኑ 1990 ጀምሮ በትንሹ 65 የሚሆኑ ሰዎች በእስልምና ኃይማኖት ላይ ስድብ በመሰንዘራቸው ተገድለዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ