አሜሪካ፡ የዘር ልዩነት ለእናቶች ሞት ምክንያት ሆኗል

ነፍሰጡር ሴት ወንበር ላይ ተቀምጣ Image copyright Getty Images

በአሜሪካ ከእርግዝና ጋር በተያያዘ የሚሞቱ እናቶች ቁጥር ማሻቀቡን የበሽታ ቁጥጥር ማዕከል (ሲ ዲ ሲ) በጥናቴ ደርሸበታለሁ ብሏል፤ ምከንያቱ ደግሞ ጥቁር መሆን ነው ሲል አመላክቷል።

ጥናቱ እንዳመለከተው ጥቁር አሜሪካውያን፣ የአላስካ ነባር አሜሪካውያን፣ እና ነባር አሜሪካውያን እናቶች ሞት ቁጥር ከነጭ አሜሪካውን በሦስት እጥፍ ይበልጣል።

በየዓመቱ 700 ገደማ የሚሆኑ ሴቶች ከእርግዝና ጋር በተያያዘ እንደሚሞቱም ጥናቱ ይፋ አድርጓል። 60 በመቶ የሚሆነው የሞት ምክንያትም ቀድሞ መከላከል የሚቻል ነው ሲል ጥናቱ ጠቅሷል።

በአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል (Centers for Disease Control) ዳይሬክተር የሆኑት አን ሹቻት "በጣም በርካታ ሴቶች ቀድሞ መከላከል በሚቻልና ከእርግዝና ጋር በተያያዘ ይሞታሉ" ብለዋል። እነዚህን ችግሮችም ለመለየትና ለመፍታት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል።

በሕይወት ከሌለች እናት የተወለደችው ሕፃን

ከዚሁ ጋር በተገናኘም በዚህ ጥናት ያልተካተቱት የአሜሪካ የፅንስና ማህፀን ሐኪሞች ኮሌጅ ባለፈው ሳምንት አንድ መግለጫ አውጥቶ ነበር፤ በመግለጫቸውም ላይ በጤና ጥበቃው ስርዓትና በጤና ተቋማት የዘር መድሎ እንደሚፈፀም ገልፀዋል።

"ለእናቶች ሞት ምክንያት ዋናው ዘረኝነት ነው" ሲሉም በመግለጫቸው አስፍረዋል። "ችግሩ በጤና ተቋማትና በጤና ጥበቃ ሥርዓቱ ያለው ጥግ የነካ ዘረኝነት ዋናው ምክንያት እንደሆነ አስታውቋል።

ሲ ዲ ሲ በጥናቱ ከአውሮፓውያኑ 2011-2017 ድረስ ያለውን የእናቶች ሞት የተመለከተ ሲሆን ባለፉት አምስት ዓመታት ከእርግዝና ጋር በተያያዘ 3400 ሞት መመዝገቡን አስታውቋል።

በነጭ ሴቶች፤ ከሚወለዱ 100 ሺዎቹ 13 እናቶች ሲሞቱ፤ ይህ በጥቁር እናቶች ሲታይ ደግሞ ቁጥሩ በሦስት እጥፍ አድጎ ከ100 ሺዎቹ 42 እናቶች ሕይወታቸው ያልፋል።

አራት ልጆች የወለዱ እናቶች ከግብር ነፃ ሊሆኑ ነው

በነባር አሜሪካውያን እና በአላስካ ሴቶች ሲታይ ቁጥሩ 32.5 ሲሆን ኢሲያ እና ፓስፊክ ሴቶች 14.2 ሆኖ ተመዝግቧል። በጣም ዝቅተኛ ቁጥር የሚያሳው ሂስፓኒክ ሴቶች ሲሆን ከ100 ሺዎቹ የሚሞቱት 11 እናቶች ብቻ ናቸው።

ዋነኛው በእርግዝና ወቅት ለሞት ከሚዳርጉ ምክንያቶች የተጠቀሰው ከልብ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሲሆኑ፤ የልብ ህመምና ስትሮክ ሞቱን በሦስት እጥፍ ይጨምሩታል።

በዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መሠረት በአሜሪካ የእናቶች ሞት ቁጥር መጨመሩ ከሌላው ዓለም ጋር ሲነፃፀር ያልተጠበቀ ቢሆንም በዓለም ከአውሮፓውያኑ 1990 እና 2015 መካካል ባሉት ዓመታት የእናቶች ሞት በ44 በመቶ እንደቀነሰ ታውቋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ